በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መጥፎ ልማዴን ለማሸነፍ ረድቶኛል

መጥፎ ልማዴን ለማሸነፍ ረድቶኛል

መጥፎ ልማዴን ለማሸነፍ ረድቶኛል

● ባለፈው ዓመት ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1 (እንግሊዝኛ) የተባለ መጽሐፍ ወጥቶ ነበር። በዚህ መጽሐፍ ገጽ 180 ላይ ጻድቅ ሰባት ጊዜ እንኳ ቢወድቅ ይነሳል የሚለው በ⁠ምሳሌ 24:16 ላይ የሚገኘው ጥቅስ ተብራርቷል። ይህ ሐሳብ በጣም ያበረታታት አንዲት ወጣት እንዲህ ብላለች፦ “በዚህ ገጽ ላይ ያለው ምሳሌ ያለብኝን መጥፎ ልማድ ለማሸነፍ የማደርገውን ጥረት አምላክ እንደሚያስተውል እንድገነዘብ ረድቶኛል። . . . ይህ መጽሐፍ ችግሬን በግልጽ ጠቅሼ መጸለይ እንደምችልና የሚሰማኝን የዋጋ ቢስነት ስሜት ለመቋቋም የአምላክን እርዳታ መጠየቅ እንዳለብኝ አስገንዝቦኛል። በመሆኑም ይህ ልማድ ሊያገረሽብኝ ሲል ወደ አምላክ እጸልያለሁ፤ እንዲህ ማድረጌ ደግሞ መጥፎ ልማዴን ለማሸነፍ ረድቶኛል።

“ባለፉት ዓመታት ከ77 ጊዜ በላይ በዚህ መጥፎ ልማድ ብሸነፍም ያለብኝን ድክመት ማሸነፍ እንደምችል እርግጠኛ ነኝ። አሁን እንደቀድሞው በዚህች ምድር ላይ ካሉ ኃጢአተኞች ሁሉ እኔ የከፋሁ እንደሆንኩ አይሰማኝም።”

ይህን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

❑ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

❑ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።