በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአንባቢዎቻችን

ከአንባቢዎቻችን

ከአንባቢዎቻችን

በማይድን በሽታ የተያዙ ሰዎችን የሚንከባከብ ተቋም—ዓላማው ምንድን ነው? (ሐምሌ 2011) ከበጎ አድራጎት ጋር የተያያዘ ሥራ የምሠራ እንደመሆኔ መጠን በማይድን በሽታ የተያዙ ሰዎችን መንከባከብ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ሥልጠና ወስጃለሁ፤ በመሆኑም የሐምሌ 2011 ንቁ! መጽሔት ላይ ያወጣችሁት ሐሳብ ትክክል እንደሆነ አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁ። በማይድን በሽታ የተያዙ ሰዎችን በደንብ ለመንከባከብ የሚያስችሉ በሚገባ የተደራጁ ተቋማት በዛሬው ጊዜ በጣም ያስፈልጋሉ። የአምላክ መንግሥት የሚመጣበትን ጊዜ በጉጉት እየተጠባበኩ ነው፤ በዚህ ወቅት ማንም ሰው “ታምሜአለሁ” አይልም እንዲሁም አምላክ እንባችንን ከዓይኖቻችን ላይ ይጠርጋል።—ኢሳይያስ 33:24፤ ራእይ 21:3, 4

ኤም. አር.፣ ጣሊያን

ታይሮይድ ዕጢህ እንዴት ነው? (ግንቦት 2009) በዚህ ርዕስ ሥር ለቀረበው ሐሳብ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። ከተወሰነ ጊዜ በፊት ታይሮይድ ዕጢዬ ላይ የሆነ ችግር እንዳለ ብገነዘብም ምንም ዓይነት እርምጃ አልወሰድኩም ነበር። ይሁንና ይህንን ርዕስ ካነበብኩ በኋላ ወደ ባለሙያ ሄጄ ተመረመርኩ፤ በዚህም ምክንያት ግሬቭስ የተባለ በሽታ እንደያዘኝ አወቅኩ። ደስ የሚለው፣ በሽታዬ አስከፊ ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት ሊታወቅ ችሏል። በጣም አመሰግናችኋለሁ።

ቲ. ኬ.፣ ጃፓን

እምነት ልትጥልበት የምትችል መጽሐፍ—ክፍል 1-7 (ከኅዳር 2010–ግንቦት 2011) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጠቀሱ የዓለም ኃያላን መንግሥታት የሚናገረውን ይህን ሰባት ተከታታይ ርዕስ ስላወጣችሁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ፤ ርዕሶቹ ከፍተኛ ምርምር የተደረገባቸውና ግሩም በሆነ መንገድ የተጻፉ ናቸው። ድንቅ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች የሆኑት እነዚህ ርዕሶች በብሮሹር መልክ ተዘጋጅተው ቢወጡ በጣም ደስ ይለኛል። እነዚህ ተከታታይ የሆኑ የታሪክ ዘገባዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ትንቢቶችን ላስጻፈው አካል ማለትም ለይሖዋ ጥልቅ የሆነ አክብሮት እንድናሳይ ያደርጉናል።

ጂ. ኤች.፣ ዩናይትድ ስቴትስ

የወጣቶች ጥያቄ . . . ማኅበራዊ ድረ ገጾችን በተመለከተ ምን ማወቅ ይኖርብኛል? (ሐምሌ 2011) በዚህ ርዕስ ሥር ለቀረበው ሐሳብ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። ዕድሜዬ 26 ዓመት ሲሆን [በማኅበራዊ ድረ ገጽ ላይ] የራሴን አካውንት ለመክፈት እያሰብኩ ነበር፤ ሆኖም ይህን ለማድረግ ያሰብኩት ብዙ ጓደኞች እንዲኖሩኝ ፈልጌ ሳይሆን በርካታ ሰዎች አካውንት እንድከፍት ስለገፋፉኝ ነው። ይህ ርዕስ በጣም ረድቶኛል። ጓደኛ ለማግኘት የግድ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ተጠቃሚ መሆን አያስፈልግም።

ኤም. ፒ.፣ ፊሊፒንስ

ይህ ርዕስ ስለ ማኅበራዊ ድረ ገጽ መጥፎነት ብቻ የሚናገር መስሎኝ ነበር። ሆኖም ርዕሱ የያዘው ሐሳብ ሚዛናዊነት የሚንጸባረቅበት ነው። ማኅበራዊ ድረ ገጽ ያሉትን ጥሩም ሆነ መጥፎ ገጽታዎች የሚያቀርብ ከመሆኑም በላይ እንዲህ ባሉ ድረ ገጾች ስንጠቀም ሊያጋጥሙን ከሚችሉ አደጋዎች እንዴት ራሳችንን መጠበቅ እንደምንችል ምክር ይሰጣል። የግል መረጃዎችን በኢንተርኔት ላይ ስናስቀምጥ ምን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብን የተሰጠውን ሐሳብ መቼም ቢሆን አልረሳውም።

ኬ. ደብልዩ.፣ ዩናይትድ ስቴትስ

ለተሳካ የቤተሰብ ሕይወት ቁልፍ የሆኑ ነገሮች (ጥቅምት 2009) ቤተሰባችን ከዚህ ልዩ እትም ከፍተኛ ጥቅም አግኝቷል። በተለይ ደግሞ ሰባቱን ቁልፍ ነጥቦች አንድ በአንድ በሚያብራሩት ርዕሶች ሥር የቀረቡትን “ይህን ለማድረግ ሞክር” የሚሉትን ሣጥኖች በጣም ወድጃቸዋለሁ። በዚህ ርዕስ ሥር የቀረቡትን ቀጥተኛ ምክሮች በቤተሰባችን ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ጀምረናል።

ኤች. ኤች.፣ ኮሪያ

ቤተሰብ የሚወያይበት በቋሚነት ስለሚወጣው ስለዚህ ዓምድ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። የስድስት ዓመቷ ልጃችን ለልጆች የቀረበውን የሥዕል ጥያቄ የምትወደው ሲሆን በተለይ ሥዕሎችን ቀለም መቀባት ያስደስታታል። እነዚህ ርዕሶች፣ ወላጆች ልጆቻቸውን ገና ከጨቅላነታቸው ጀምሮ የማሠልጠን ኃላፊነታቸውን እንዲያስታውሱ ያደርጓቸዋል። ለትንንሽ ልጆች ብላችሁ የምታዘጋጇቸው እንዲህ ያሉ ርዕሶች በጣም ጠቃሚ ናቸው።

ኤም. ፒ.፣ ፖላንድ