በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

4. ምግብ ቤት ስትመገቡ አስተዋይ ሁኑ

4. ምግብ ቤት ስትመገቡ አስተዋይ ሁኑ

4. ምግብ ቤት ስትመገቡ አስተዋይ ሁኑ

ጄፍ የተባለ ጤናማና ጠንካራ የሆነ የ38 ዓመት ሰው ከቤተሰቡ ጋር ምግብ ለመብላት በፒትስበርግ፣ ፔንስልቬንያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ወደሚገኝ አንድ ምግብ ቤት ሄደ። ከአንድ ወር በኋላ ጄፍ በጉበት በሽታ ምክንያት ሞተ። የሕመሙ መንስኤ ምን ነበር? በሄፕታይተስ ኤ የተበከለ ባሮ ሽንኩርት መመገቡ ነው።

በአንድ ምዕራባዊ አገር ሕዝቡ ለምግብ ከሚያውለው ገንዘብ ውስጥ ግማሽ የሚያህለውን የሚያጠፋው በምግብ ቤቶች ነው ማለት ይቻላል። የሚያሳዝነው ግን በዚያው አገር ከሚከሰቱት ምግብ ወለድ ሕመሞች ግማሽ ያህል ለሚሆኑት መንስኤው በምግብ ቤቶች የሚቀርበው ምግብ ነው።

እውነት ነው፣ ውጭ የምትበላ ከሆነ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦችን የሚገዛው፣ ወጥ ቤቱን የሚያጸዳውና ምግቡን የሚያበስለው ሌላ ሰው ነው። ያም ቢሆን የምትበላበትን ቦታና የምትበላውን ምግብ እንዲሁም የተረፈህን ምግብ እንዴት ወደ ቤት እንደምትወስድ መወሰን ትችላለህ።

አካባቢውን አስተውሉ

በብራዚል የምትኖረው ዳያን እንዲህ ብላለች፦ “ወደ አንድ ምግብ ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ ስንሄድ ጠረጴዛዎቹ፣ የጠረጴዛዎቹ ልብሶች፣ ዕቃዎቹና አስተናጋጆቹ ንጹሕና ጽዱ መሆናቸውን እመለከታለሁ። ካልሆነ ግን ወጥተን ወደ ሌላ ምግብ ቤት እንሄዳለን።” በአንዳንድ አገሮች የጤና ጥበቃ ባለሥልጣናት የምግብ ቤቶችን ንጽሕና በየጊዜው የሚመረምሩ ሲሆን ባገኙት ውጤት ላይ ተመሥርተው ደረጃ በማውጣት ለሕዝብ ያሳውቃሉ።

የተረፋችሁን ምግብ ወደ ቤት ስትወስዱ ተጠንቀቁ

የዩናይትድ ስቴትስ ምግብና መድኃኒት አስተዳደር እንደሚከተለው በማለት ይመክራል፦ “ምግብ ቤት ከተመገባችሁ በኋላ በሁለት ሰዓት ውስጥ ቤታችሁ የማትደርሱ ከሆነ የተረፋችሁን ምግብ ይዛችሁ አትሂዱ።” የተረፋችሁን ምግብ የምትወስዱ ከሆነ ግን በቀጥታ ወደ ቤት ሄዳችሁ ማቀዝቀዣ ውስጥ ክተቱት፤ በተለይ ደግሞ የአየሩ ሙቀት ከ32 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በላይ ከሆነ እንዲህ ማድረጋችሁ አስፈላጊ ነው።

በእነዚህ ተከታታይ ርዕሶች ውስጥ የቀረቡትን አራት ነጥቦች ተግባራዊ ካደረጋችሁ ምግባችሁ እንዳይበከል መከላከል ትችላላችሁ።

[በገጽ 7 ላይ የሚገኝ ሣጥን/​ሥዕል]

ልጆቻችሁን አሠልጥኑ፦ “ለጤና አደገኛ ሊሆኑ የሚችሉ ምግቦችን መለየት እንዲችሉ ልጆቻችንን አሠልጥነናቸዋል።”​—ኖኤሚ፣ ፊሊፒንስ