አንተ ምን ለውጥ ታመጣ ነበር?
አንተ ምን ለውጥ ታመጣ ነበር?
በዓለማችን ላይ ካሉት ሁኔታዎች አንተን የበለጠ የሚረብሽህ የትኛው ነው?
ረሃብ
ድህነት
በሽታ
ወንጀል
የፍትሕ መጓደል
ጦርነት
የአካባቢ ብክለት
ጥላቻ
ከታች ከተዘረዘሩት መካከል እውን ሆኖ ማየት የሚያጓጓህ የትኛው ነው?
በአገሮች መካከል ሰላም ሰፍኖ ማየት
ጥሩ ሕክምና እንደ ልብ ማግኘት
መድልዎ የሌለበት ዓለም
በቂ ምግብና የመጠጥ ውኃ ማግኘት
ከስጋት ነፃ የሆነ የመኖሪያ ሰፈር
ንጹሕ የሆነ አካባቢ
ፍትሕ የሰፈነበት ሥርዓት
ዓለማችን ተለውጦ የማየት ሕልምህ እውን የሚሆን ይመስልሃል? አንዳንዶች፣ የዚህ ጥያቄ መልስ የተመካው በመንግሥታት ላይ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ታዲያ የዓለም መሪዎች ምድራችን የተሻለች ቦታ እንድትሆን ማድረግ ይችላሉ? እውነታው ምን ያሳያል?