ንቁ! መስከረም 2012
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
ለብዙዎች አስፈሪ የሆነው የዓለም መጨረሻ
ሰዎች፣ ዛሬ ያለው ሥልጣኔ የመጥፋት አደጋ እንዲጋረጥበት ያደርጋሉ ብለው የሚያስቧቸውን ስድስት ክስተቶች ተመልከት።
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
የዓለም መጨረሻ የምታስበው ዓይነት ላይሆን ይችላል
መጽሐፍ ቅዱስ፣ ታላቅ ለውጥ መምጣቱ የተረጋገጠ ነገር እንደሆነ ይገልጻል። ታዲያ ይህ ለውጥ ምን ያስከትላል?
የወጣቶች ጥያቄ
ከትዳር ምን መጠበቅ እችላለሁ?—ክፍል 1
ትዳር ስትመሠርት ምን ጥቅሞች እንደምታገኝ መጠበቅ ትችላለህ? ምን ዓይነት ተፈታታኝ ሁኔታዎችስ ሊያጋጥሙህ ይችላሉ?
መጽሐፍ ቅዱስ—ትክክለኛ ትንቢት የያዘ መጽሐፍ—ክፍል 5
ኢየሱስ ክርስቶስ ጊዜውንና ጉልበቱን በመጠቀም ‘የመንግሥቱን ምሥራች’ አውጇል። ታዲያ እሱ የሰበከው መልእክት ኢየሱስ ሲሞት ተዳፍኖ ቀርቷል?
ዘመናዊ መካነ አራዊትን መጎብኘት
ዘመናዊ መካነ አራዊት የሚሰጠው አገልግሎት ምንድን ነው? ከምድረ ገጽ ሊጠፉ የተቃረቡ እንስሳትን ለመታደግስ ምን ጥረት ያደርጋል?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
የአንድ ሃይማኖታዊ ድርጅት አባል መሆን ያስፈልግሃል?
አንዳንዶች ሃይማኖታዊ ድርጅቶችን ትተው የሚወጡት ለምንድን ነው? አምላክ የሚፈልገው በምን መንገድ እንድናመልከው ነው?
የመካከለኛው ዘመን የሕክምና ሊቃውንት
እንደ አቨሴና ያሉ የሕክምና ሊቃውንት የደረሱባቸው ግኝቶችና አዳዲስ እውቀቶች ለዘመናዊው የሕክምና ዘዴ አስተዋጽኦ ያበረከቱት እንዴት እንደሆነ የሚገልጸውን ይህን ዘገባ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
ያለ ደም የሚሰጡ አማራጭ ሕክምናዎች
ከ40 ከሚበልጡ አገሮች የተውጣጡ እውቅ ባለሙያዎች ያለ ደም የሚሰጡ አማራጭ ሕክምናዎችን አስመልክቶ ስላገኙት መረጃ የሰጡትን አስተያየት እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
ከዓለም አካባቢ
የተካተቱ ዜናዎች፦ የሕክምና ቱሪዝም በእስያ፣ በአንድ ጊዜ ብዙ ነገሮችን ማከናወን የሚሞክሩ ሰዎች፣ ከአጫሾች የሚወጣ የሲጋራ ጭስ፣ በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ ሕይወታቸውን የሚያጡ ሰዎች እና በሩሲያ ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩ።
ሎሚ—ሁለገቡ ፍሬ
ልትበላው፣ ጨምቀህ ልትጠጣው እንዲሁም ጥሩ መዓዛ ያለው ዘይት ለማውጣት ልትጠቀምበት ትችላለህ። እነዚህ ሎሚ ካሉት ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ጥቂቶቹ ናቸው። ስለዚህ ሁለገብ ፍሬ የተዘጋጀውን ይህን ርዕስ በማንበብ ተጨማሪ እውቀት ማግኘት ትችላለህ።
ቤተሰብ የሚወያይበት
በዚህ ወር፣ ሥጋ ደዌ ስለነበረበት አንድ አመስጋኝ ሰው እንዲሁም ስለ ሙሴና በማደጋስካር ስለሚኖሩ የይሖዋ መሥክሮች በማንበብ እውቀትህን እንድታሰፋ እንጋብዝሃለን።