በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

የሚከተሉትን ሥዕሎች ከጥቅሶቹ ጋር አዛምድ

ዘፍጥረት 1:1-31ን አንብብ። እያንዳንዱን ሥዕል ተስማሚ ከሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ጋር አዛምድ። (ሥዕሎቹ የተቀመጡት ተዘበራርቀው ነው።)

ለውይይት፦

 

የፍጥረት ቀናት የ24 ሰዓት ርዝመት እንደሌላቸው እንዴት እናውቃለን?

ፍንጭ፦ ዘፍጥረት 2:4ን (በ1954 ትርጉም) እና መዝሙር 90:4ን አንብብ።

ከፍጥረት ሥራው ስለ ይሖዋ ምን ትማራለህ?

ፍንጭ፦ መዝሙር 115:16ን፣ ሮም 1:20ን፣ 1 ዮሐንስ 4:8ን እና ራእይ 4:11ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

 

በቤተሰብ ደረጃ ወጣ ብላችሁ የፍጥረት ሥራዎችን እየተመለከታችሁ ለመዝናናት ዕቅድ አውጡ። መካነ አራዊት፣ የአትክልት ስፍራ ወይም ስለ ሰማይ አካላት ገለጻ የሚሰጡ ቦታዎችን በመጎብኘት ስለምትወዷቸው እንስሳት፣ ዕፅዋት ወይም ፕላኔቶች አዳዲስ ነገሮችን ለማወቅ ሞክሩ። ከዚያም የፍጥረት ሥራዎቹን በመመርመር ስለ ይሖዋ የተማራችኋቸውን ነገሮች በቤተሰብ ተወያዩ።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 23 ዮናታን

ጥያቄ

  1. ሀ. ዮናታን የ․․․․․ የበኩር ልጅ ነው።

  2. ለ. እውነት ወይስ ሐሰት? የዮናታን አባት ዮናታን ላይ ጦር ወርውሮበታል።

  3. ሐ. ዮናታን በተለይ ይወደው የነበረው ማንን ነው? ለምንስ?

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

ዮናታን ከአባቱ ከሳኦል ቀጥሎ የሚነግሥ እንዲሁም ዳዊትን 30 ዓመት ገደማ የሚበልጠው ቢሆንም ዳዊትን በይሖዋ እንደተቀባ ንጉሥ በመመልከት ደግፎታል። (1 ሳሙኤል 23:15-18) እንዲያውም ከቅናተኛው አባቱ፣ ከሳኦል እጅ አድኖታል። (1 ሳሙኤል 20:1-42) ዮናታን የተወው የትሕትና ምሳሌ ሌሎች መልካም ነገር ሲያገኙ አብረናቸው መደሰት እንደሚኖርብን ያስገነዝበናል።

መልስ

  1. ሀ. ንጉሥ ሳኦል—1 ሳሙኤል 14:47, 49

  2. ለ. እውነት—1 ሳሙኤል 20:33

  3. ሐ. ዳዊትን። ዳዊት ከጎልያድ ጋር ሲዋጋ የነበረውን ድፍረትና ለይሖዋ ያለውን ፍቅር በመመልከቱ ነበር።—1 ሳሙኤል 17:1 እስከ 18:4

ሕዝቦችና አገሮች

ፒያ ሶን አንግ እና ሱ ምያ ያዴና ልዊን እንባላለን፤ የ11 እና የ7 ዓመት ልጆች ስንሆን የምንኖረው በምያንማር ነው። በምያንማር ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 3,600፣ 6,300 ወይስ 10,000?

የምንኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከምያንማር በጣም ይርቃል?

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

መልስ

  1. 1 እና ረ

  2. 2 እና ለ

  3. 3 እና ሀ

  4. 4 እና ሠ

  5. 5 እና ሐ

  6. 6 እና መ

  7. 3,600