ንቁ! ጥር 2014 | በዓይነቱ ልዩ የሆነ ድረ ገጽ

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ የተሻለ ግንዛቤ ማግኘት ወይም የቤተሰብህ ሕይወት ይበልጥ አስደሳች እንዲሆን ማድረግ ትፈልጋለህ? ወጣት ከሆንክ ደግሞ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምክር ማግኘት ትፈልጋለህ? ሕጋዊው ድረ ገጻችን ለሁሉም ሰው የሚጠቅም መረጃ ይዟል።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

በዓይነቱ ልዩ የሆነ ድረ ገጽ

ድረ ገጻችንን በመጠቀም አንተም ሆንክ ቤተሰብህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሚገኘው ጊዜ የማይሽረው ጥበብ እንዴት መጠቀም እንደምትችል ተመልከት።

ከዓለም አካባቢ

ከርዕሰ ጉዳዮቹ መካከል፦ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች የሚኖሩ ልጆች ያላቸው መብት፣ በጣሊያን በኢንተርኔት አማካኝነት የሚደርስ ጥቃት ያስከተለው ፍርሃት እና በጃፓን የሥራ እድገት ለመቀበል ፈቃደኛ የማይሆኑ ወጣቶች ቁጥር እያደገ መሄድ

ቃለ ምልልስ

አንዲት የማይክሮባዮሎጂ ባለሙያ ስለምታምንበት ነገር ምን ትላለች?

በታይዋን የምትኖር ፌንግ-ሊንግ ያንግ የተባለች ሳይንቲስት አንድ ሕዋስ ከሚገመተው በላይ ውስብስብ መሆኑ በዝግመተ ለውጥ ንድፈ ሐሳብ ላይ የነበራትን አመለካከት እንድትለውጥ አድርጓታል። ለምን?

ለቤተሰብ

የእኩዮችን ተጽዕኖ መቋቋም የሚቻልበት መንገድ

የእኩዮች ተጽዕኖ ጥሩ ሰዎችን መጥፎ ነገር እንዲያደርጉ ሊገፋፋቸው ይችላል። የእኩዮች ተጽዕኖን በተመለከተ ማወቅ የሚገባህ ነገር ምንድን ነው? እንዴትስ መቋቋም ትችላለህ?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ሥነ ፍጥረት

መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ሕያዋን ነገሮችን ስለ ፈጠረባቸው ስድስት ‘ቀናት’ ይናገራል። እነዚህ ቀናት የ24 ሰዓት ርዝማኔ ያላቸው ናቸው?

አገሮችና ሕዝቦች

ጣሊያንን እንጎብኝ

ጣሊያን ዘመናት ባስቆጠረው ታሪኳ፣ የተለያየ ገጽታ በተላበሰው መልክዓ ምድሯና ተጫዋች በሆነው ሕዝቧ ትታወቃለች። ስለዚች አገርም ሆነ በዚያ ያሉት የይሖዋ ምሥክሮች እያደረጉት ስላለው እንቅስቃሴ አንብብ።

ንድፍ አውጪ አለው?

የሸረሪት የማጣበቅ ችሎታ ሚስጥር

የሸረሪት ድር እንደ አስፈላጊነቱ በኃይል የሚያጣብቅ ወይም በቀላሉ የሚላቀቅ ሙጫ አለው። ይህ ሊሆን የቻለው እንዴትና ለምን እንደሆነ ተመልከት።