በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

በዓይነቱ ልዩ የሆነ ድረ ገጽ

በዓይነቱ ልዩ የሆነ ድረ ገጽ
  • መጽሐፍ ቅዱስን 50 በሚያህሉ ቋንቋዎች፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ መረጃዎችን ደግሞ ከ500 በሚበልጡ ቋንቋዎች አንብብ።

  • ወደ 70 በሚጠጉ የምልክት ቋንቋዎች የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ተመልከት።

  • ድረ ገጹን በመቶዎች በሚቆጠሩ ቋንቋዎች ቃኝ።

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ላይ የተመሠረቱ በድምፅ ብቻ የተቀረጹ ድራማዎችን አዳምጥ።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ክንውኖች በሥዕላዊ መግለጫዎች ሕያው ሆነው ሲቀርቡ እይ።

  • በሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተፈታታኝ ሁኔታዎችን ለመቋቋም የሚረዱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድራማዎችንና ቪዲዮዎችን ተመልከት።

  • ኤሌክትሮኒክ መጻሕፍትን፣ የመጽሔት ርዕሶችንና የድምፅ ፋይሎችን ያለ ምንም ክፍያ አውርድ።

  • ከ100 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች ወደተዘጋጀው የመረጃ ክምችት የሚያስገባውን የመጠበቂያ ግንብ ማኅበርን የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት በመጠቀም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምርምር አድርግ።

ለባለትዳሮች

“የተሳካ የቤተሰብ ሕይወት እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ። እኔና ባለቤቴ በተለይ ልጆች ከወለድን ወዲህ በትዳራችን ውስጥ የተለያዩ ችግሮች ገጥመውናል። እርዳታ ያስፈልገናል”

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦

“ቤት በጥበብ ይሠራል፤ በማስተዋልም ይጸናል።”—ምሳሌ 24:3

ድረ ገጹ ያሉት ጠቃሚ ገጽታዎች

“ባለትዳሮች እና ወላጆች” የሚለው ክፍል እንደሚከተሉት ያሉትን ተፈታታኝ ሁኔታዎች እንድትወጡ ይረዳችኋል፦

  • የመጀመሪያውን ዓመት የትዳር ሕይወት ስኬታማ ማድረግ

  • ከአማቾች ጋር ተስማምቶ መኖር

  • ለልጆች ተግሣጽ መስጠት

  • ጭቅጭቅ

  • ገንዘብ ነክ ችግሮች

(የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > ባለትዳሮች እና ወላጆች በሚለው ሥር ይገኛል)

ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? የተባለው መጽሐፍ ገና ነጠላ ሳላችሁ ለትዳር ከመዘጋጀት አንስቶ ለአረጋውያን ወላጆች እንክብካቤ እስከ ማድረግ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የሚኖረውን የቤተሰብ ሕይወት በተመለከተ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ያነሳል።

(www.pr418.com/am ድረ ገጽ ላይም ማግኘት ይቻላል። የሕትመት ውጤቶች > መጻሕፍትና ብሮሹሮች በሚለው ሥር ይገኛል)

ለወላጆች

“ከልጆቼ የሚበልጥብኝ ምንም ነገር የለም። ካደጉ በኋላ የምኮራባቸው ሰዎች እንዲሆኑልኝ እፈልጋለሁ”

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦

“ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፤ በሚሸመግልበት ጊዜ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።”—ምሳሌ 22:6

ድረ ገጹ ያሉት ጠቃሚ ገጽታዎች

“ልጆች” የሚለው ክፍል ሥዕላዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፣ የሥዕል ጨዋታዎች፣ ቪዲዮዎችና ልጆቻችሁን ለማስተማር ሊረዷችሁ የሚችሉ እንደሚከተሉት ያሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ይዟል . . .

  • ታዛዥ ሁን

  • ደግነት አሳይ

  • እርስ በርስ ተስማሙ

  • “አመሰግናለሁ” በል

(የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > ልጆች በሚለው ሥር ይገኛል)

የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ እና ከታላቁ አስተማሪ ተማር የተባሉት መጻሕፍት በሚያማምሩ ሥዕሎች ያሸበረቁ ሲሆን ከልጆችህ ጋር አብረህ እንድታነባቸው የተዘጋጁ ናቸው።

(www.pr418.com/am ላይም ማግኘት ይቻላል። የሕትመት ውጤቶች > መጻሕፍትና ብሮሹሮች በሚለው ሥር ይገኛል)

ለወጣቶች

“ከትምህርት ቤት፣ ከወላጆች፣ ከጓደኞችና ከተቃራኒ ፆታ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙኝን አንዳንድ ሁኔታዎች እንዴት መያዝ እንደሚገባኝ የሚጠቁም ሐሳብ ባገኝ ደስ ይለኛል። አሁን ልጅ ስላልሆንኩ ማንም እንዲህ አድርግ፣ አታድርግ እንዲለኝ አልፈልግም”

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦

“በወጣትነትህም ዘመን ልብህ ደስ ያሰኝህ።”—መክብብ 11:9

ድረ ገጹ ያሉት ጠቃሚ ገጽታዎች

“ወጣቶች” የሚለው ክፍል እንደሚከተሉት ባሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሊጠቅሙህ የሚችሉ ጽሑፎችና ቪዲዮዎች ይዟል . . .

  • የብቸኝነት ስሜት

  • በትምህርት ቤት የሚያጋጥሙ ችግሮች

  • የወላጆችን መመሪያ መጣስ

  • ጉልበተኛ ልጆች የሚሰነዝሩት ማስፈራሪያ ወይም የፆታ ትንኮሳ

(የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > ወጣቶች በሚለው ሥር ይገኛል)

ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለው መጽሐፍ ጥራዝ 1 እና 2 ወደ 77 ለሚጠጉ በተደጋጋሚ ለሚነሱ ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ ይዘዋል።

(www.pr418.com/am ላይም ማግኘት ይቻላል። የሕትመት ውጤቶች > መጻሕፍትና ብሮሹሮች በሚለው ሥር ይገኛል)

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ማወቅ ለሚፈልጉ

“መጽሐፍ ቅዱስን ማወቅ እፈልጋለሁ። ታዲያ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?”

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦

“ቅዱስ መጽሐፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፈ ነው፤ እንዲሁም ለማስተማር . . . ይጠቅማል።”2 ጢሞቴዎስ 3:16

ድረ ገጹ ያሉት ጠቃሚ ገጽታዎች

የቅዱሳን መጻሕፍት አዲስ ዓለም ትርጉም ትክክለኛና በቀላሉ የሚገባ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ነው።

(የሕትመት ውጤቶች > መጽሐፍ ቅዱስ በሚለው ሥር ይገኛል)

“የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው” የሚለው ክፍል “ለሚደርስብን መከራ ተጠያቂው አምላክ ነው?” “ስንሞት ምን እንሆናለን?” እንደሚሉት ላሉ የተለያዩ ጥያቄዎች ግልጽ የሆነ መልስ ይሰጣል።

(የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው በሚለው ሥር ይገኛል)

“መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ ለመማር ጠይቅ” የሚለው ገጽ በነፃ ከምንሰጠው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንድትጠቀም ያስችልሃል።

(በመነሻው ገጽ ላይ የሚገኘውን “መጽሐፍ ቅዱስን ለመማር ጠይቅ” የሚለውን ሊንክ ጠቅ አድርግ)

“የማነበው ነገር አልገባ ስላለኝ መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ አቆምኩ። ‘ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?’ የሚለውን መጽሐፍ በመጠቀም ካጠናሁት በኋላ ግን መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያህል ቀላልና ግልጽ እንደሆነ ስረዳ በጣም ተገረምኩ።”ክርስቲና

በየዕለቱ 700,000 የሚያህሉ ሰዎች jw.org የተባለውን ድረ ገጽ ይመለከታሉ። አንተም ይህን ድረ ገጽ እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።