ንቁ! ጥቅምት 2014 | እውነተኛ ስኬት ምንድን ነው?
ስኬት አገኘህ የሚባለው ሕልምህን እውን ስታደርግ ነው? ወይም የተመኘኸውን ነገር ስታገኝ ነው? ወይስ ከዚህ የበለጠ ነገርን ይጨምራል?
ከዓለም አካባቢ
ከርዕሰ ጉዳዮቹ መካከል፦ አነስተኛ ጥሎሽ መስጠት ያለው አደጋ፣ ለባሕር ላይ ወንበዴዎች የተሰጠው የማስለቀቂያ ክፍያ እና የሚፈልሱ ወፎች የፈጸሙት አስገራሚ ጀብዱ።
ለቤተሰብ
ፈታኝ ስሜቶችን መቋቋም የሚቻልበት መንገድ
ሰዎች ከፈለጉ ፈታኝ የሆኑ ስሜቶችን ማሸነፍ ይችላሉ። ሁልጊዜ ትክክለኛ የሆነውን ለማድረግ ያለህን ቁርጠኝነት ለማጠናከር እንዲሁም በፈተና እንዳትሸነፍ የሚረዱህን ስድስት ምክሮች ተመልከት።
አገሮችና ሕዝቦች
ቤሊዝን እንጎብኝ
ይህች ትንሽ አገር ለጃጓሮች የተከለለ ፓርክ የሠራች የመጀመሪያዋ አገር ናት፤ የቤሊዝ ኮራል ሪፍ በርዝመቱ ከዓለም ሁለተኛ የሆነው ኮራል ሪፍ ክፍል ነው።
በምድር ወገብ አካባቢ የሚገኘው ደን በራሪ አትክልተኞች
በራሪ ቀበሮዎች በመባል የሚታወቁት ፍሬ በል የሌሊት ወፎች የምድርን ሥነ ምህዳር ለመጠበቅ በጣም አስፈላጊ ናቸው።