በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | እውነተኛ ስኬት ምንድን ነው?

አንተ ስኬትን የምትለካው እንዴት ነው?

አንተ ስኬትን የምትለካው እንዴት ነው?

ራስህን ለመፈተሽ የሚከተሉትን ሁኔታዎች አስብ።

እውነተኛ ስኬት እንዳገኘ የሚሰማህ ማን ነው?

  • አለማየሁ

    አለማየሁ የራሱ ንግድ አለው። ሐቀኛ፣ ታታሪና ትሑት ሰው ነው። ንግዱ ትርፋማ ስለሆነለት እሱና ቤተሰቡ የተመቻቸ ሕይወት ይመራሉ።

  • ካሳሁን

    ካሳሁንም በተመሳሳይ ንግድ ላይ የተሰማራ ሲሆን ከአለማየሁ የሚበልጥ ገቢ አለው። ይሁንና ከተፎካካሪዎቹ በልጦ ለመገኘት ሲል ከልክ በላይ ይሠራል፤ በዚህም ምክንያት ብዙ በሽታ ይዞታል።

  • ያኔት

    ያኔት ትምህርት የምትወድና በትጋት የምታጠና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነች። በመሆኑም በትምህርቷ ጥሩ ውጤት ታመጣለች።

  • ሔለን

    ሔለን ከያኔት የተሻለ ውጤት ያላት ሲሆን የደረጃ ተማሪ ነች፤ ነገር ግን ፈተና ላይ ትኮርጃለች፤ የመማር ፍላጎቷም አነስተኛ ነው።

ካሳሁን እና ሔለን ወይም አራቱም ግለሰቦች ስኬታማ እንደሆኑ ከተሰማህ ስኬትን የምትለካው ሰዎች ባገኙት ውጤት ብቻ ነው ማለት ነው፤ ውጤቱን ያገኙት በምን መንገድ ነው የሚለውን ግምት ውስጥ አላስገባህም።

ስኬታማ እንደሆኑ የሚሰማህ አለማየሁ እና ያኔት ብቻ ከሆኑ ግን ስኬትን የምትለካው በግለሰቡ ባሕርይ ወይም በሥራ ባሕሉ ነው ማለት ነው። ይህ ተገቢ የሆነ መሥፈርት ነው። እስቲ የሚከተሉትን ሁኔታዎች አስብ፦

  • ያኔት ለወደፊት ሕይወቷ የሚጠቅማት ከፍተኛ ውጤት ማግኘቷ ነው ወይስ ለትምህርት ፍቅር ያላት መሆኑ?

  • ለአለማየሁ ልጆች የሚሻለው የቱ ነው? ገንዘብ ሊገዛ የሚችለውን ነገር ሁሉ ማግኘታቸው ነው ወይስ አባታቸው ከነሱ ጋር ጊዜ የሚያሳልፍ መሆኑ?

ከዚህ የምናገኘው ትምህርት፦ እውነተኛ ያልሆነ ስኬት የሚለካው ከውጭ በሚታዩ ነገሮች ነው፤ እውነተኛ ስኬት የሚለካው ግን ከትክክለኛ መሥፈርቶች አንጻር ነው።