በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በዓይነቱ ልዩ የሆነ በዓል—እርስዎስ በዚያ ይገኙ ይሆን?

በዓይነቱ ልዩ የሆነ በዓል—እርስዎስ በዚያ ይገኙ ይሆን?

በዓይነቱ ልዩ የሆነ በዓል—እርስዎስ በዚያ ይገኙ ይሆን?

ከ3, 500 ዓመታት በፊት ትልቅ ግምት በሚሰጠው አንድ ዕለት ይሖዋ አምላክ በግብጽ ባርነት ሥር የሚገኝ እያንዳንዱ እስራኤላዊ ቤተሰብ አንድ በግ ወይም ፍየል አርዶ ደሙን በበሩ መቃንና ጉበን ላይ እንዲረጭ አዝዞ ነበር። በዚያው ምሽት የአምላክ መልአክ ይህ ምልክት ያላቸውን በሮች እያለፈ በሁሉም ግብጻውያን ቤቶች ውስጥ የሚገኙትን በኩር ወንድ ልጆች ገደለ። ከዚያ በኋላ እስራኤላውያን ከባርነት ነጻ ወጡ። አይሁዳውያን ያን ሁኔታ ለማሰብ የማለፍን በዓል በየዓመቱ አክብረዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ለእርሱ የመጨረሻ የሆነውን የማለፍ በዓል ከሐዋርያቱ ጋር አክብሮ እንደጨረሰ የመሥዋዕታዊ ሞቱ መታሰቢያ የሆነ እራት አቋቋመ። ለሐዋርያቱ ያልቦካ ቂጣ ሰጣቸውና “እንካችሁ፣ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው” አለ። ከዚያም በጽዋው የነበረውን ወይን ጠጅ አንስቶ ሰጣቸውና እንዲህ አለ:- “ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ ስለ ብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።” በተጨማሪም ኢየሱስ “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” ሲል ተናግሯል። (ማቴዎስ 26:​26-28፤ ሉቃስ 22:​19, 20) ኢየሱስ ተከታዮቹ በዚህ መንገድ የሞቱን መታሰቢያ በዓል እንዲያከብሩ አዝዟቸዋል።

በዚህ ዓመት የሚከበረው የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ በዓል ረቡዕ ሚያዝያ 19 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሚያዝያ 11) ቀን ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይሆናል። በመላው ዓለም የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች የሞቱን መታሰቢያ በዓል ኢየሱስ ባሳሰበው መንገድ ለማክበር በዚህ ልዩ ምሽት ይሰበሰባሉ። እርስዎም በበዓሉ ላይ ተገኝተው እንዲመለከቱ ሞቅ ያለ ግብዣ እናቀርብልዎታለን። እባክዎ ትክክለኛውን ቦታና ጊዜ በአቅራቢያዎ ከሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ጠይቀው ይረዱ።