በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመምህሩ መሠረተ ቢስ ጥላቻ ከወላጆች ተቃውሞ ገጠመው

የመምህሩ መሠረተ ቢስ ጥላቻ ከወላጆች ተቃውሞ ገጠመው

የመምህሩ መሠረተ ቢስ ጥላቻ ከወላጆች ተቃውሞ ገጠመው

በኢጣሊያ ካሳኖ ሙርጄ በሚባል ቦታ የሚኖር የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ለተወሰኑ ተማሪዎች በር ላይ የሚለጠፍ ምልክት አድሎ ወደ ቤታቸው ይልካቸዋል። በየቤታቸው መግቢያ በር ላይ እንዲለጠፍ ታስቦ የተዘጋጀው ይህ ምልክት “እኛ ካቶሊኮች ነን። ስለዚህ የይሖዋ ምሥክሮች ይህንን በር እንዳያንኳኩ እንጠይቃለን” የሚል ማሳሰቢያ የተጻፈበት ነበር።

ምንም እንኳን የአንዳንዶቹ ተማሪዎች ወላጆች የይሖዋ ምሥክሮች ባይሆኑም የመምህሩን ተግባር በጥብቅ ተቃውመዋል። ሙዎቪቲ ሙዎቪቲ የተባለው ጋዜጣ ‘እንዲህ ያለውን መልእክት ለልጆች መስጠት ልጆች እንደ እነርሱ ዓይነት አመለካከት የሌለውን ሰው ሁሉ እንዳይቀበሉ ወይም አንድ ሰው በእምነቱ “የተለየ” ስለሆነ ብቻ እንዲያገልሉት የሚያደርግ ባሕርይ እንዲኖራቸው የሚያበረታታ’ ነው በማለት ወላጆች በመምህሩ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ማሰማታቸውን ዘግቧል። ለጋዜጣው የጻፉ አንድ ወላጅ ይህን በበር ላይ የሚለጠፍ ምልክት “የአረም ዘር፣ ያለማወቅና የድንቁርና ውጤት” ሲሉ ጠርተውታል።

ከላይ ያለው ሪፖርት እንደሚያሳየው ሚዛናዊ አመለካከት ያላቸው ብዙ ሰዎች ሃይማኖታዊ ጥላቻን በሰዎች ልብ ውስጥ መዝራት የሚያስከትለውን አደጋ ይገነዘባሉ። እንዲሁም የይሖዋ ምሥክሮች በመላው ኢጣሊያም ሆነ በዓለም ዙሪያ ለሚያከናውኑት ክርስቲያናዊ አገልግሎት አክብሮት አላቸው። ታዲያ እርስዎስ ምሥክሮቹ ‘ስለ ተስፋቸው እንዲያስረዱዎት’ ለምን አይጠይቋቸውም? ከእርስዎ ጋር ‘በጥልቅ አክብሮት’ ለመወያየት ፈቃደኞች ናቸው።​—⁠1 ጴጥሮስ 3:​15 NW