በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለይሖዋ እስከ መጨረሻው ታማኝ መሆን

ለይሖዋ እስከ መጨረሻው ታማኝ መሆን

ለይሖዋ እስከ መጨረሻው ታማኝ መሆን

በዛሬው ጊዜ ታማኝነት እምብዛም የማይታይ ነገር ቢሆንም የእውነተኛው አምላክ የይሖዋ አገልጋዮች ተለይተው እንዲታወቁ የሚያደርግ ባሕርይ ነው። ታማኝ ሰው ፈተናዎች ቢደርሱበትም ከእምነቱ ፍንክች አይልም። ከዚህም በላይ ጊዜው የቱንም ያህል ቢረዝም ከአቋሙ አይወላውልም። ለምሳሌ ጥሩ ንጉሥ የነበረውን የሕዝቅያስን ሁኔታ ተመልከት። መጽሐፍ ቅዱስ “ከእርሱም በኋላ ከእርሱም በፊት ከነበሩት ከይሁዳ ነገሥታት ሁሉ እርሱን የሚመስል አልነበረም” በማለት ይገልጻል። ሕዝቅያስን ከሌሎቹ ነገሥታት ልዩ ያደረገው ምን ነበር? ሐሰተኛ አምላክ በነበረው በሞሎክ አምላኪዎች ቢከበብም ‘ከእግዚአብሔር ጋር ተጣብቋል።’ አዎን፣ ሕዝቅያስ ‘እግዚአብሔርን ከመከተል አልራቀም፣ እግዚአብሔርም ለሙሴ ያዘዘውን ትእዛዛቱን ጠብቋል።’​—⁠2 ነገሥት 18:​1-6

ለይሖዋ እስከ መጨረሻው ታማኝ ሆኖ በመገኘት ረገድ ሌላው ምሳሌ ሐዋርያው ጳውሎስ ነው። ሐዋርያው ስላከናወነው ነገር በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘው ዘገባ ለአምላክ የሙሉ ነፍስ አገልግሎት በማቅረብ ረገድ ያሳየውን የጸና አቋም በማያሻማ ሁኔታ ያስረዳል። ጳውሎስ በምድራዊ ሕይወቱ መገባደጃ ላይ “መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፣ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፣ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ” ማለት ችሎ ነበር።​—⁠2 ጢሞቴዎስ 4:​7

ሕዝቅያስና ጳውሎስ እንዴት ያሉ ግሩም የታማኝነት ምሳሌዎች ናቸው! እኛም ለታላቁ አምላካችን ለይሖዋ እስከ መጨረሻው ታማኝ ሆነን በመገኘት እምነታቸውን እንምሰል።​—⁠ዕብራውያን 13:​7