በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥቅምት 7, 2000 የሚደረግ ዓመታዊ ስብሰባ

ጥቅምት 7, 2000 የሚደረግ ዓመታዊ ስብሰባ

ጥቅምት 7, 2000 የሚደረግ ዓመታዊ ስብሰባ

የፔንሲልቬንያ የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር አባላት ዓመታዊ ስብሰባ ጥቅምት 7, 2000 በኒው ጀርሲ ክፍለ ሀገር፣ በጀርሲ ከተማ 2932 ኬኔዲ በሊቨርድ በሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። አባላቱ ብቻ የሚገኙበት ስብሰባ ከጠዋቱ 3:​15 ከተደረገ በኋላ 4 ሰዓት ላይ አጠቃላይ ዓመታዊው ስብሰባ ይደረጋል።

ካለፈው ዓመት ወዲህ የፖስታ አድራሻቸውን የለወጡ የማኅበሩ አባላት መደበኛዎቹ የማስታወቂያ ደብዳቤዎችና የውክልና ማስረጃዎች በሐምሌ ወር ውስጥ እንዲደርሷቸው ለውጡን አሁኑኑ ለጸሐፊው ቢሮ ማስታወቅ ይኖርባቸዋል።

ከዓመታዊው የስብሰባ ማስታወቂያዎች ጋር ለአባላቱ የሚላኩት ውክልናዎች ከነሐሴ 1 በፊት ለማኅበሩ ጽሕፈት ቤት ተመልሰው መድረስ አለባቸው። እያንዳንዱ አባል በስብሰባው ላይ ራሱ ይገኝ ወይም አይገኝ እንደሆነ በመግለጽ ውክልናውን ወዲያውኑ ሞልቶ መመለስ አለበት። በስብሰባው ላይ ማን እንደሚገኝ የሚታወቀው በዚህ መሠረት ስለሆነ በእያንዳንዱ የውክልና ቅጽ ላይ የሚሰጠው መረጃ በዚህ ነጥብ ላይ ግልጽ መሆን ይኖርበታል።

መደበኛውን የሥራ ጉዳይና ሪፖርት ጨምሮ ጠቅ​ላላው ስብሰባ ከቀኑ 7 ሰዓት ወይም ከዚያ ብዙ ሳይ​ቆይ ያበቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከሰዓት በኋላ ስብሰባ አይኖርም። ያለው ቦታ የተወሰነ በመሆኑ መግባት የሚ​ቻለው በቲኬት ብቻ ይሆናል። ዓመታዊውን ስብሰባ ወደ ሌሎች አዳራሾች በስልክ ለማስተላለፍ የተደረገ ዝግጅት የለም።