አምላካዊ ጥበብ እንዴት ይገለጻል?
አምላካዊ ጥበብ እንዴት ይገለጻል?
“የድሀው ጥበብ ግን ተናቀች ቃሉም አልተሰማችም።” ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን ድሀ ቢሆንም በጥበቡ መላ ከተማዋን ከጥፋት ስላዳነው ሰው የሚናገረውን ታሪክ የደመደመው በእነዚህ ቃላት ነበር። የሚያሳዝነው “ያን ድሀ ሰው ግን ማንም አላሰበውም።”—መክብብ 9:14-16
ብዙውን ጊዜ ሰዎች ዝቅተኛ ኑሮ ያላቸውን ሰዎች የመናቅ ዝንባሌ አላቸው። የላቁ ተግባራት ቢያከናውኑ እንኳ ድሀ ስለሆኑ ብቻ ሰዎች ይንቋቸዋል። ይህ ሁኔታ በኢየሱስም ላይ የደረሰ ሲሆን ኢሳይያስ ስለ እርሱ ትንቢት ተናግሮ ነበር:- “የተናቀ ከሰውም የተጠላ፣ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው።” (ኢሳይያስ 53:3) ኢየሱስ በዘመኑ የነበሩት ታዋቂ መሪዎች የነበራቸው ዓይነት ቦታ ወይም ሀብት ስላልነበረው ብቻ አንዳንዶች ንቀውት ነበር። ሆኖም ኢየሱስ ከማንኛውም ኃጢአተኛ ሰብዓዊ ፍጡር በጣም የላቀ ጥበብ ነበረው። በኢየሱስ የትውልድ ከተማ የነበሩት ሰዎች “ይህ የጸራቢ ልጅ” እንዲህ ያለውን ጥበብ ማሳየቱንና ተአምራት ማድረጉን ፈጽሞ ለማመን አልፈለጉም። ይሁን እንጂ ይህ በጣም ከባድ ስህተት ስለነበር ታሪኩ በመቀጠል “በአለማመናቸውም ምክንያት በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም” ይላል። እነዚያ ሰዎች እንዴት ያለ ኪሳራ ደርሶባቸዋል!—ማቴዎስ 13:54-58
እኛም ተመሳሳይ ስህተት አንሥራ። ኢየሱስ “ጥበብም በልጆችዋ [“በሥራዋ፣” የ1980 ትርጉም ] ጸደቀች” ሲል ተናግሯል። የአምላክን ሥራ የሚሠሩና ሰማያዊውን ጥበብ ለሌሎች የሚያካፍሉ ሰዎች የሚታወቁት ባላቸው ክብር ወይም ኅብረተሰቡ ውስጥ ባላቸው ቦታ ሳይሆን በሚያሳዩት “መልካም ፍሬ” ማለትም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በተመሠረተው እምነታቸውና ተግባራቸው ነው።—ማቴዎስ 7:18-20፤ 11:19