በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይሖዋን የሚወዱ ሁሉ በፊቱ ውድ ናቸው

ይሖዋን የሚወዱ ሁሉ በፊቱ ውድ ናቸው

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

ይሖዋን የሚወዱ ሁሉ በፊቱ ውድ ናቸው

ከመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ጀምሮ ሊባኖስ ባሏት የተፈጥሮ ሀብቶች የታወቀች ነበረች። (መዝሙር 72:​16፤ ኢሳይያስ 60:​13) በተለይ ከውበታቸው፣ ከመዓዛቸውና ከጥንካሬያቸው የተነሳ ለግንባታ ሥራ በጣም ይፈለጉ የነበሩት ግርማ ሞገስ የተላበሱ አርዘ ሊባኖስ የተሰኙ ዛፎችዋ እጅግ የተወደዱ ነበሩ። ይሁን እንጂ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ከአርዘ ሊባኖስ ዛፍ የሚበልጥ ውድ ነገር ከሊባኖስ ተገኝቷል። የማርቆስ ወንጌል ዘገባ የሊባኖስ የቀድሞ ግዛቶች ከሆኑት ከጢሮስና ከሲዶና ‘ኢየሱስ እንዴት ትልቅ ነገር እንዳደረገ ሰምተው ብዙ ሰዎች . . . ወደ እርሱ መጡ’ በማለት ይነግረናል።​—⁠ማርቆስ 3:​8

ዛሬም በተመሳሳይ ሊባኖስ በይሖዋ ዓይን በጣም ውድ የሆኑ ፍሬዎች ማፍራቷን ቀጥላለች። የሚከተሉት ተሞክሮዎች ይህንን ያጎላሉ።

ዊሳም የተባለ አንድ ወጣት ምሥክር ለክፍሉ ተማሪዎች የ30 ደቂቃ ንግግር እንዲያቀርብ ተጠየቀ። ዊሳም ይህ ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችለው ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነ ስለተሰማው ሕይወት የተገኘው እንዴት ነው? በዝግመተ ለውጥ ወይስ በፍጥረት ? (እንግሊዝኛ) የተባለውን መጽሐፍ ተጠቅሞ ፍጥረት በሚል ርዕስ ንግግሩን አዘጋጀ። አስተማሪው ዊሳም ያዘጋጀውን ንግግር ሲመለከት ወዲያው ትምህርቱ ጠቃሚ እንደሆነ ስለተገነዘበ ንግግሩን ወደ 45 ደቂቃ ማራዘም እንደሚችል ነገረው።

ዊሳም ንግግሩን እንደጀመረ አስተማሪው አቋረጠውና ርዕሰ መምህሯን አስጠራት። ወዲያውኑ ርዕሰ መምህሯ በመምጣቷ ንግግሩን እንደገና ጀመረ። ርዕሰ መምህሯ ዊሳም በመግቢያው ላይ ያነሳቸው ጥያቄዎች ጉጉት ስላሳደሩባት ሁሉም ተማሪዎች የንግግሩን ቅጂ ማግኘት እንዳለባቸው ተናገረች።

ከጥቂት ጊዜ በኋላ አንድ ሌላ መምህር በክፍሉ አጠገብ ሲያልፍ አንድ የተለየ ነገር በመከናወን ላይ እንዳለ ስላተዋለ ምን እንደሆነ ጠየቀ። ጉዳዩ ሲነገረው ዊሳም ለማረጋገጥ እየሞከረ ያለው የፍጥረትን ትክክለኛነት ነው ወይስ የዝግመተ ለውጥን በማለት ጠየቀ። “የፍጥረትን” የሚል መልስ ተሰጠው። መምህሩ ዊሳም ከይሖዋ ምሥክሮች አንዱ መሆኑን በተረዳ ጊዜ “ንግግሩን ስታዳምጡ ሳይንስ ፍጥረትን እንጂ ዝግመተ ለውጥን እንደማይደግፍ ትረዳላችሁ” ሲል ተናገረ።

መምህሩ ቀደም ሲል የፍጥረት መጽሐፍ ቅጂ አግኝቶ የነበረ ሲሆን መጽሐፉን በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ንግግሮች ለመስጠት ሲጠቀምበት ቆይቷል! መምህሩ ክፍሉን ለቅቆ ከመሄዱ በፊት በሚቀጥለው ቀን ከራሱ ተማሪዎች ጋር ሆኖ ዊሳም የሚሰጠውን ንግግር መስማት ይችል እንደሆነ ጠየቀ። ይህም ስለ ይሖዋ ሌላ ጥሩ ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችል አጋጣሚ አስገኝቶአል።

የሀያ ሁለት ዓመቷ ኒና የእውነትን ውኃ ተጠምታ ነበር። አንድ ቀን የአክስቷ ልጅ መጽሐፍ ቅዱስ ሰጣትና ወደ ጰንጠቆስጤ ቤተ ክርስቲያን ወሰዳት። ኒና መጽሐፍ ቅዱስን በደስታ ታነብ የነበረ ሲሆን ከዚህ ንባቧም ክርስቲያኖች መስበክ እንዳለባቸው ስለተገነዘበች ለምታውቃቸው ሰዎች በሙሉ መናገር ጀመረች። ያነጋገረችው ሰው ሁሉ “የይሖዋ ምሥክር ነሽ? ” እያለ ሲጠይቃት ትገረም ነበር።

ከስድስት ዓመታት በኋላ የይሖዋ ምሥክሮች ቤቷን አንኳኩተው ስለ አምላክ መንግሥት ነገሯት። መጀመሪያ ላይ በትምህርቶቻቸው ላይ ስህተት ለማግኘት ብትሞክርም በኋላ ግን የሚሰጧት መልሶች ሁሉ ትክክልና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረቱ እንደሆኑ ተገነዘበች።

ውሎ አድሮ ኒና ይሖዋ ስለተባለው የአምላክ ስም፣ መንግሥቱ ስለሚያመጣቸው በረከቶችና እነዚህን ስለመሳሰሉ ነገሮች የቀሰመችው ትምህርት እውነትን እንዳገኘች ስላሳመናት ራሷን ለአምላክ በመወሰን ተጠመቀች። ኒና ላለፉት ሰባት ዓመታት የሙሉ ጊዜ ወንጌላዊ ሆና አገልግላለች። በእርግጥም ይሖዋ ለእርሱ እውነተኛ ፍቅር ያላቸውን ሰዎች ይባርካል።​—⁠1 ቆሮንቶስ 2:​9