በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታስታውሳለህን?

ታስታውሳለህን?

ታስታውሳለህን?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በማንበብ ተጠቅመሃልን? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ ለማስታወስ ሞክር:-

ኢሳይያስ 65:​17-19 ላይ ስለ “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር” የሚናገረው ትንቢት ፍጻሜ የአይሁዳውያንን ከምርኮ መመለስ ብቻ ሳይሆን ከዚያ የበለጠ ነገር እንደሚያመለክት እርግጠኞች መሆን የምንችለው ለምንድን ነው?

በአንደኛው መቶ ዘመን እዘአ ሐዋርያው ጴጥሮስና ዮሐንስ ሲጽፉ ገና የሚመጡ በረከቶችን የሚያካትት ወደፊት የሚያገኘውን ፍጻሜ በመጥቀሳቸው ምክንያት ነው። (2 ጴጥሮስ 3:​13፤ ራእይ 21:​1-4)​—⁠4/15 ገጽ 10-12

ኃይለኛ ስለሆኑ አምላክ አከል ሰዎች የሚነገሩት ጥንታዊ የግሪክ አፈ ታሪኮች በምን ላይ የተመሠረቱ ሊሆኑ ይችላሉ?

እነዚህ አፈ ታሪኮች ከጥፋት ውኃ በፊት አንዳንድ መላእክት የሰው አካል ለብሰው በምድር ላይ ግፍና ሥነ ምግባር የጎደለው አኗኗር ስለመከተላቸው ከሚናገረው እውነተኛ ታሪክ ተቀባብተውና ተጣምመው የቀረቡ ሊሆኑ ይችላሉ። (ዘፍጥረት 6:​1, 2)​—⁠4/15 ገጽ 27

የጎለመሱ ክርስቲያኖች በሰርግ ግብዣ ወቅት እንዳይፈጠሩ የሚከላከሏቸው አንዳንድ አደገኛ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?

የአልኮል መጠጥ እንደልብ በመቅረቡ እንዲሁም ጆሮ የሚያደነቁር ሙዚቃና ቅጥ ያጣ ጭፈራ በመኖሩ ሊፈጠር የሚችል ሁካታ የበዛበት ፈንጠዝያ ማስወገድ አስፈላጊ ነው። ሁሉም ሰው በሠርግ ግብዣው ላይ መገኘት እንደሚችል በግልጽ ካልተነገረ በስተቀር ጥሪ ያልተደረገላቸው ሰዎች መምጣት የለባቸውም። ሙሽራው ሥነ ሥርዓቱ በተገቢው ሰዓት እስኪጠናቀቅ ድረስ ኃላፊነት ያለባቸው ክርስቲያኖች በቦታው እንደሚቆዩ ማረጋገጥ አለበት።​—⁠5/1 ገጽ 19-22

መዝሙር 128:​3 ላይ በአንድ ሰው ማዕድ ዙሪያ “እንደ ወይራ ቡቃያ” ስለሆኑ ወንዶች ልጆች መጠቀሱ ምን ሐሳብ ያስተላልፋል?

አብዛኛውን ጊዜ የወይራ ዛፍ ከግንዱ ሥር አዳዲስ ችግኞችን ያበቅላል። ዋነኛው ግንድ ረጅም ዘመን በማስቆጠሩ የተነሳ እንደ ቀድሞው ፍሬ መስጠቱን በሚያቆምበት ጊዜ በዙሪያው የበቀሉት አዳዲስ ችግኞች ጠንካራ ግንዶች ሊሆኑ ይችላሉ። በተመሳሳይ ወላጆች ከጎናቸው ሆነው ይሖዋን በማገልገል ፍሬ የሚያፈሩ ልጆች በማግኘታቸው ሊደሰቱ ይችላሉ።​—⁠5/15 ገጽ 27

ልጆች ጤናማ መንፈስ በሰፈነበት ቤተሰብ ውስጥ የሚያገኟቸው አንዳንድ ጥቅሞች ምንድን ናቸው?

እንዲህ ዓይነቱ መንፈስ ለሥልጣን ጤናማ አመለካከት እንዲይዙ፣ ተገቢ ለሆኑ የሥነ ምግባር ደንቦች አድናቆት እንዲያሳዩና ከሌሎች ጋር አስደሳች ዝምድና መፍጠር እንዲችሉ መሠረት ይጥላል። እንዲሁም ከአምላክ ጋር ወዳጅነት እንዲመሠርቱም ሊረዳቸው ይችላል።​—6/1 ገጽ 18

በሩቅ ምሥራቅ በሚገኝ አንድ አገር ውስጥ ሁሉም ክርስቲያኖች ወንድማማች ናቸው የሚለውን አስተሳሰብ ለማስፈን ምን ተደርጓል?

ወንድሞች አንዳንዶችን ሲጠሩ ከፍ ተደርገው የሚታዩ ሰዎችን በሚያመለክት መጠሪያ እንዳይጠቀሙ ማሳሰቢያ ተሰጣቸው። ከዚህ ይልቅ ሁሉም ወንድሞች እንደመሆናቸው መጠን በአንድ ዓይነት ስያሜ መጠራት አለባቸው።​—⁠6/15 ገጽ 21, 22

የይሖዋ ምሥክሮች ከደም በተውጣጡ መድኃኒቶች ይጠቀማሉን?

‘ከደም ራቁ’ የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዝ ሙሉውን ደምም ሆነ ዋና ዋናዎቹን ክፍሎች (ፕላዝማ፣ ቀይና ነጭ የደም ሕዋስ እና አርጊ ሕዋሰ ደም) መውሰድን እንደሚከለክል እናምናለን። (ሥራ 15:​28, 29) ከዋና ዋናዎቹ ክፍሎች የተገኙትን የደም ክፍልፋዮች በተመለከተ ደግሞ እያንዳንዱ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚልና ከአምላክ ጋር ያለውን ዝምድና ግምት ውስጥ በማስገባት በግሉ ይወስናል።​—⁠6/15 ገጽ 29-31

በዛሬው ጊዜ ውስጣዊ ሰላም ማግኘት ይቻላልን?

አዎን፣ ይቻላል። ኢየሱስ ክርስቶስ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ሰዎችን ወደ ንጹሕ አምልኮ ጎዳና እና በኢሳይያስ 32:​18 ላይ ወደተገለጸው ሰላም እየመራቸው ነው። በተጨማሪም እንዲህ ዓይነቱን ሰላም የሚያገኙ ሰዎች መዝሙር 37:​11, 29 ፍጻሜ በሚያገኝበት ጊዜ በምድር ላይ ዘላቂ ሰላም የማግኘት ተስፋ አላቸው።​—⁠7/1 ገጽ 7

ጆርጅ ያንግ በዘመናዊው ቲኦክራሲያዊ ታሪክ ውስጥ ምን ሚና ተጫውቷል?

ከ1917 አንስቶ በበርካታ አገሮች የመንግሥቱ ምሥራች ብርሃን አብሪ ሆኖ አገልግሏል። በአገልግሎቱ አማካኝነት ድፍን ካናዳን ያዳረሰ ሲሆን በካሪቢያን ወዳሉ ደሴቶች፣ ወደ ብራዚልና ሌሎች ወደ ደቡብ አሜሪካና ወደ ማዕከላዊ አሜሪካ አገሮች፣ ወደ ስፔይን፣ ወደ ፖርቱጋል፣ ወደ ቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት እና ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተጉዟል።​— 7/1 ገጽ 22-7

አንደኛ ቆሮንቶስ 15:​29 አንዳንዶች “ስለ ሙታን የሚጠመቁ” መሆናቸውን መግለጹ ምን ትርጉም ይዟል?

የጥቅሱ ሐሳብ ክርስቲያኖች በመንፈስ ቅዱስ ሲቀቡ ወደ ሞት ከዚያም ለሰማያዊ ሕይወት ትንሣኤ ወደሚያገኙበት የሕይወት ጎዳና መጥለቃቸውን ያመለክታል።​—⁠7/15 ገጽ 17

ሐዋርያው ጳውሎስ ደብዛው ጠፍቷል በሚባልባቸው ዓመታት ውስጥ ምን ሲያደርግ ነበር?

በሶርያና በኪልቅያ ጉባኤዎችን ለማቋቋም ወይም ለማጠናከር ድጋፍ ሰጥቶ ሊሆን ይችላል። በ⁠2 ቆሮንቶስ 11:​23-27 ላይ የተጠቀሱት አብዛኞቹ መከራዎች የደረሱበት በዚህ ወቅት መሆን አለበት። ይህም በአገልግሎቱ በንቃት ይሳተፍ እንደነበር ያሳያል።​—⁠7/15 ገጽ 26, 27

ከራሳችን በምንጠብቀው ነገር ምክንያታዊ እንድንሆን ምን ሊረዳን ይችላል?

ይሖዋ የሰውን ሁኔታ የሚረዳ መሆኑን አስታውሱ። ወደ እሱ መጸለያችን ሚዛናዊ አስተሳሰብ እንድንይዝ የሚረዳን ሲሆን ልካችንን የምናውቅ መሆናችንንም ያሳያል። ሌላው ሊረዳን የሚችለው ነገር ደግሞ አንድ የጎለመሰ ጓደኛችንን በማነጋገር አዲስ አመለካከት መያዝ ነው።​—⁠8/1 ገጽ 29, 30