በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዝምታ እንደ መስማማት ሲቆጠር

ዝምታ እንደ መስማማት ሲቆጠር

ዝምታ እንደ መስማማት ሲቆጠር

ሃይማኖት በናዚ ፖለቲካ ውስጥ የተጫወተውን ሚና ቢትሬያል​—⁠ጀርመን ቸርችስ ኤንድ ዘ ሆሎኮስት የተባለው መጽሐፍ በግልጽ ያብራራል። “ክርስቲያኖች አገዛዙን ይደግፉ የነበረ ከመሆኑም በላይ አብዛኞቹ በአይሁዳውያን ላይ ስደት ሲደርስ ምንም ዓይነት የተቃውሞ ድምፅ አላሰሙም። በዚህ ሁኔታ ላይ የታየው ዝምታ በጉዳዩ መስማማትን በቃል ከመግለጽ አይተናነስም” ሲል መጽሐፉ ይገልጻል።

ክርስቲያን ነን ባዮች የናዚን አገዛዝ እንዲደግፉ ያደረጋቸው ምን ነበር? መጽሐፉ እንደሚለው አብዛኞቹ ሂትለር “ለጀርመን ሕዝብ ባወጣው ሕግና ሥርዓት ተስበው ነበር።” መጽሐፉ እንዲህ ሲል ይገልጻል:- “ሂትለር ወሲባዊ ሥዕሎችንና ጽሑፎችን፣ ዝሙት አዳሪነትን፣ ውርጃን፣ ግብረ ሰዶምን እንዲሁም በዘመናዊው ሥነ ጥበብ ላይ የሚንጸባረቀውን ‘ወራዳ ምግባር’ ከመቃወሙም በላይ ሴቶች ቤት ውስጥ የመሥራት ባሕላቸውን ጠብቀው እንዲቆዩ ለማበረታታት ሲል አራት፣ ስድስትና ስምንት ልጆች ለወለዱት ሴቶች የነሐስ፣ የብርና የወርቅ ሜዳሊያ ይሸልም ነበር። ሂትለር ለባሕላዊ እሴቶች ከፍተኛ ዋጋ በመስጠቱና የጀርመንን ብሔራዊ ክብር ዝቅ እንደሚያደርግ ተደርጎ ለተወሰደው የቨርሳይ ውል ምላሽ በመስጠት በወታደራዊ ኃይል ብሔራዊ የበላይነትን የማስጠበቅ መርህ በመከተሉ የናዚ አገዛዝ አብዛኞቹን ሰዎች አልፎ ተርፎም ብዙዎቹን ጀርመናውያን ክርስቲያኖች ሊስብ ችሏል።”

ሆኖም አንድ ቡድን የተለየ አቋም ነበረው። ቢትሬያል የተሰኘው መጽሐፍ “የይሖዋ ምሥክሮች በጦርነት ለመካፈልም ሆነ የጦር ኃይል ለመጠቀም እምቢ ብለው ነበር” በማለት አብራርቷል። እንዲህ ያለው አቋም የናዚ መንግሥት በዚህ አነስተኛ ቡድን ላይ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት እንዲያደርስ መገፋፋቱ አልቀረም። ብዙዎቹ የዚህ ቡድን አባላት ወደ ማጎሪያ ካምፖች የተጣሉ ሲሆን የኢየሱስ ተከታዮች ነን ይሉ የነበሩት ሌሎቹ ክርስቲያኖች ግን ምንም ዓይነት የተቃውሞ ድምፅ አላሰሙም። መጽሐፉ በማከል “ካቶሊኮችና ኘሮቴስታንቶች በአጠቃላይ ለይሖዋ ምሥክሮች ከማዘን ይልቅ ጥላቻ አሳይተዋል እንዲሁም የምሥክሮቹን ፀረ ጦርነት አቋም ከመደገፍ ይልቅ የሂትለርን የጭካኔ መርህ ደግፈዋል” ሲል ተናግሯል። ይህ ዝምታቸው ያለጥርጥር ምሥክሮቹ በናዚ አገዛዝ ግፍ እንዲፈጸምባቸው የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል።

ቤተ ክርስቲያን በናዚ ፖለቲካ ውስጥ የነበራት ተሳትፎ ከፍተኛ የመከራከሪያ ነጥብ ሆኖ ቢቀጥልም ቢትሬያል የይሖዋ ምሥክሮችን “መንግሥቱን ለመደገፍም ሆነ ከእርሱ ጋር ለመተባበር አሻፈረኝ ያለ ሃይማኖታዊ ቡድን” በማለት ጠርቷቸዋል።