በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ልባም ነህን?

ልባም ነህን?

ልባም ነህን?

ሙሴ በእስራኤል ላይ አለቆች በሚሾምበት ወቅት “ጥበበኞች፣ አስተዋዮችም [“ልባም፣” NW ] አዋቂዎችም” የሆኑ ሰዎች ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት አድርጓል። (ዘዳግም 1:​13) ከዕድሜ ጋር አብሮ የሚመጣው ልምድ ዋነኛው መመዘኛ አልነበረም። ጥበብና ማስተዋልም ያስፈልግ ነበር።

ልባም ሰው በንግግሩና በጠባዩ ጥሩ የማመዛዘን ችሎታ እንዳለው ያሳያል። በተጨማሪም ዌብስተርስ ናይንዝ ኒው ኮሊጂየት ዲክሽነሪ እንደሚለው ልባም ሰው “በብልህነት ዝምታን የሚመርጥ” ሰው ነው። አዎን፣ “ዝም ለማለት ጊዜ አለው፣ ለመናገርም ጊዜ አለው።” ልባም ሰው ደግሞ በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት ይገነዘባል። (መክብብ 3:​7) መጽሐፍ ቅዱስ “በቃል ብዛት ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው” ብሎ ስለሚናገር ብዙውን ጊዜ ዝም ለማለት የሚያበቃ ጥሩ ምክንያት አለ።​—⁠ምሳሌ 10:​19

ክርስቲያኖች እርስ በርስ ባላቸው ግንኙነት ረገድ ልባሞች ለመሆን ይጥራሉ። ብዙውን ጊዜ እርሱ ተናጋሪ የሆነ ወይም በአነጋገሩ ተጽእኖ የሚያሳድር ሰው ሁልጊዜ የላቀ ቦታ ይሰጠዋል ወይም በጣም አስፈላጊ ሰው ነው ማለት አይደለም። ሙሴ ‘በቃሉ የበረታ’ ቢሆንም እንኳ ትዕግሥት፣ ትህትናና ራስን መግዛት እስኪያዳብር ድረስ እስራኤላውያንን ውጤታማ በሆነ መንገድ መምራት እንዳልቻለ አስታውስ። (ሥራ 7:​22) ስለዚህ በተለይ በሌሎች ላይ ሥልጣን ያላቸው ሁሉ ልክን የማወቅና የእሺ ባይነትን መንፈስ ለማሳየት መጣር አለባቸው።​—⁠ምሳሌ 11:​2 NW 

ኢየሱስ “ባለው ሁሉ ላይ” የሾመው ቡድን በአምላክ ቃል ውስጥ “ታማኝና ልባም ” ተብሎ ተገልጿል። (ማቴዎስ 24:​45-47፣ በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።) ቦታቸውን በመዘንጋት በስሜታዊነት ከይሖዋ ቀድመው መሄድ አይፈልጉም ወይም ደግሞ አምላክ ስለ አንድ ነገር ያለው አመለካከት ግልጽ በሚሆንበት ጊዜ እርምጃ ከመውሰድ ወደ ኋላ አይሉም። መቼ መናገር እንዳለባቸውና መቼ ደግሞ ተጨማሪ ማብራሪያ በትዕግሥት መጠበቅ እንዳለባቸው ያውቃሉ። ሁሉም ክርስቲያኖች የባሪያውን ክፍል እምነት መኮረጅ ብቻ ሳይሆን እንደ እርሱ ልባም መሆናቸውን ለማሳየት መጣራቸው የተገባ ነው።​—⁠ዕብራውያን 13:​7