በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“በአርአያነት የሚጠቀስ አንድነት”

“በአርአያነት የሚጠቀስ አንድነት”

“በአርአያነት የሚጠቀስ አንድነት”

በብራዚል ሳኦ ፖሎ በኢንዲያቱብ የሚታተም አንድ ጋዜጣ ከላይ ያለውን ርዕሰ አንቀጽ ይዞ ወጥቶ ነበር። ለመሆኑ በአርአያነት የሚጠቀሱት እነማን ናቸው? የርዕሰ አንቀጹ አዘጋጅ “አዲስ ‘የመንግሥት አዳራሽ’ (መቅደሶቻቸውን ወይም መሰብሰቢያዎቻቸውን እንደዚያ ብለው ይጠሯቸዋል) በመገንባት ላይ ያሉት የይሖዋ ምሥክሮች የሚያሳዩት ግሩምና ሕያው የትብብር አርአያነት ትኩረት የሚስብ ነው” ሲል ጽፏል።

በይሖዋ ምሥክሮች መካከል ያለው አንድነት እንደዚህ ባለው አጋጣሚ በግልጽ ይታያል። ስለዚህም ጽሑፉ “ወንዶች፣ ሴቶች፣ እንዲሁም በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ ወጣቶች አንድ ላይ ተሰባስበው አምላክን የሚያመልኩበትን አዳራሽ ለመገንባት በፈቃደኝነት ሲሠሩ ማየት እጅግ የሚማርክ ነው” ሲል ጠቅሷል።

የይሖዋ ምሥክሮች በሌሎች ዘርፎችም ጥሩ አርአያ ናቸው። ርዕሰ አንቀጹ ሐሳቡን ሲቀጥል “ከማጥናትና ከመጸለይ በተጨማሪ የአልኮልና የዕፅ ሱሰኛ የሆኑ ሰዎች ከሱሳቸው እንዲላቀቁ መርዳትም አንዱ ግባቸው ሲሆን አንድነትና ፍቅር የሚሰፍንበትን መንገድ ለሌሎች ያስተምራሉ” ብሏል። ይህን ከግብ የሚያደርሱት እንዴት ነው? የይሖዋ ምሥክሮች የመጽሐፍ ቅዱስን ምክሮች መማርና ተግባራዊ ማድረግ አንድን ሰው ከመጥፎ ሱስ እንዲላቀቅ እንደሚረዳው ያውቃሉ። ከመጽሐፍ ቅዱስ የተማሩትን ለሌሎች ለማስተማር የሚጥሩት ለዚህ ነው። ርዕሰ አንቀጹ ሲያጠቃልል “ያለ ጥርጥር ዛሬ ነገ ሳይባል ሊኮረጅ የሚገባው አርአያነት” ነው ብሏል።

ማንኛውም ሰው የይሖዋ ምሥክሮች በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች ላይ መገኘት የሚችል ሲሆን ገንዘብ አይሰበሰብም። በአቅራቢያህ ባለ የመንግሥት አዳራሽ እንድትገኝ ከልብ ተጋብዘሃል።