በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዓለም አቀፍ ሰላም እንዴት ይገኛል?

ዓለም አቀፍ ሰላም እንዴት ይገኛል?

ዓለም አቀፍ ሰላም እንዴት ይገኛል?

ዓለም አቀፍ ሰላም ከአድማስ እየታየ ነውን? ብዙዎች በአንድ ወቅት እንደዚያ ብለው አስበው ነበር፤ ሆኖም አሁን ጥርጣሬ ገብቷቸዋል። በደቡብ አፍሪካው ዴይሊ ሜይል ኤንድ ጋርዲያን ላይ የወጣ አንድ ሪፖርት ወደፊት ስለሚገጥሙን አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲዘግብ “አዲስ ዓለም አቀፍ ሥርዓት እንደሚመጣ ከ10 ዓመት በፊት የተነገሩት ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን እንደሚያገኙ የሚጠቁም ጭላንጭል እንኳን አይታይም” ብሏል።

አዘጋጆቹ ትኩረት ያደረጉት ከአሥርተ ዓመት በፊት ሰፍኖ በነበረው ተስፋ ላይ ነው። ቀዝቃዛው ጦርነት ገና ማብቃቱ ነበር፤ እንዲሁም የጦር መሣሪያ የበላይነት ለማግኘት የሚደረገው እሽቅድምድም አክትሞ ነበር። ብዙዎች አዲስ ዘመን የጠባ መስሏቸው ስለነበር የሰው ልጅ ድህነትን፣ በሽታንና አካባቢያዊ ችግሮችን በመዋጋት ረገድ አንድ እመርታ ያሳያል ብለው ጠብቀው ነበር። ዘገባው “አሁን እነዚያ ትንበያዎች እንዲያው ምናባዊ ሆነው ቀርተዋል። ጨርሶ ባልተጠበቁ ቦታዎች አዳዲስ ግጭቶች እየተቀሰቀሱ ነው፤ ድህነት ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ ነው። ሁለት አዳዲስ የኑክሌር ባለቤት አገሮች ተጨምረዋል። የተባበሩት መንግሥታት በሰው ዘር ላይ በተከታታይ የደረሰውን ቀውስ የማስወገድ አቅም በማጣቱ ዝናው ጎድፏል። እንዲያውም አሁን አስፈሪ ሁኔታዎች እያንዣበቡ ነው።”

የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የሰው ጥረቶች ምንም ያህል ጥሩ ቢሆኑ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ መሆን እንደማይችሉ ይገነዘባሉ። ለምን? ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ‘ዓለም በሞላው በክፉው ተይዟል።’ (1 ዮሐንስ 5:​19) ዓለም በሰይጣን ቁጥጥር ሥር እያለ አምላክ ፈጥሮት ወደነበረው ገነታዊ ሁኔታ እንዲመለስ ማድረግ አይቻልም።

ይሁን እንጂ ብሩህ አመለካከት ለመያዝ የሚያስችል በቂ ምክንያት አለ። ይሖዋ አምላክ በዓለም ላይ ሰላም እንደሚያሰፍን ቃል ገብቷል። ቃሉን የሚፈጽመው ይህን የነገሮች ሥርዓት እንደ አሮጌ ልብስ በመጣፍና በመጠገን ሳይሆን “ጽድቅ የሚኖርባትን . . . አዲስ ምድር” በማምጣት ነው። (2 ጴጥሮስ 3:​13) አዎን፣ በአምላክ መንግሥት አማካኝነት ምድራችን ወደ ሰላማዊና ደስተኛ መኖሪያነት ትለወጣለች። ሕይወትና ሥራ ታዛዥ ለሆነው መላው የሰው ዘር ዘላቂ የደስታ ምንጭ ይሆንለታል። ከዚህም በላይ አም​ላክ ‘እንባዎችን ሁሉ ከዓይኖቻቸው እንደሚያብስ፣ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ እንደማይኖር፣ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ እንደማይሆን’ ቃል ገብቷል። እነዚህ ተስፋዎች ምንም መሠረት እንደሌላቸው ሰብዓዊ ትንበያዎች አይደሉም። ከዚህ ይልቅ ሊዋሽ የማይችለው ፈጣሪ የተናገራቸው መሬት ጠብ የማይሉ ቃላት ናቸው።​—⁠ራእይ 21:​4፤ ቲቶ 1:​2