በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሃይማኖታዊ ውህደት የሚፈጠርበት ጊዜ ቀርቧልን?

ሃይማኖታዊ ውህደት የሚፈጠርበት ጊዜ ቀርቧልን?

ሃይማኖታዊ ውህደት የሚፈጠርበት ጊዜ ቀርቧልን?

የሉተራን ዓለም አቀፍ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የሆኑት ክሪስቲያን ክራዉስ “በአብያተ ክርስቲያኖቻችን ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠውን ቀን የማየት አጋጣሚ አግኝተናል” በማለት ተናግረዋል። በተመሳሳይም ሊቀ ጳጳስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ “በክርስቲያኖች መካከል የተሟላ ውህደት ለመፍጠር በሚደረገው አስቸጋሪ ጉዞ ላይ አዲስ ምዕራፍ ከፋች እርምጃ” ሲሉ ተደምጠዋል።

እንዲህ ብለው በስሜት እንዲናገሩ ያነሳሳቸው ስለ መጽደቅ የሚናገረውን መሠረተ ትምህርት አስመልክቶ የወጣውን የጋራ ድንጋጌ ለማጽደቅ ጥቅምት 31, 1999 በጀርመን ኦውግስበርግ የተፈረመው ኦፊሴላዊ የጋራ ስምምነት ነው። ስምምነቱ የተፈረመበት ጊዜና ቦታ በሚገባ የታሰበበት ነበር። ማርቲን ሉተር የፕሮቴስታንት ተሐድሶ ንቅናቄን ለመጀመር 95 የተቃውሞ ሐሳቦችን ዊተንበርግ በሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ግንብ ላይ የለጠፈው ጥቅምት 31, 1517 እንደሆነ ይነገራል። ኦውግስበርግ ደግሞ የሉተራን እምነት ተከታዮች በ1530 ካቶሊክ አጥብቃ የተቃወመችውንና በፕሮቴስታንቶችና በካቶሊኮች መካከል ለተፈጠረው የማይታረቅ ቅራኔ ምክንያት የሆነውን የኦውግስበርግ የእምነት ቃል የሚባል መግለጫ ያጸደቁበት ቦታ ነው።

ይህ የጋራ መግለጫ እንደተባለው ሁሉ በአብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን መከፋፈል የሚያስወግድ ወሳኝ እርምጃ ይሆን? ብሩህ አመለካከት ያላቸው ሁሉም ወገኖች አይደሉም። ከ250 የሚበልጡ የፕሮቴስታንት ሃይማኖታዊ ምሁራን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በቁጥጥሯ ሥር እንደምታደርጋቸው የሚያስጠነቅቅ የተቃውሞ ማመልከቻ አስገብተዋል። በተጨማሪም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በ2000 ኃጢአትን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ይቅር የማለት ልዩ ሥርዓት ማወጅዋ ፕሮቴስታንቶችን አስቆጥቷል። ይህ ጉዳይ ደግሞ ከ500 ዓመታት በፊት ለሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መቃቃር ምክንያት ነበር። የትሬንት ጉባኤ ያጸደቀው የኦውግስበርግ የእምነት ቃል የሚባለው መግለጫም ሆነ የካቶሊክ ተቃውሞ አሁንም ለውጥ ስላልታየበት ውህደቱ እውን ሊሆን አይችልም።

በሕዝበ ክርስትና አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለው ልዩነትና አለመግባባት የጋራ ስምምነት በመፈረም የሚስተካከል አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ የእምነት ውህደት የሚገኘው የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በጥብቅ በማመን ነው። (ኤፌሶን 4:​3-6) እውነተኛ ውህደት እውን ሊሆን የሚችለው አምላክ ከእኛ የሚፈልግብንን በመማርና የተማርነውን ተግባራዊ በማድረግ እንጂ ከሌሎች ጋር ለመመሳሰል ሲባል አቋምን በማላላት አይደለም። ታማኝ የነበረው ነቢዩ ሚክያስ “ሕዝብም ሁሉ እያንዳንዱ በየአምላኩ ስም ይሄዳል፣ እኛም በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ለዘላለም እንሄዳለን” ሲል አውጆአል።​—⁠ሚክያስ 4:​5