በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በጎነትን ማዳበር ያለብን ለምንድን ነው?

በጎነትን ማዳበር ያለብን ለምንድን ነው?

በጎነትን ማዳበር ያለብን ለምንድን ነው?

ኩኑሂቶ የተባለ በመካከለኛ ዕድሜ ላይ የሚገኝ አንድ ጃፓናዊ በቅርቡ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተጓዘ። a እዚያ ከደረሰ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ሥራውን ሊያሳጣው የሚችል አንድ ሁኔታ ገጠመው። ኩኒሂቶ እንዲህ ሲል ገልጿል:- “አለቃዬ በአንድ የኃላፊነት ቦታ ላይ መሥራት እችል እንደሆነ ሲጠይቀኝ ኃላፊነቱን ተቀብዬ መሥራት እንደምችል እርግጠኛ ሆኜ ነበር። ሆኖም ባደግኩበት ባሕል ልከኝነት እንደ በጎ ምግባር የሚቆጠር በመሆኑ ‘እችለዋለሁ ብለህ ነው፤ ለማንኛውም የተቻለኝን ሁሉ ለማድረግ እሞክራለሁ’ ብዬ መለስኩለት። በዚህ ጊዜ አሜሪካዊው አለቃዬ ብቁ እንዳልሆንኩና በራስ የመተማመን መንፈስ እንደሚጎድለኝ ሆኖ ተሰማው። እንዲህ እንደተሰማው ሳውቅ አንዳንድ ማስተካከያዎች ማድረግ እንዳለብኝ ተገነዘብኩ።”

በኒው ዮርክ ሲቲ የምትኖረው ማሪያ ጎበዝ ተማሪ ስትሆን ምንጊዜም የክፍል ጓደኞቿን መርዳት ያስደስታታል። ሁዋን ማሪያ ከምትረዳቸው ተማሪዎች መካከል አንዱ ነበር። ሆኖም ከማሪያ ጋር ፍቅር ስለያዘው ስሜቷን ለመማረክ ይጥር ነበር። ማሪያ የሥነ ምግባር ንጽሕናዋን ጠብቃ ለመኖር ትፈልግ የነበረ ቢሆንም እንኳ ሁዋን ላቀረበላት ጥያቄ በመሸነፍ የጾታ ብልግና ፈጸመች።

የተለያዩ ባሕሎች ባሉበትና በሥነ ምግባር በተበላሸው በዚህ ዓለም ውስጥ በጎ ምግባር ይዞ መመላለስ በእርግጥም ፈታኝ ነው። ታዲያ በጎነትን ማዳበር ያስፈለገው ለምንድን ነው? በጎ ምግባር አምላክን ደስ የሚያሰኝ በመሆኑ ነው። አብዛኞቻችን ደግሞ የአምላክን ሞገስ ማግኘት እንደምንፈልግ የታወቀ ነው።

የአምላክ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢዎቹ በጎነትን እንዲያዳብሩ አጥብቆ ያሳስባል። ለምሳሌ ያህል ሐዋርያው ጳውሎስ “በጎነት ቢሆን ምስጋናም ቢሆን፣ እነዚህን አስቡ” ሲል ጽፏል። (ፊልጵስዩስ 4:​8) በተጨማሪም ሐዋርያው ጴጥሮስ ‘በእምነታችን ላይ በጎነትን ለመጨመር መትጋት’ እንዳለብን አጥብቆ ይመክረናል። (2 ጴጥሮስ 1:​5) ይሁን እንጂ በጎነት ምንድን ነው? በክፍል ውስጥ ልንማረው የምንችለው ነገር ነውን? ልናዳብረው የምንችለውስ እንዴት ነው?

[የግርጌ ማስታወሻ]

a አንዳንዶቹ ስሞች ተቀይረዋል።