በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ለእምብርትህ ፈውስ ይሆንልሃል”

“ለእምብርትህ ፈውስ ይሆንልሃል”

“ለእምብርትህ ፈውስ ይሆንልሃል”

የሰውን ዘር የሚያጠቁ አብዛኞቹ በሽታዎች እንደ ፍርሃት፣ ሐዘን፣ ቅናት፣ ብስጭት፣ ጥላቻና የጥፋተኝነት ስሜት ከመሳሰሉ ስሜታዊ ውጥረቶች እንደሚመነጩ ይታመናል። ከዚህ አንፃር ‘ይሖዋን መፍራት’ “ለሥጋህ [“ለእምብርትህ፣” NW ] ፈውስ ለአጥንትህም ጠገን” ነው የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ አነጋገር ምንኛ ያጽናናል!​—⁠ምሳሌ 3:​7, 8

አጥንት የሰውነት ምሰሶ ነው። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ አንድን ሰው በተለይም ጥልቅ በሆኑ ስሜቶች የሚነካውን የአንድን ሰው ውስጣዊ ማንነት ለማመልከት “አጥንት” የሚለውን ቃል በምሳሌያዊ አነጋገር ይጠቀምበታል። ሆኖም ይሖዋን መፍራት “ለእምብርትህ ፈውስ” የሚሆነው እንዴት ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን እዚህ ላይ “እምብርት” ተብሎ ስለተጠቀሰው ቃል ያላቸው አመለካከት የተለያየ ነው። አንድ ተንታኝ “እምብርት” “በሰውነት ማእከላዊ” ቦታ ስለሚገኝ በጣም አስፈላጊ የሰውነት አካላትን በሙሉ ሊወክል ይችላል ብለዋል። ሌላው ምሁር ደግሞ “እምብርት” የሚለው ቃል በ⁠ሕዝቅኤል 16:​4 ላይ እንደተሠራበት እትብት ማለት ሊሆን ይችላል የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል። እንደዚያ ከሆነ ምሳሌ 3:​8 ራሱን መመገብ የማይችል ፅንስ ሙሉ በሙሉ የእናቱ ጥገኛ እንደሆነው ሁሉ እኛም የአምላክ ጥገኞች እንደሆንን የሚያስገነዝብ ሊሆን ይችላል። ሌላው አመለካከት ደግሞ “እምብርት” የሰውነትን ጡንቻዎችና ጅማቶች ሊያመለክት ይችላል የሚል ነው። በዚህ ጥቅስ ላይ እነዚህ የሰውነት አካላት ጠንካራ ከሆነው የአካል ክፍል ይኸውም “ከአጥንት” ጋር ተወዳድረዋል።

ትክክለኛ ትርጉሙ ምንም ይሁን ምን አንድ ነገር እሙን ነው። ይሖዋን ላለማሳዘን መፍራት የጥበብ መንገድ ነው። ከአምላክ የአቋም ደረጃዎች ጋር ተስማምቶ መኖር አሁንም ቢሆን በአካል ጤነኞች እንድንሆን ሊረዳን ይችላል። ከዚህም በላይ የይሖዋን ሞገስ ያስገኝልናል። ይህ ደግሞ ይሖዋ በቅርቡ በሚያመጣው አዲስ ዓለም ውስጥ በአካልም በስሜትም ፍጹም ጤንነት ወደምናገኝበት ፍጻሜ ወደሌለው ሕይወት ይመራናል።​—⁠ኢሳይያስ 33:​24፤ ራእይ 21:​4፤ 22:​2

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

Dr. G. Moscoso/SPL/Photo Researchers