የሙት ባሕር ጥቅልሎች ትኩረትህን ሊስቡት የሚገባው ለምንድን ነው?
የሙት ባሕር ጥቅልሎች ትኩረትህን ሊስቡት የሚገባው ለምንድን ነው?
የሙት ባሕር ጥቅልሎች እስከተገኙበት ጊዜ ድረስ ጥንታዊ ናቸው የሚባሉት የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ቅጂዎች በዘጠነኛውና በአሥረኛው መቶ ዘመን እዘአ ገደማ የተዘጋጁት ነበሩ። የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ተጽፈው ያለቁት እነዚህ ቅጂዎች ከመዘጋጀታቸው አንድ ሺህ ከሚበልጡ ዓመታት በፊት ስለሆነ እነዚህ ቅጂዎች የአምላክን ቃል በትክክል ያስተላልፋሉ ብለን እምነት ልንጥልባቸው እንችላለን? የዓለም አቀፉ የሙት ባሕር ጥቅልሎች አዘጋጅ ቡድን አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ሁልዮ ትሬቦዬ ባሬራ እንደሚከተለው ብለዋል:- “[በኩምራን] የተገኘው የኢሳይያስ ጥቅልል ቅዱስ ጽሑፉ ከአንድ ሺህ ለሚበልጡ ዓመታት በአይሁድ ገልባጮች አማካኝነት በከፍተኛ ጥንቃቄ በቀጥታ ሲገለበጥ መቆየቱን የሚያሳይ ጠንካራ ማስረጃ ነው።”
ባሬራ እዚህ ላይ የጠቀሱት ጥቅልል ሙሉውን የኢሳይያስ መጽሐፍ ይዟል። ከአስቴር መጽሐፍ በስተቀር የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች የእያንዳንዱ መጽሐፍ የተወሰነ ክፍል በኩምራን በተገኙት ከ200 በላይ በሚሆኑ ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ውስጥ ይገኛል። ከኢሳይያስ ጥቅልል በስተቀር አብዛኞቹ መጻሕፍት ከእያንዳንዱ መጽሐፍ አንድ አሥረኛውን የያዘ ቁርጥራጭ ብቻ ነው የተገኘው። በኩምራን ከተገኙት የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት መካከል ይበልጥ የታወቁት መዝሙር (36 ቅጂዎች)፣ ዘዳግም (29 ቅጂዎች) እና ኢሳይያስ (21 ቅጂዎች) ናቸው። በግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚጠቀሱት መጻሕፍት ደግሞ እነዚህ ናቸው።
ጥቅልሎቹ ምንም እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መሠረታዊ የሆነ ለውጥ አለመደረጉን ቢያስረዱም በሁለተኛው ቤተ መቅደስ ዘመን ይኖሩ የነበሩ አይሁዶች የሚጠቀሙባቸው እርስ በርሳቸው ልዩነት ያላቸው የተለያዩ የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች እንደነበሩም ይጠቁማሉ። በሥርዓተ ሆህያት ወይም በቃላት ከማሶራዊው ጽሑፍ ጋር ፍጹም ተመሳሳይ የሆኑት ሁሉም ጥቅልሎች አይደሉም። አንዳንዶቹ ለግሪክኛው የሰፕቱጀንት ትርጉም ይበልጥ ይቀርባሉ። ቀደም ሲል ምሁራን በግሪክኛው የሰፕቱጀንት ትርጉም ውስጥ ያሉት ልዩነቶች በስህተት የተፈጠሩ ወይም ደግሞ ሆን ተብለው በተርጓሚው የተጨመሩ ሐሳቦች ናቸው ብለው አስበው ነበር። አሁን ግን አብዛኞቹ እነዚህ ልዩነቶች በራሱ በዕብራይስጡ ጽሑፍ መካከል ባሉት ልዩነቶች ሳቢያ የተፈጠሩ መሆናቸው ከጥቅልሎቹ መረዳት ተችሏል። በአንዳንድ ወቅቶች ልዩነት የሚፈጠረው የጥንት ክርስቲያኖች አንዳንድ ጊዜ ከማሶራዊ ጽሑፍ የተለየ አቀማመጥ ካላቸው ከዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ይጠቅሱ ስለነበረ ሊሆን ይችላል።—ዘጸአት 1:5፤ ሥራ 7:14
እነዚህ ውድ ቅርስ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅልሎችና ቁርጥራጮች የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች የተላለፉበትን መንገድ ለማጥናት ግሩም መሠረት ይሆናሉ። የሰፕቱጀንት ትርጉምና የሳምራውያኑ የፔንታቱች ቅጂ ጥቅሶችን በማነጻጸር ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው መሆናቸውን የሙት ባሕር ጥቅልሎች አረጋግጠዋል። የሙት ባሕር ጥቅልሎች በማሶራዊ ጽሑፍ ውስጥ ያሉትን ጥቅሶች ማሻሻል የሚቻልበትን መንገድ ለማጤን የሚረዳ ተጨማሪ መረጃ ይሰጣሉ። የሙት ባሕር ጥቅልሎች የአዲሲቱ ዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ኮሚቴ የይሖዋ ስም ከማሶራዊው ጽሑፍ ውስጥ ወጥቶ በነበረባቸው ቦታዎች መልሶ ለመክተት ያደረገውን ውሳኔ የሚያጠናክሩ ናቸው።
በኩምራን የነበረው ሃይማኖታዊ ቡድን ይመራባቸው ስለነበሩ ደንቦችና እምነቶች የሚገልጹት ጥቅልሎች በኢየሱስ ኢሳይያስ 40:3 ላይ የሚገኘው በምድረ በዳ ለይሖዋ መንገድ ስለመጥረግ የሚናገረው ጥቅስ በእነሱ ላይ እየተፈጸመ እንዳለ በተሳሳተ መንገድ ተረድተው ነበር። በርካታ ቁርጥራጮች የጥቅልሎቹ ጸሐፊዎች መምጫው በደጅ እንደቀረበ አድርገው ይመለከቱት ስለነበረው መሲህ ይጠቅሳሉ። ሉቃስ ‘ሕዝቡም የመሲሁን መምጣት ሲጠባበቁ ሳለ’ በማለት ከሰጠው አስተያየት አንጻር ይህ ትኩረት የሚስብ ነው።—ሉቃስ 3:15
ዘመን የነበረው የአይሁድ እምነት አንድ ብቻ እንዳልነበር ግልጽ የሚያደርጉ ናቸው። በኩምራን የነበረው ሃይማኖታዊ ቡድን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን የተለየ ሃይማኖታዊ ወግ ነበረው። ሃይማኖታዊ ቡድኑን ወደ ምድረ በዳ እንዲሰደድ ያደረገው ይህ ሳይሆን አይቀርም። በየሙት ባሕር ጥቅልሎች ኢየሱስ በሰበከበት ዘመን የአይሁድ አኗኗር ምን ይመስል እንደነበረ በተወሰነ ደረጃ እንድንረዳ ያግዙናል። የጥንቱን ዕብራይስጥና መጽሐፍ ቅዱስን እያወዳደሩ ለማጥናት ያስችላሉ። ሆኖም አብዛኞቹ የሙት ባሕር ጥቅልሎች መጻሕፍት አሁንም የበለጠ ጥናት ሊደረግባቸው ያስፈልጋል። ስለሆነም አዲስ ማስተዋል ገና ሊገኝ ይችላል። አዎን፣ የ20ኛው መቶ ዘመን ታላቅ የአርኪኦሎጂ ግኝት በያዝነው በ21ኛው መቶ ዘመን ምሁራንንም ሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች እንዲደሰቱ ማድረጉን ይቀጥላል።
[በገጽ 7 ላይ የሚገኝ ሥዕል ምንጭ]
በኩምራን የተደረገ ቁፋሮ:- Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.; በእጅ የተገለበጠ ጥንታዊ ጽሑፍ:- Courtesy of Shrine of the Book, Israel Museum, Jerusalem