በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአንባብያን ጥያቄዎች

የአንባብያን ጥያቄዎች

የአንባብያን ጥያቄዎች

ለሽያጭ የሚውሉ የኮምፒውተር ፕሮግራሞችን ለሌሎች የማስተላለፍን ልማድ በተመለከተ እውነተኛ ክርስቲያኖች ሊኖራቸው የሚገባው አመለካከት ምንድን ነው?

አንዳንዶች “በከንቱ ተቀበላችሁ፣ በከንቱ ስጡ” የሚሉትን የኢየሱስ ቃላት አላግባብ በመጥቀስ ይህ ዓይነቱ ልማድ ስህተት እንዳልሆነ ለማስረዳት ይሞክሩ ይሆናል። ኢየሱስ ይናገር የነበረው የባለቤትነት መብታቸው የተጠበቀ የጽሑፍ ሥራዎችን ወይም የኮምፒውተር ፕሮግራሞችን ቅጂ በነፃ ለሌሎች አሳልፎ ስለመስጠት አልነበረም። የእነዚህን ነገሮች አጠቃቀም በተመለከተ በሕግ የተደነገገ ነገር ይኖራል። ኢየሱስ ስለመስጠት የተናገረው ከአገልግሎት ጋር በተያያዘ መንገድ ነው። ኢየሱስ ስለ አምላክ መንግሥት ለመስበክ ወደ ተለያዩ ከተሞችና መንደሮች ሊሄዱ የተዘጋጁት ሐዋርያቱ የታመሙትን እንዲፈውሱና አጋንንትን እንዲያወጡ ነግሯቸዋል። ሐዋርያቱ ይህንን ‘በነፃ ሊሰጡ’ እንጂ ክፍያ ሊጠይቁ አይገባም ነበር።​—⁠ማቴዎስ 10:​7, 8

በግልም ሆነ በድርጅት መልክ የኮምፒውተር ተጠቃሚዎች ቁጥር በመብዛቱ የኮምፒውተር ፕሮግራም ፈላጊዎች ቁጥር ጨምሯል። ብዙውን ጊዜ እነዚህ ፕሮግራሞች የሚገኙት በግዥ ነው። እርግጥ አንዳንድ ሰዎች የኮምፒውተር ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት መጠቀም የፈለገ ማንኛውም ሰው በነፃ እንዲያገኘው በማድረግ ማባዛትም ሆነ ለሌላ ሰው ማስተላለፍ እንደሚቻል ይገልጻሉ። ይሁን እንጂ አብዛኞቹ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ለሽያጭ የሚውሉ ናቸው። በግልም ይሁን በድርጅት መልክ በዚህ ፕሮግራም መጠቀም የሚፈልጉ ሰዎች ፕሮግራሙን መግዛት ወይም ገንዘብ መክፈል ይጠበቅባቸዋል። አንድ ሰው ምንም ዓይነት ክፍያ ሳያከናውን አንድን የኮምፒውተር ፕሮግራም ቢወስድ ወይም ቢያባዛ ሕገ ወጥ ድርጊት ይሆናል። ሙሉ መጻሕፍትን በማባዛት ቅጂውን በነፃ ለሌላ ወገን ከመስጠት ተለይቶ አይታይም።

የኮምፒውተር ጨዋታዎችን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች የተጠቃሚነት ፈቃድ የሚኖራቸው ሲሆን ባለቤቱ/ተጠቃሚው በዚያ ላይ ከተጠቀሰው መመሪያ ወይም እገዳ ጋር የመስማማት ግዴታ ይኖርበታል። ከእነዚህ የፈቃድ ወረቀቶች መካከል ብዙዎቹ ፕሮግራሙን ኮምፒውተሩ ላይ ማስገባት ወይም በዚህ ፕሮግራም መጠቀም የሚችለው አንድ ሰው ብቻ እንደሆነ ይጠቅሳሉ። ብዙውን ጊዜም በቤት ውስጥም ሆነ በሥራ ቦታ ወይም በትምህርት ቤት ፕሮግራሙን ማስገባት የሚቻለው አንድ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ነው። አንዳንድ የፈቃድ ወረቀቶች ተጠቃሚው ለራሱ የፕሮግራሙን ሁለተኛ ቅጂ መያዝ የሚችል ቢሆንም ለሌሎች ሰዎች አባዝቶ መስጠት እንደሌለበት ይጠቅሳሉ። ባለቤቱ ጠቅላላውን ፕሮግራም ለሌላ ሰው አሳልፎ መስጠት ከፈለገ (የተጠቃሚነት ፈቃዱንና ሰነዱን ጨምሮ ማለት ነው) እንደዚያ ማድረግ ይችላል። ይሁን እንጂ ከዚህ በኋላ የእርሱ ተጠቃሚነት ያከትማል ማለት ነው። የተጠቃሚነት ፈቃድ አንዱ ከሌላው ስለሚለያይ አንድ ሰው ፕሮግራሙን ሲገዛ ወይም ከሌላ ወገን ሲቀበል የተጠቃሚነት ፈቃዱ ምን ገደቦችን እንደሚያካትት ማጣራት ይኖርበታል።

ብዙ አገሮች የኮምፒውተር ፕሮግራሞችን ጨምሮ “የፈጠራ ውጤቶችን የባለቤትነት መብት” ማስጠበቅን በሚጠይቀው የባለቤትነት መብት አጠባበቅ ስምምነት ውስጥ የታቀፉ በመሆናቸው ይህንን ጉዳይ በሕግ ለማስከበር ይጥራሉ። ለምሳሌ ያህል ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ በጥር 14, 2000 እትሙ ላይ “የጀርመንና የዴንማርክ ፖሊሶች የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ዘራፊ ቡድን ሲሉ የጠሯቸውን” የኮምፒውተር ፕሮግራሞችና ጨዋታዎች ሲያባዙና ሲያሰራጩ አልፎ ተርፎም በኢንተርኔት አማካኝነት ለገበያ ሲያቀርቡ ያገኟቸውን “ሰዎች በቁጥጥር ሥር አውለዋል” በማለት ዘግቧል።

በዚህ ረገድ የክርስቲያን ጉባኤ አቋም ምን መሆን አለበት? ኢየሱስ “የቄሣርን ለቄሣር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ” በማለት ተናግሯል። (ማርቆስ 12:​17) ይህም ክርስቲያኖች ከአምላክ ሕግ ጋር የማይጋጩትን የአገሩን ሕጎች እንዲታዘዙ ይጠይቅባቸዋል። መንግሥታትን በተመለከተ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚከተለው ሲል ጽፏል:- “ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። . . . ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ።”​—⁠ሮሜ 13:​1, 2

በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ያሉ ሽማግሌዎች የባለቤትነትን መብት በተመለከተ የወጡትን ሕግጋት ተግባራዊነት እንደሚከታተል ወይም እንደሚያስፈጽም አካል የሌሎችን ኮምፒውተር የመፈተሽ ኃላፊነት የለባቸውም። ይሁን እንጂ ክርስቲያኖች የእነርሱ ያልሆነውን ነገር ከመውሰድ መቆጠብና ለሕግ ተገዢ መሆን እንዳለባቸው ያምናሉ ይህንኑም ያስተምራሉ። ይህም ክርስቲያኖች ሕግ በመጣስ እንዳይቀጡ የሚጠብቃቸው ከመሆኑም ሌላ በአምላክ ፊት በጎ ሕሊና እንዲኖራቸው ይረዳቸዋል። ጳውሎስ እንደሚከተለው ሲል ጽፏል:- “ስለዚህ ስለ ቊጣው ብቻ አይደለም ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው።” (ሮሜ 13:​5) በተመሳሳይም ጳውሎስ የእውነተኛ ክርስቲያኖችን ፍላጎት በሚከተሉት ቃላት ገልጾታል:- “በነገር ሁሉ በመልካም እንድንኖር ወደን፣ መልካም ሕሊና እንዳለን ተረድተናልና።”​—⁠ዕብራውያን 13:​18

[በገጽ 29 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕል]

አንዳንድ መሥሪያ ቤቶችና ትምህርት ቤቶች ከአንድ በላይ ተጠቃሚ እንዲኖር የሚፈቅድና በፕሮግራሙ እስከ ምን ያህል ሰው ድረስ ሊጠቀም እንደሚችል ለይቶ የሚጠቅስ ፈቃድ ያላቸውን የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ይገዛሉ። በ1995 የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች የሚከተለውን ምክር ባካተተ አንድ ጽሑፍ ላይ ውይይት አድርገዋል:-

“የኮምፒውተር ፕሮግራሞችን የሚያዘጋጁና የሚሸጡ አብዛኞቹ ኩባንያዎች ሕጋዊ የሆነ የባለቤትነት መብት ያላቸው ሲሆን ፕሮግራሙን ሕጋዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም ምን እንደሚያስፈልግ የሚገልጽ የፈቃድ ወረቀት ያዘጋጃሉ። ብዙውን ጊዜ ይህ የፈቃድ ወረቀት ባለንብረቱ የፕሮግራሙን ቅጂ ለሌላ ሰው መስጠት እንደማይችል ይገልጻል፤ እንዲያውም ዓለም አቀፍ የባለቤትነት መብት ድንጋጌም እንዲህ ማድረጉ ሕጋዊ እንዳልሆነ ይገልጻል። . . . አንዳንድ ትልልቅ ኩባንያዎች የምሥክር ወረቀት ያላቸው ፕሮግራሞችን ከኮምፒውተሮች ጋር ይሸጣሉ። ነገር ግን አንዳንድ የኮምፒውተር ሱቆች ኮምፒውተሩ ውስጥ ያስገቡት ፕሮግራም ሕጋዊ ስላልሆነ የምሥክር ወረቀት አያዘጋጁም። የገዛው ሰው በፕሮግራሞቹ ሲጠቀም ሕግ እየተላለፈ ነው ማለት ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ መልኩ ክርስቲያኖች የባለቤትነት መብታቸው የተጠበቀና (እንደ ማኅበሩ ጽሑፎች ማለት ነው) ከኤሌክትሮኒክስ የመረጃ አምዶች ያለ ባለቤቶቹ ሕጋዊ ፈቃድ የሚባዙ መረጃዎችን ከመጠቀም ወይም ወደ ኮምፒውተራቸው ከማዛወር መቆጠብ ይኖርባቸዋል።”