በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ያለ ደም የሚሰጥ ቀዶ ሕክምና—“እየተለመደ የመጣ የሕክምና ዘዴ”

ያለ ደም የሚሰጥ ቀዶ ሕክምና—“እየተለመደ የመጣ የሕክምና ዘዴ”

ያለ ደም የሚሰጥ ቀዶ ሕክምና—“እየተለመደ የመጣ የሕክምና ዘዴ”

ማክሌንስ የተባለ መጽሔት “ ‘ያለ ደም የሚደረግ’ ቀዶ ሕክምና” በሚል ርዕስ ሥር በመላው ካናዳ የሚገኙ ዶክተሮች “ባለፉት አምስት ዓመታት ያለ ደም የሚደረግ ቀዶ ሕክምና የተለመደ የሕክምና ዘዴ እየሆነ እንደመጣ” ዘግቧል። ከእነዚህ ዶክተሮች መካከል አንዱ በዊንፔግስ ጤና ሳይንስ ማዕከል ሰመመን ሰጪ ሐኪም የሆኑት ብሪያን ሙርሄድ ይገኙበታል። ደም መስጠትን በማይጠይቁ አማራጭ ዘዴዎች ላይ ምርምር እንዲያደርጉ ያነሳሳቸው ምንድን ነው?

ዶክተር ሙርሄድ በ1986 በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በተመሠረተ እምነታቸው ምክንያት ያለ ደም ቀዶ ሕክምና እንዲደረግላቸው የጠየቁ የሚደማ ቁስል ያለባቸውን አንድ የ70 ዓመት የይሖዋ ምሥክር አዛውንት በቀዶ ሕክምና የመርዳት ፈታኝ ሁኔታ ገጠማቸው። (ሥራ 15:​28, 29) ዶክተር ሙርሄድ “የበሽተኛው የደም ዝውውር ግፊት ከፍ እንዲል ለማድረግ ቀደም ሲል እምብዛም ጥቅም ላይ ያልዋለውን ሳላይን ሶሉሽንን በደም ሥር የመስጠት ዘዴ ተጠቀሙ። የተጠቀሙበት ዘዴ ስኬታማ ከመሆኑም በላይ ‘ለትንሽ ለትልቁ ችግር ደም እንሰጥ ነበር። ፊታችንን ወደ ሌሎች አማራጭ ዘዴዎች ዞር ማድረግ የሚገባን ጊዜ ላይ ደርሰናል ብዬ አስባለሁ’ የሚለውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የዶክተሩን እምነት የሚያጠናክር ነበር” ሲል ማክሌንስ ዘግቧል።

“ወደፊት የደም አቅርቦት እጥረት ያጋጥማል የሚለው አሳሳቢ ሁኔታና በቫይረስ የተበከለ ደም ይሰጠን ይሆናል የሚለው የብዙ በሽተኞች ስጋት” ያለ ደም በሚሰጠው ሕክምና ላይ ተጨማሪ ምርምር እንዲደረግ ትልቅ ግፊት አሳድረዋል። በምርምሩ ላይ ለተካፈሉት ዶክተሮች ምስጋና ይድረሳቸውና የይሖዋ ምሥክሮች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም የውጤቱ ተጠቃሚ ሆነዋል። ማክሊንስ “ያለ ደም የሚደረገው ቀዶ ሕክምና በተለያዩ ምክንያቶች ደም የመስጠትን ልማድ ከማስወገዱም በላይ በተበከለ ደም ሳቢያ ለሚገጥም ኢንፌክሽን የመጋለጡ አደጋ (አጋጣሚው አነስተኛ ቢሆንም) ይቀንሳል” በማለት ዘግቧል። የሚሰጠው ደም “ንጹሕ” ቢሆንም እንኳ የታካሚውን በሽታ የመከላከል አቅም ለጊዜውም ቢሆን በማዳከም ኢንፌክሽን ሊያስከትልበት ይችላል።

የይሖዋ ምሥክሮች ደም መውሰድን የማይጠይቁ አማራጭ የሕክምና ዓይነቶችን በተመለከተ የጸና አቋም እንዲይዙ ያደረጋቸው ምስጢር ምንድን ነው? ይህን በሚመለከት ደም ሕይወትህን ሊያድን የሚችለው እንዴት ነው? የሚለውን ብሮሹር ማንበብ ትፈልግ ይሆናል። ይህን ብሮሹር ከይሖዋ ምሥክሮች ማግኘት ትችላለህ።

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ደም ሕይወትህን ሊያድን የሚችለው እንዴት ነው?