በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መጽሐፍ ቅዱስን ለማወቅ የሚያስችል እርዳታ

መጽሐፍ ቅዱስን ለማወቅ የሚያስችል እርዳታ

መጽሐፍ ቅዱስን ለማወቅ የሚያስችል እርዳታ

መጽሐፍ ቅዱስ በዓይነቱ ልዩ የሆነ መጽሐፍ ነው። ጸሐፊዎቹ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት እንደጻፉት የተናገሩ ሲሆን የመጽሐፉም ይዘት በመንፈስ አነሳሽነት እንደተጻፈ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዟል። (2 ጢሞቴዎስ 3:​16) መጽሐፍ ቅዱስ ሕይወት ያገኘነው እንዴት ነው፣ የመኖራችን ዓላማ ምንድን ነው እና መጨረሻችንስ ምን ይሆን ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። በእርግጥም ልንመረምረው የሚገባ መጽሐፍ ነው!

ምናልባት መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ሞክረህ ለመረዳት አስቸጋሪ ሆኖብህ ይሆናል። በአእምሮህ ለሚመላለሱት ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዴት መልስ ማግኘት እንደምትችል ለማወቅ ተቸግረህ ይሆናል። ከሆነ እንደዚህ ያለ ችግር ያጋጠመህ አንተ ብቻ አይደለህም። ሁኔታህ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ይኖር ከነበረ አንድ ሰው ጋር ይመሳሰላል። ሰውዬው ከኢየሩሳሌም ወደ ትውልድ አገሩ ወደ ኢትዮጵያ በሰረገላ ይጓዝ ነበር። ይህ ኢትዮጵያዊ ባለ ሥልጣን ከሰባት መቶ ዓመት በፊት በኢሳይያስ የተጻፈውን የመጽሐፍ ቅዱስ የትንቢት መጽሐፍ ድምፁን ከፍ አድርጎ ያነብብ ነበር።

በድንገት፣ አንድ ሰው ከሰረገላው ጎን እየሮጠ ሰላምታ አቀረበለት። ሰውዬው የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ፊልጶስ ሲሆን “በእውኑ የምታነበውን ታስተውለዋለህን?” በማለት ኢትዮጵያዊውን ጠየቀው። ኢትዮጵያዊውም “የሚመራኝ ሳይኖር ይህ እንዴት ይቻለኛል?” ሲል መለሰለት። ከዚያም ሰረገላው ላይ እንዲወጣ ፊልጶስን ጋበዘው። ፊልጶስ ሰውዬው ያነብብ የነበረውን የመጽሐፍ ክፍል ትርጉም ካብራራለት በኋላ “ስለ ኢየሱስ ወንጌልን” ይሰብክለት ጀመር።​—⁠ሥራ 8:​30-35

ከብዙ ዓመታት በፊት ኢትዮጵያዊው የአምላክን ቃል እንዲያስተውል ፊልጶስ እንደረዳው ሁሉ ዛሬም የይሖዋ ምሥክሮች ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያስተውሉ ይረዷቸዋል። አንተንም ለመርዳት ፈቃደኞች ናቸው። ብዙውን ጊዜ ቅዱስ ጽሑፋዊ ከሆኑት መሠረተ ትምህርቶች በመነሳት መጽሐፍ ቅዱስን በዘዴ ማጥናት በጣም ጥሩ ነው። (ዕብራውያን 6:​1) እድገት እያደረግህ ስትመጣ ሐዋርያው ጳውሎስ “ጠንካራ ምግብ” ብሎ የጠራውን ጥልቅ እውነት መረዳት ትጀምራለህ። (ዕብራውያን 5:​14) የምታጠናው መጽሐፍ ቅዱስን ቢሆንም መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት የሚያግዙ ሌሎች ጽሑፎች የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን የሚያብራሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የሚገኙበትን ቦታ እንድታውቅና ትርጉማቸውን እንድታስተውል ሊረዱህ ይችላሉ።

ብዙውን ጊዜ ጥናቱ አንተን በሚያመችህ ሰዓትና ቦታ ሊደረግ ይችላል። እንዲያውም አንዳንዶች በስልክ ያጠናሉ። ጥናቱ ተማሪዎች እንደሚማሩት በክፍል ውስጥ የሚሰጥ አይደለም። አስተዳደግህንና የትምህርት ችሎታህን ግምት ውስጥ በማስገባት ከሁኔታህ ጋር በሚስማማ መንገድ በግለሰብ ደረጃ የሚዘጋጅ ነው። እንደዚህ ላለው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍያ አትጠየቅም። (ማቴዎስ 10:​8) ፈተና ስለማይሰጥ ምንም የሚያስጨንቅህ ነገር አይኖርም። ለጥያቄዎችህ አጥጋቢ መልስ የምታገኝ ከመሆኑም በላይ ወደ አምላክ እንዴት መቅረብ እንደምትችል ትማራለህ። ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስን ለምን አታጠናም? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ደስታህን እንዴት ከፍ ሊያደርግልህ እንደሚችል የሚያሳዩ አንዳንድ ምክንያቶችን ተመልከት።