በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥቅምት 6, 2001 የሚደረግ ዓመታዊ ስብሰባ

ጥቅምት 6, 2001 የሚደረግ ዓመታዊ ስብሰባ

ጥቅምት 6, 2001 የሚደረግ ዓመታዊ ስብሰባ

የፔንሲልቬንያ የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር አባላት ዓመታዊ ስብሰባ ጥቅምት 6, 2001 በኒው ጀርሲ ክፍለ ሀገር፣ በጀርሲ ሲቲ 2932 ኬኔዲ በሊቨርድ በሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። አባላቱ ብቻ የሚገኙበት ስብሰባ ከጠዋቱ 3:​15 ከተደረገ በኋላ 4 ሰዓት ላይ አጠቃላይ ዓመታዊው ስብሰባ ይደረጋል።

ካለፈው ዓመት ወዲህ የፖስታ አድራሻቸውን የለወጡ የማኅበሩ አባላት መደበኛዎቹ የማስታወቂያ ደብዳቤዎችና የውክልና ማስረጃዎች በሐምሌ ወር ውስጥ እንዲደርሷቸው ለውጡን አሁኑኑ ለጸሐፊው ቢሮ ማስታወቅ ይኖርባቸዋል።

ከዓመታዊው የስብሰባ ማስታወቂያዎች ጋር ለአባላቱ የሚላኩት የውክልና ሠነዶች ከነሐሴ 1 በፊት ለማኅበሩ ጽሕፈት ቤት ተመልሰው መድረስ አለባቸው። እያንዳንዱ አባል በስብሰባው ላይ ራሱ ይገኝ ወይም አይገኝ እንደሆነ በመግለጽ ውክልናውን ወዲያውኑ ሞልቶ መመለስ አለበት። በስብሰባው ላይ ማን እንደሚገኝ የሚታወቀው በዚህ መሠረት ስለሆነ በእያንዳንዱ የውክልና ሠነድ ላይ የሚሰጠው መረጃ በዚህ ነጥብ ላይ ግልጽ መሆን ይኖርበታል።

መደበኛውን የሥራ ጉዳይና ሪፖርት ጨምሮ ጠቅላላው ስብሰባ ከቀኑ 7 ሰዓት ወይም ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ያበቃል ተብሎ ይገመታል። ከሰዓት በኋላ ስብሰባ አይኖርም። ያለው ቦታ የተወሰነ በመሆኑ መግባት የሚቻለው በቲኬት ብቻ ይሆናል። ዓመታዊውን ስብሰባ ወደ ሌሎች አዳራሾች በስልክ ለማስተላለፍ የተደረገ ዝግጅት የለም።