በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ጠንካራ ነው

ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ጠንካራ ነው

ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ጠንካራ ነው

ወርቅ በውበቱና በጥንካሬው በጣም ተፈላጊ የሆነ ማእድን ነው። ወርቅ በአብዛኛው ተፈላጊ የሆነበት ምክንያት ለረጅም ጊዜ ቢቆይ እንኳ ድምቀቱን የማይለውጥና የማይደበዝዝ በመሆኑ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት ውኃ፣ ኦክስጅን፣ ድኝ ወይም ማንኛውም ሌላ ነገር ሊያበላሸው ስለማይችል ነው። በሰጠሙ ዕቃዎች ውስጥ ወይም ሌላ ቦታ የተገኙ በርካታ ከወርቅ የተሠሩ ጌጣጌጦች ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ እንኳ መልካቸውን ሳይለውጡ ተገኝተዋል።

ይሁን እንጂ በጣም የሚያስገርመው መጽሐፍ ቅዱስ ከወርቅ ይልቅ ጠንካራና “በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር” ነገር እንዳለ ይናገራል። (1 ጴጥሮስ 1:​7) በእሳትና በሌሎች ሂደቶች አማካኝነት “የተፈተነ” ወይም የተጣራ ወርቅ 99.9 ከመቶ ንጹሕ ሊሆን ይችላል። ሆኖም በደንብ የተጣራ ወርቅ እንኳ የሦስት እጅ ሃይድሮክሎሪክ አሲድ እና የአንድ እጅ ናይትሪክ አሲድ ድብልቅ በሆነው በአኩዋሬጂያ ውስጥ ቢከቱት ይጠፋል ወይም ይሟሟል። በመሆኑም መጽሐፍ ቅዱስ ‘ወርቅ ይጠፋል’ ብሎ መናገሩ ከሳይንስ አንጻር ትክክለኛ ነው።

በአንጻሩ ግን እውነተኛ ክርስቲያናዊ እምነት ‘ነፍስን ያድናል።’ (ዕብራውያን 10:​39) ሰዎች በኢየሱስ ላይ እንዳደረጉት ሁሉ ጠንካራ እምነት ያለውን አንድ ግለሰብ ሊገድሉ ይችላሉ። ሆኖም እውነተኛ እምነት ያላቸው ሰዎች “እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ” የሚል ቃል ተገብቶላቸዋል። (ራእይ 2:​10) እምነታቸውን ጠብቀው የሞቱ ሰዎች በአምላክ መታሰቢያ ውስጥ ስለሚቆዩ ከሞት ያስነሳቸዋል። (ዮሐንስ 5:​28, 29) የቱንም ያህል ብዛት ያለው ወርቅ ቢሆን ይህን ሊያስገኝ አይችልም። በዚህ ረገድ እምነት ከወርቅ የበለጠ ዋጋ አለው ሊባል ይችላል። ይሁን እንጂ እምነት እንዲህ ያለውን ከፍተኛ ዋጋ እንዲያገኝ ከተፈለገ መጥራት ወይም መፈተን ይገባዋል። እንዲያውም ጴጥሮስ ከወርቅ ይልቅ የከበረ ዋጋ አለው ብሎ የጠቀሰው ‘የተፈተነን እምነት’ ነው። አንተም በእውነተኛው አምላክ በይሖዋ እና በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ጠንካራ እምነት መገንባት እንድትችል የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስ እንድታጠና ሊረዱህ ፈቃደኞች ናቸው። ይህ ኢየሱስ እንደተናገረው “የዘላለም ሕይወት” ያስገኛል።​—⁠ዮሐንስ 17:​3