በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የተሰጠ የምሥክር ወረቀት

የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የተሰጠ የምሥክር ወረቀት

የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የተሰጠ የምሥክር ወረቀት

በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ የሚገኘው የኮንጎ እና የአፍሪካ ጋዜጠኞች ኅብረት ለእድገት (AJOCAD) የተባለው ድርጅት “[በኮንጎ] ለሚታየው እድገት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች ወይም ማኅበራዊ ተቋማት” እንዲህ ያለውን የምሥክር ወረቀት ይሰጣል።

የይሖዋ ምሥክሮች “በማስተማር እንዲሁም ትምህርት ሰጪ የሆኑ ጽሑፎችን በማተምና በማሰራጨት ለኮንጎ ሕዝብ እድገት ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ” ድርጅቱ ኅዳር 17, 2000 የምሥክር ወረቀት ሰጥቷቸዋል።

ኪንሻሳ ውስጥ የሚዘጋጀው ለ ፋር የተባለው ጋዜጣ የተሰጠውን ሽልማት አስመልክቶ አስተያየቱን ሲሰጥ “መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! የተባሉ መጽሔቶችን ወይም በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጁ ሌሎች ጽሑፎችን አግኝቶ ያላነበበ የኮንጎ ዜጋ የለም ለማለት ይቻላል። እነዚህ መጽሔቶች ሁሉንም የሕይወት ዘርፎች [ይዳስሳሉ]” ብሏል። እነዚህ ጽሑፎች “የዘመናችንን ችግሮች እንዴት መቋቋም እንደሚቻል” እንዲሁም “ከወቅታዊ ሁኔታዎች በስተጀርባ ያለውን እውነተኛ ትርጉም” እንደሚጠቁሙ ጋዜጣው ጨምሮ ገልጿል። እያንዳንዱ የንቁ! መጽሔት እትም “በፖለቲካ ጉዳዮች ገለልተኛ ሲሆን አንዱን ዘር ከሌላው አያስበልጥም።” ከዚህም በተጨማሪ መጽሔቶቹ “አሁን ያለውን ክፉና ዓመፀኛ ሥርዓት የሚተካ ሰላም የሰፈነበትና አስተማማኝ አዲስ ዓለም እንደሚመጣ ፈጣሪ በሰጠው ተስፋ ላይ ሰዎች ያላቸውን እምነት እንዲያሳድጉ” ይረዳሉ።

ይህ ድርጅት እንዳመለከተው የይሖዋ ምሥክሮች የሚያዘጋጁአቸው ጽሑፎች ለአብዛኛው የኮንጎ ሕዝብ ጠቃሚ መሆናቸው ታይቷል። እነዚህን ጽሑፎች በመቶ በሚቆጠሩ ቋንቋዎች ማግኘት ስለሚቻል አንተም ተስፋን ከሚያለመልመው ከዚህ መልእክት ጥቅም ማግኘት ትችላለህ።

እነዚህን ጽሑፎች እንዴት ማግኘት እንደምትችል ለማወቅ ቀጥሎ ያለውን ተመልከት።