በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በአንድ ወቅት ተኩላ ነበርን—አሁን ግን በጎች ሆነናል!

በአንድ ወቅት ተኩላ ነበርን—አሁን ግን በጎች ሆነናል!

በአንድ ወቅት ተኩላ ነበርን​—⁠አሁን ግን በጎች ሆነናል!

እኔና ሳኪና ልጆች ሳለን ጎረቤታሞች ነበርን። ሳኪና ግዙፍና ወፍራም ስትሆን እኔ ደግሞ ቀጫጫ ነበርኩ። ብዙ ጊዜ እንጣላ የነበረ ሲሆን ይባስ ብለን አንድ ቀን ተደባደብን። ከዚያን ቀን ጀምሮ ተኮራርፈን መነጋገርም ሆነ ሰላም መባባል አቆምን። ከጊዜ በኋላ ሁለታችንም መኖሪያ ቀየርንና ተለያየን።

በ1994 ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት በመጀመሬ ቀስ በቀስ የባሕርይ ለውጥ ማድረግ ጀመርኩ። ከአራት ዓመት በኋላ በቡጁምቡራ፣ ብሩንዲ ተደርጎ በነበረው የልዩ ስብሰባ ቀን ላይ ሳኪናን ሳያት በጣም ተገረምኩ። እዚህ ስላየኋት ደስ ቢለኝም ሰላምታችን ቀዝቃዛ ነበር። በዚያው ዕለት ትንሽ ቆየት ብሎ ከጥምቀት እጩዎች ጋር ስመለከታት ዓይኔን ማመን አቃተኝ። እርሷም ሙሉ በሙሉ ተለውጣለች። ከዚህ ቀደም ዘወትር እንጣላ እንደነበረው የጠበኝነት ባሕርይዋን ትታለች። በውኃ በመጠመቅ ራሷን ለአምላክ መወሰኗን በሕዝብ ፊት ስታሳይ መመልከት ምንኛ የሚያስደስት ነበር!

ከውኃው ስትወጣ ሮጬ አቀፍኳትና በጆሮዋ “ምን ያህል እንጣላ እንደነበር ታስታውሻለሽ?” አልኳት። “አዎን፣ አስታውሳለሁ። ያ ጊዜ አልፏል። አሁን ሌላ ሰው ነኝ” አለችኝ።

ሁለታችንም አንድ የሚያደርገውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በማግኘታችንና የነበረንን የተኩላ ዓይነት ባሕርይ ለውጠን በታላቁ እረኛ በይሖዋ አምላክ በጎች መካከል በመገኘታችን ደስተኞች ነን። በእርግጥም የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የሰዎችን ጠባይ ይለውጣል።