በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአንባብያን ጥያቄዎች

የአንባብያን ጥያቄዎች

የአንባብያን ጥያቄዎች

ቆላስይስ 1:​16 ስለ አምላክ ልጅ ሲናገር “ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል” ይላል። ‘ሁሉ ለእርሱ’ ማለትም የአምላክ ልጅ ለሆነው ለኢየሱስ ተፈጥሮአል ሲባል ምን ማለት ነው?

ይሖዋ ከራሱ ከኢየሱስ በስተቀር ሌሎች ነገሮችን ሁሉ ለመፍጠር አንድያ ልጁን ዋና ሠራተኛ አድርጎ ተጠቅሞበታል። (ምሳሌ 8:​27-30፤ ዮሐንስ 1:​3) ልጁም ከእነዚህ የፍጥረት ሥራዎች ደስታ የሚያገኝ ሲሆን ከዚህ አንጻር ሲታይ “ለእርሱ” ተፈጥረዋል መባሉ የተገባ ነው።

ሰብዓዊ ወላጆች ወንዶች ወይም ሴቶች ልጆች ሲያገኙ ደስ እንደሚላቸው እናውቃለን። በመሆኑም አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌ ‘አባት ደስ ስለሚሰኝበት ልጅ’ ይናገራል። (ምሳሌ 3:​12፤ 29:​17) በተመሳሳይም ይሖዋ አምላክ ሕዝቦቹ እስራኤላውያን ታማኝ በነበሩበት ጊዜ ተደስቶባቸዋል። (መዝሙር 44:​3፤ 119:​108፤ 147:​11) አሁን እኛ እስካለንበት ዘመን ድረስ ያሉ የታመኑ ሰዎች በሚያደርጉትም ነገር ይደሰታል።​—⁠ምሳሌ 12:​22፤ ዕብራውያን 10:​38

ስለሆነም አምላክ የሥራ ባልደረባው ኢየሱስ በሥራው ውጤት እንዲደሰት ማድረጉ የተገባ ነው። እንዲያውም ምሳሌ 8:​31 ‘ከምድሩ ደስታን እንዲሁም ከሰው ልጆች ተድላን’ ያገኝ እንደነበር ይናገራል። ቆላስይስ 1:​16 “ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥረዋል” የሚለው ከዚህ አንጻር ነው።​—⁠በሰያፍ የጻፍነው እኛነን።