በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በመካከለኛው አፍሪካ በመለኮታዊው ስም ይጠቀማሉ

በመካከለኛው አፍሪካ በመለኮታዊው ስም ይጠቀማሉ

በመካከለኛው አፍሪካ በመለኮታዊው ስም ይጠቀማሉ

በመካከለኛው አፍሪካ የሚኖሩ አብዛኞቹ ሰዎች በአምላክ ያምናሉ። የሁሉ ፈጣሪ መሆኑን ፈጽሞ አይጠራጠሩም። (ራእይ 4:​11) ሆኖም በሌሎች አገሮች እንደሚኖሩ በርካታ ሰዎች ሁሉ እነሱም በአብዛኛው ይሖዋ በሚለው የግል ስሙ አይጠሩትም።

በመካከለኛው አፍሪካም ሆነ በሌሎች የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ሰዎች “ስምህ ይቀደስ” በማለት የጌታን ጸሎት ሲያቀርቡ የአምላክን ስም ማመልከታቸው ነው። (ማቴዎስ 6:​9) ሆኖም ለረጅም ጊዜ ይህን ስም የሚያውቁት ጥቂቶች ብቻ ነበሩ። ይሁን እንጂ ባለፉት በርካታ ዓመታት የይሖዋ ምሥክሮች ያከናወኑት ቅንዓት የተሞላበት የስብከት እንቅስቃሴ መለኮታዊውን ስም መጠቀምን በተመለከተ የሰዎች አመለካከት እንዲለወጥ አድርጓል። በዛሬው ጊዜ መለኮታዊው ስም በበርካታ የአፍሪካ ቋንቋዎች በሰፊው የታወቀ ከመሆኑም በላይ ተቀባይነት አግኝቷል። ከእነዚህ ቋንቋዎች መካከል ዙሉ (ኡጃሆዋ)፣ የሩባ (ጅሆፋ)፣ ቆሳ (ኡይሆዋ) እና ስዋሒሊ (ይሖፋ) ይገኙበታል። ሆኖም በእነዚህ ቋንቋዎች የተዘጋጁ አብዛኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አሁንም በመለኮታዊው ስም አይጠቀሙም።

በመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ፣ በሱዳንና በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ አንዳንድ ክፍሎች በሚነገረው በዛንዲ ቋንቋ የተዘጋጀው መለኮታዊውን ስም የሚጠቀመው መጽሐፍ ቅዱስ ድንቅ የትርጉም ሥራ ነው። በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች በትውልድ ቋንቋቸው ይኮቫ ብለው በመጥራት የአምላክን ስም ይጠቀሙበታል። መለኮታዊው ስም በአንድ የመግባቢያ ቋንቋ የተገለጸበት መንገድ ምንም ይሁን ምን በስሙ መጠቀም አስፈላጊ ነው። ለምን? ምክንያቱም “የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።”​—⁠ሮሜ 10:​13 NW 

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ካርታ/ሥዕል]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

መካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ

ሱዳን

የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ

[ምንጭ]

The Complete Encyclopedia of Illustration/J. G. Heck