በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመንግሥቱን መልእክት በቀላሉ ሊገኙ ለማይችሉ ሰዎች ማድረስ

የመንግሥቱን መልእክት በቀላሉ ሊገኙ ለማይችሉ ሰዎች ማድረስ

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

የመንግሥቱን መልእክት በቀላሉ ሊገኙ ለማይችሉ ሰዎች ማድረስ

የይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥቱን መልእክት ለሰዎች ሁሉ ለማድረስ ጥረት ያደርጋሉ። አንዳንድ ጊዜ በቤታቸው በቀላሉ የማይገኙ ሰዎችን አግኝቶ ለማነጋገር ከፍተኛ ጥረት ይጠይቃል። (ማርቆስ 13:​10) ይህን በሚመለከት በአንዲት የደቡብ አሜሪካ አገር የሚያገለግል አንድ ልዩ አቅኚ የሚከተለውን ተሞክሮ ተናግሯል።

“አንድ ቀን አገረ ገዢው እኔና ባለቤቴ ተመድበን የምናገለግልበትን አካባቢ ለመጎብኘት እንደሚመጡ ሰማሁ። እሳቸውም እምብዛም ቤታቸው ስለማይገኙ ደብዳቤ ጻፍኩና አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር፣ የሰው ዘር አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ እና ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባሉትን መጽሐፎች ጨምሮ አንዳንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን አንድ ላይ አድርጌ ላክሁላቸው። ደብዳቤው እያንዳንዱ ጽሑፍ የተዘጋጀበትን ዓላማ የሚገልጽ ነበር።

“ስለ ጽሑፎቹ ያላቸውን አስተያየት ማወቅ ፈልጌ ስለነበር ከእሳቸው ጋር መገናኘት እችል እንደሆነ ጥያቄ አቀረብኩ። ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ላነጋግራቸው እንደምችል ተነገረኝና የይሖዋ ምሥክሮች—⁠ከስሙ በስተጀርባ ያለው ድርጅት የተባለውን ቪዲዮ ካሴት ይዤ ሄድኩ። ለሁለት ሰዓታት ያህል አብረን ቆየን። ቪዲዮውን ከአገረ ገዥው ጋር አብረን ከተመለከትን በኋላ ምን እንደተሰማቸው ጠየቅኋቸው። ‘በምድር ላይ እንደ እናንተ ያለ ድርጅት የለም። መንግሥታችን የነደፋቸውን ፕሮጀክቶች ለማጠናቀቅ የሚረዱኝ እንደ እናንተ ያሉ ሰዎች ባገኝ ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር!’ በማለት መለሱልኝ። ከዚያም የድርጅታችንን ዋና መሥሪያ ቤት ጎብኝቼ አውቅ እንደሆነ ጠየቁኝ። ከ14 ዓመት ዕድሜዬ ጀምሮ ብሩክሊን ኒው ዮርክ የሚገኘውን ዋና መሥሪያ ቤት የመጎብኘት ግብ ቢኖረኝም እስከ አሁን አጋጣሚውን እንዳላገኘሁ ገለጽኩላቸው። በቀላሉ ሊደረስባቸው ከማይችሉ ግቦች መካከል አንዱ ይህ ነበር። ለአንድ አፍታ ትኩር ብለው ከተመለከቱኝ በኋላ ይህን አጋጣሚ እንዳገኝ እንደሚፈልጉ ገለጹልኝ። አንዳንድ ሕጋዊ ጉዳዮችን ካስፈጸሙልን በኋላ የአውሮፕላን ትኬቱን በስጦታ አበረከቱልን!

“አገረ ገዥው አሁን መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች ዘወትር ይደርሷቸዋል። በቅርቡ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ይጀምራሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።”