በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“አሁን ችግሬ ምን እንደነበር ተረዳሁ!”

“አሁን ችግሬ ምን እንደነበር ተረዳሁ!”

“አሁን ችግሬ ምን እንደነበር ተረዳሁ!”

በቶኪዮ የሚኖር አንድ ሰው ታኅሣሥ 1, 2000 መጠበቂያ ግንብ እትም ላይ የወጣውን የሕይወት ታሪክ ሲያነብ የተሰማው እንዲህ ነበር። ታሪኩ “ሕይወታችሁ ነገ ምን እንደሚሆን አታውቁም” የሚል ርዕስ ያለው ሲሆን በሕክምና አጠራር ማኒክ ዲፕረሽን በሚባል የአእምሮ ሕመም ስለሚሰቃይ አንድ የቀድሞ ሚስዮናዊ የሚናገር ነው።

በቶኪዮ የሚኖረው ሰው ለዚህ መጽሔት አዘጋጆች በጻፈው ደብዳቤ ላይ እንዲህ ብሏል:- “በታሪኩ ላይ የተገለጹት የበሽታው ምልክቶች በሙሉ በእኔ ላይ ከታዩት ምልክቶች ጋር አንድ ዓይነት ናቸው። ስለዚህ ወደ አእምሮ ሕመምተኞች ሆስፒታል ሄጄ ስመረመር ማኒክ ዲፕረሽን እንዳለብኝ ተረዳሁ። የመረመረኝ ዶክተር በሁኔታው በጣም ተገርሞ ‘ይህ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ ሕመምተኞች ነን ብለው አያስቡም’ በማለት ተናገረ። በሽታው ሥር ከመስደዱ በፊት ምንነቱን ለማወቅ ችያለሁ።”

በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እያንዳንዱን የመጠበቂያ ግንብ እትምና በተጓዳኝ የሚወጣውን ንቁ! መጽሔት በማንበብ የተለያዩ ጥቅሞች አግኝተዋል። ርዕሶቹ ትምህርት ሰጪና አርኪ ሆነውላቸዋል። በአሁኑ ጊዜ መጠበቂያ ግንብ በ141 ቋንቋዎች የሚታተም ሲሆን ንቁ! ደግሞ በ86 ቋንቋዎች ይታተማል። አንተም መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን ዘወትር ማንበብ ትችላለህ።