በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በዓለም ዙሪያ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ዘንድ አድናቆት ያተረፈው የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም

በዓለም ዙሪያ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ዘንድ አድናቆት ያተረፈው የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም

ምሉዓን ሆናችሁና ጽኑ እምነት ይዛችሁ ቁሙ

በዓለም ዙሪያ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ዘንድ አድናቆት ያተረፈው የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም

አሥራ ሁለት ዓመትና ሦስት ወር ከአሥራ አንድ ቀን ከፈጀ ትጋትና ጥረት የሚጠይቅ ሥራ በኋላ የአንድ አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም የመጨረሻ ክፍል መጋቢት 13, 1960 ተጠናቀቀ። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ የአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም የሚል ስያሜ ተሰጠው።

ከአንድ ዓመት በኋላ የይሖዋ ምሥክሮች ይህን ትርጉም በአንድ ጥራዝ አትመው አወጡት። በ1961 ይህ እትም በአንድ ሚልዮን ቅጂዎች ታትሞ ተሰራጨ። በአሁኑ ጊዜ ግን የታተሙት ቅጂዎች ብዛት ከመቶ ሚልዮን የበለጠ ሲሆን ይህም የአዲሲቱ ዓለም ትርጉምን ሰፊ ዓለም አቀፋዊ ስርጭት ካላቸው መጽሐፍ ቅዱሶች ተርታ ሊያሰልፈው በቅቷል። ይሁን እንጂ ምሥክሮቹ ይህን ትርጉም እንዲያዘጋጁ ያነሳሳቸው ምን ነበር?

አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ለምን አስፈለገ?

የይሖዋ ምሥክሮች የቅዱሳን ጽሑፎችን መልእክት ለመረዳትና ለሌሎች ለማወጅ ላለፉት ዓመታት በተለያዩ የእንግሊዝኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ሲጠቀሙ ቆይተዋል። እነዚህ ትርጉሞች የራሳቸው መልካም ጎኖች ቢኖሯቸውም በአብዛኛው የሕዝበ ክርስትና ሃይማኖታዊ ወጎችና ትምህርቶች ተጽዕኖ ይታይባቸዋል። (ማቴዎስ 15:6) ስለሆነም የይሖዋ ምሥክሮች በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፉት የመጀመሪያዎቹ ጽሑፎች የያዙትን ሐሳብ በትክክል የሚያቀርብ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እንደሚያስፈልግ ተገነዘቡ።

ይህን ችግር ለመቅረፍ የመጀመሪያው እርምጃ የተወሰደው የይሖዋ ምሥክሮች የአስተዳደር አካል አባል የሆነው ናታን ኤች ኖር በጥቅምት 1946 አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እንዲዘጋጅ ሐሳብ ባቀረበበት ወቅት ነበር። የመጀመሪያው ቅጂ የሚያስተላልፈውን ሐሳብ በትክክል የሚያስቀምጥ፣ በቅርቡ ከተገኙ ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች የተሰባሰቡ አዳዲስ የምሁራን ግኝቶችን ያካተተና የዛሬዎቹ አንባብያን ሊረዱት በሚችሉት ቋንቋ የተጻፈ ትርጉም የማዘጋጀት ዓላማ ይዞ የተነሣው የአዲሲቱ ዓለም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ኮሚቴ ታኅሣሥ 2, 1947 ሥራውን ጀመረ።

በ1950 የመጀመሪያው ክፍል ማለትም የአዲሲቱ ዓለም የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም ታትሞ ሲወጣ ተርጓሚዎቹ ግባቸውን እንደመቱ ተረጋገጠ። ከዚህ በፊት ለመረዳት አስቸጋሪ የነበሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በሚያስገርም ሁኔታ ግልጽ ሆኑ። ለምሳሌ ያህል በማቴዎስ 5:​3 ላይ ያለውን “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው” የሚለውን ግራ የሚያጋባ ጥቅስ ተመልከት። “ለመንፈሳዊ ፍላጎታቸው ንቁ የሆኑ ደስተኞች ናቸው” ተብሎ ተተርጉሟል። ደቀ መዛሙርቱ “የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድን ነው?” በማለት ለኢየሱስ ያቀረቡት ጥያቄ “የመገኘትህና የነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ ምልክት ምን ይሆናል?” ተብሎ ተተርጉሟል። (ማቴዎስ 24:​3) እንዲሁም “እግዚአብሔርንም የመምሰል ምስጢር” የሚለው የሐዋርያው ጳውሎስ አባባል “ለአምላክ ያደሩ የመሆን ቅዱስ ምስጢር” ተብሎ ተተርጉሟል። (1 ጢሞቴዎስ 3:​16) በእርግጥም የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም አዲስ እውቀት እንዲገኝ በር ከፍቷል።

ብዙ ምሁራን በዚህ የትርጉም ሥራ ተደንቀዋል። እንግሊዛዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር አሌክሳንደር ቶምሰን የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም በግሪክኛ የአሁን ጊዜን የሚያመለክተውን ግስ በትክክል በመተርጎም ረገድ ተወዳዳሪ እንደሌለው ተናግረዋል። በምሳሌ ለማስረዳት ያህል ኤፌሶን 5:25ን “ባሎች ሆይ፣ . . . ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤” በማለት ፈንታ “ባሎች ሆይ፣ ሚስቶቻችሁን መውደዳችሁን ቀጥሉ” ሲል ተርጉሞታል። ቶምሰን የአዲሲቱ ዓለም ትርጉምን አስመልክተው ሲናገሩ “ይህን የሰዋሰው አገባብ ልዩ ገጽታ የዚህን ያህል ምልዑ በሆነ መልኩ ያቀረበና በተደጋጋሚ የተጠቀመ ሌላ ትርጉም የለም” ብለዋል።

የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ን የላቀ የሚያደርገው ሌላ ገጽታ ይሖዋ የሚለውን የአምላክን የተጸውኦ ስም በዕብራይስጡም ሆነ በግሪክኛው የቅዱሳን ጽሑፎች ክፍል ውስጥ መጠቀሙ ነው። በተለምዶ ብሉይ ኪዳን እየተባለ በሚጠራው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ብቻ የአምላክ የዕብራይስጥ ስም ወደ 7, 000 የሚጠጋ ጊዜ መገኘቱ ፈጣሪያችን አምላኪዎቹ በስሙ እንዲጠሩትና የራሱ ስብዕና ያለው አካል አድርገው እንዲመለከቱት እንደሚፈልግ በግልጽ ያሳያል። (ዘጸአት 34:6, 7) የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እንደዚህ እንዲያደርጉ አስችሏል።

የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም በብዙ ቋንቋዎች ለመታተም በቃ

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም በእንግሊዝኛ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ለማግኘት ይጓጉ ነበር። ደግሞም በቂ ምክንያት አላቸው። በአንዳንድ አገሮች ውስጥ በአካባቢው ቋንቋ የሚገኙ ትርጉሞችን የሚያሰራጩ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበራት ተወካዮች መጽሐፍ ቅዱሶቻቸው በይሖዋ ምሥክሮች እጅ ውስጥ ሲገባ ስለማይደሰቱ እነዚህን ትርጉሞች ማግኘት አስቸጋሪ ነበር። ከዚህም በላይ እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በአብዛኛው ወሳኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን ያድበሰብሳሉ። በአንድ የደቡብ አውሮፓ ቋንቋ የተዘጋጀ ትርጉም ለዚህ ዓይነተኛ ምሳሌ ነው። “ስምህ ይቀደስ” የሚሉት የኢየሱስ ቃላት የሚገኙበትን ስለ አምላክ ስም የሚገልጸውን ወሳኝ ጥቅስ “በአሕዛብ የተከበርክ ሁን” በማለት ተርጉሞታል።​—⁠ማቴዎስ 6:9

በ1961 ተርጓሚዎች የእንግሊዝኛውን የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ወደ ሌሎች ቋንቋዎች የመተርጎሙን ሥራ ጀምረው ነበር። ከሁለት ዓመት በኋላ የአዲሲቱ ዓለም የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም በሌሎች ተጨማሪ ስድስት ቋንቋዎች ተተርጉሞ ቀረበ። በዚያን ጊዜ በዓለም ዙሪያ ይገኙ ከነበሩ ምሥክሮች ከአራቱ ሦስቱ ይህን መጽሐፍ ቅዱስ በቋንቋቸው ማንበብ ይችሉ ነበር። ቢሆንም የይሖዋ ምሥክሮች ይህን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በሚልዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ማዳረስ እንዲችሉ ከተፈለገ ገና ብዙ ሥራ መሠራት ነበረበት።

በ1989 በይሖዋ ምሥክሮች ዓለም አቀፉ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ የትርጉም አገልግሎት ክፍል ሲቋቋም የዚህ ግብ ተፈጻሚነት ይበልጥ እውን እየሆነ መጣ። ይህ ክፍል የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት ጥናትን ከኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ጋር ያቀናጀ የአተረጓጎም ዘዴን ፈጠረ። ይህን ዘዴ በመጠቀም የተለመደው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሥራ ይፈጅ ከነበረው በጣም ባነሰ ጊዜ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎችን በአንድ ዓመት የዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎችን ደግሞ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለመተርጎም ተቻለ። ይህ ዘዴ ተግባራዊ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ የእንግሊዝኛው የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ከሁለት ቢልዮን የሚበልጡ ሰዎች በሚናገሯቸው 29 ቋንቋዎች ተተርጉሟል። በሌሎች 12 ቋንቋዎችም ሥራው በመፋጠን ላይ ይገኛል። እስከ አሁን ድረስ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ከእንግሊዝኛ ወደ ሌሎች 41 ቋንቋዎች ተተርጉሟል።

ነሐሴ 3, 1950 በኒው ዮርክ ሲቲ በተካሔደው ‘የቲኦክራሲው ዕድገት’ የይሖዋ ምሥክሮች የአውራጃ ስብሰባ ላይ የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም የመጀመሪያ ክፍል ከወጣ አሁን ከ50 የሚበልጡ ዓመታት አልፈዋል። በዚያ ስብሰባ ላይ ናታን ኤች ኖር ተሰብሳቢዎቹን “ይሄን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ከዳር እስከ ዳር አንብቡት፤ እርካታ ታገኙበታላችሁ። የአምላክን ቃል በይበልጥ እንድትረዱት ስለሚያስችላችሁ በሚገባ አጥኑት። ለሌሎችም አሰራጩት” ሲል አበረታቷቸው ነበር። በውስጡ ያለው መልእክት ‘ምሉዕ ሆነህና በእግዚአብሔር ፈቃድ ጽኑ አቋም ይዘህ እንድትቆም’ ስለሚረዳህ መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ እንድታነብ እናበረታታሃለን።​—⁠ቆላስይስ 4:12 NW 

[በገጽ 8, 9 ላይ የሚገኝ ግራፍ/ሥዕል]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

“የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ታትሞ የወጣባቸው ቋንቋዎች

በመጀመሪያ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የወጣው የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም አሁን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በ41 ተጨማሪ ቋንቋዎች ይገኛል።

የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ

1950 1

1960-69 6 5

1970-79 4 2

1980-89 2 2

1990-እስከ አሁን 29 19