በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የእኩዮችን ተጽእኖ የሚቋቋሙት እንዴት ነው?

የእኩዮችን ተጽእኖ የሚቋቋሙት እንዴት ነው?

የእኩዮችን ተጽእኖ የሚቋቋሙት እንዴት ነው?

በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት የማግኘት ፍላጎት ብዙዎቹን ወጣቶች በእኩዮቻቸው አስተሳሰብና ድርጊት እንዲመሩ ተጽእኖ ያሳድርባቸዋል። በተለይ ወጣቶች አደገኛ ዕፆችን እንዲወስዱና በጾታ ብልግና እንዲካፈሉ ጥያቄ ሲቀርብላቸው እምቢ ለማለት ጥንካሬ ያስፈልጋቸዋል። ታዲያ የእኩዮችን ተጽእኖ መቋቋም የሚችሉት እንዴት ነው?

በቅርቡ በፖላንድ የሚኖሩ ሁለት በአሥራዎቹ እድሜ ውስጥ ያሉ ልጃገረዶች እንዲህ በማለት ጽፈዋል:- “የዓለም መንፈስ በብዙዎቹ የዕድሜ እኩዮቻችን ላይ በግልጽ ይታያል። በፈተናዎች ያጭበረብራሉ፣ አነጋገራቸው በጸያፍ ቃላት የተሞላ ነው፤ እንዲሁም ዘመን አመጣሽ አለባበሶችን መከተልና ልቅ የሆኑ የብልግና ዘፈኖችን ማዳመጥ ያስደስታቸዋል። እርካታ የሌላቸውና ዓመፀኛ የሆኑ በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ከሚያሳድሩት ተጽእኖ እንድንጠበቅ የሚረዱንና ለእኛ ለወጣቶች ተብለው የሚዘጋጁ ርዕሶችን በማግኘታችን ምንኛ ደስተኞች ነን!

“ወጣቶች ተፈላጊ እንደሆንና ሌሎች እንደሚያደንቁን እንድንገነዘብ ለረዱን የመጠበቂያ ግንብ ርዕሶች ያለንን አመስጋኝነት የምንገልጽበት ቃል የለንም። ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኘነው ምክር አካሄዳችንን በትክክለኛው አቅጣጫ በመምራት ይሖዋ አምላክን ማስደሰታችንን እንድንቀጥል ረድቶናል። ለይሖዋ የታማኝነት አገልግሎት ማቅረብ ከሁሉ የተሻለ የሕይወት መንገድ መሆኑን ተገንዝበናል።”

አዎን፣ ወጣቶች የእኩዮችን ተጽእኖ መቋቋም ይችላሉ። ክርስቲያን ወጣቶች ‘የማስተዋል ችሎታቸውን’ በማዳበራቸው “የዓለምን መንፈስ” ሳይሆን “ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ” የሚያንጸባርቅ ጥበብ ያለበት ውሳኔ ማድረግን ይማራሉ።​—⁠ዕብራውያን 5:​14 NW ፤ 1 ቆሮንቶስ 2:​12