በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታስታውሳለህን?

ታስታውሳለህን?

ታስታውሳለህን?

በቅርብ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች አንብበሃቸዋል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር:-

የጀርመን ፌዴራላዊ ሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባኤ ሃይማኖትን በሚመለከት ለየትኛው ሕጋዊ ድል አስተዋጽኦ አድርጓል?

ጉባኤው የይሖዋ ምሥክሮችንና ሕጋዊ እውቅና ለማግኘት ያቀረቡትን ጥያቄ በሚመለከት አንድ ሌላ ችሎት አሳልፎት የነበረውን ብይን ሽሯል። የይሖዋ ምሥክሮችን ድል ያቀዳጀው ይህ ብይን አንድ ሰው ከሃይማኖታዊ ነፃነት ድንበር ሳይወጣ ከመንግሥት ይልቅ ‘ሃይማኖታዊ እምነቱ የሚጠይቀውን መታዘዝ’ እንደሚችል አመልክቷል።​—⁠8/15 ገጽ 8

ኢዮብ ሥቃይ የደረሰበት ለምን ያህል ጊዜ ነበር?

የኢዮብ መጽሐፍ ሥቃዩ ለብዙ ዓመታት ቀጥሎ እንደነበር አያመለክትም። በኢዮብ ላይ የደረሰው ሥቃይና ውጤቱ በጥቂት ወራት ውስጥ ምናልባትም ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ተከስተው ሊሆን ይችላል።​—⁠8/15 ገጽ 31

ዲያብሎስ አፈ ታሪክ የወለደው እንዳልሆነ እርግጠኛ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?

ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ዲያብሎስ በእውን ያለ መሆኑን ያውቅ ነበር። ኢየሱስ የተፈተነው በውስጡ ባለ አንድ ዓይነት ክፋት ሳይሆን በአንድ እውን አካል ነበር። (ማቴዎስ 4:​1-11፤ ዮሐንስ 8:​44፤ 14:​30)​—⁠9/1 ገጽ 5-6

ምሳሌ 10:​15 “የባለጠጋ ሀብት ለእርሱ የጸናች ከተማ ናት፤ የድሆች ጥፋት ድህነታቸው ነው” ይላል። ይህ እውነት ሆኖ የተገኘው እንዴት ነው?

በቅጥር የተከበበች ከተማ በውስጧ የሚኖሩ ሰዎች በተወሰነ መጠን ደኅንነት እንዲሰማቸው እንደምታደርግ ሁሉ ሃብትም በሕይወት ውስጥ ከሚያጋጥሙ ስጋቶች ሊያሳርፍ ይችላል። በሌላ በኩል ግን ድህነት ያልተጠበቁ ሁኔታዎች በሚከሰቱበት ጊዜ ለጥፋት ሊዳርግ ይችላል።​—⁠9/15 ገጽ 24

በሄኖስ ዘመን “በእግዚአብሔር [“በይሖዋ፣” NW ] ስም መጠራት ተጀመረ” የሚባለው ከምን አንጻር ነው? (ዘፍጥረት 4:​26)

ከሰው ልጅ ታሪክ መጀመሪያ አንስቶ አምላክን በስሙ መጥራት የተለመደ ነበር። ስለሆነም በሄኖስ ዘመን ተጀመረ የተባለው ይሖዋን በእምነት መጥራት አልነበረም። ሰዎች የአምላክን ስም በሚያረክስ መንገድ ለራሳቸው መጠሪያነት ተጠቅመውበት አሊያም ለአምልኮ ወደ አምላክ ያቀርቡናል ብለው ለሚያስቧቸው ሌሎች ሰዎች ይህን ስም አውጥተው ሊሆን ይችላል።​—⁠9/15 ገጽ 29

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሠራበት “ተግሣጽ” የሚለው ቃል ምን ማለት ነው?

ቃሉ የትኛውንም ዓይነት በደል ወይም የጭካኔ ድርጊት አያመለክትም። (ምሳሌ 4:​13፤ 22:​15) “ተግሣጽ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል በዋነኛነት የሚያመለክተው መመሪያ፣ ትምህርት፣ እርማትና አንዳንድ ጊዜም ጥብቅ ሆኖም በፍቅር ላይ የተመሠረተ ቅጣት መስጠትን ነው። ወላጆች የይሖዋን ምሳሌ መኮረጅ የሚችሉበት አንዱ ወሳኝ መንገድ ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን የሐሳብ ግንኙነት መስመር ክፍት ለማድረግ በመጣር ነው። (ዕብራውያን 12:​7-10)​—⁠10/1 ገጽ 8, 10

ዛሬ እውነተኛ ክርስቲያኖች የአምላክን አገዛዝ እንደሚደግፉ የሚያሳዩት እንዴት ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች የአምላክን መንግሥት የሚደግፉ በመሆናቸው እገዳ በተጣለባቸው አገሮች ውስጥ እንኳ ሳይቀር በፖለቲካ ጉዳይ ጣልቃ አይገቡም ወይም ደግሞ በመንግሥት ባለ ሥልጣኖች ላይ ዓመፅ አያነሳሱም። (ቲቶ 3:​1) ኢየሱስና የመጀመሪያው መቶ ዘመን ተከታዮቹ እንዳደረጉት ጠቃሚ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ሲሆን ሰዎች ሃቀኝነት፣ የሥነ ምግባር ንጽሕናና ጥሩ የሥራ ልማድ የመሳሰሉ ጤናማ ቅዱስ ጽሑፋዊ እሴቶችን በተግባር እንዲያውሉ ለመርዳት ይጥራሉ።​—⁠10/15 ገጽ 6

በአንዲስ ሕይወት ሰጪ ውኃ በመፍሰስ ላይ የሚገኘው እንዴት ነው?

በዚያ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች የአካባቢው ሕዝብ በሚግባባባቸው የኬችዋ እና የአይማራ ቋንቋዎች ሳይቀር በመጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለሰዎች ለማዳረስ ጥረት ያደርጋሉ። ምሥክሮቹ በውኃ ውስጥ የሚያድጉ መቃዎችን እርስ በርስ በማጠላለፍ በሚሠሩ “ተንሳፋፊ” ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ጨምሮ በሐይቁ ላይ በሚገኙ የቲቲካካ ደሴቶች ላይ የሚኖሩ ሰዎችን አነጋግረዋል።​—⁠10/15 ገጽ 8-10

አምላክ በዘመናዊ የመንገደኞች አውሮፕላን ላይ ከተገጠሙ የኮምፒውተር መመሪያዎች ጋር የሚመሳሰል ምን መምሪያ ሰጥቶናል?

አምላክ የሥነ ምግባር መመሪያ ማለትም ውስጣዊ የሥነ ምግባር ስሜት በመስጠት ሰዎችን አስታጥቋቸዋል። ይህም በውርስ ያገኘነው ሕሊና ነው። (ሮሜ 2:​14, 15)​—⁠11/1 ገጽ 3-4

የኢየሱስ ሞት ከፍተኛ ዋጋ የኖረው ለምንድን ነው?

ፍጹም ሰው የነበረው አዳም ኃጢአት ሲሠራ የራሱንም ሆነ የዘሮቹን ሰብዓዊ ሕይወት አሳጣ። (ሮሜ 5:​12) ኢየሱስ ፍጹም ሰው እንደመሆኑ መጠን ሰብዓዊ ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ በመስጠቱ ታማኝ የሆኑ ሰዎች የዘላለም ሕይወት እንዲያገኙ የሚያስችል ቤዛ አስገኝቶላቸዋል።​—⁠11/15 ገጽ 5-6

በቆላስይስ 3:​11 ላይ የተጠቀሱት እስኩቴሶች እነማን ነበሩ?

እስኩቴሶች ከ700 እስከ 300 ከዘአበ የዩራሲያ አውላላ ሜዳዎችን በቁጥጥራቸው ሥር አድርገው የኖሩ ዘላኖች ነበሩ። ስመ ጥር ፈረሰኞችና ጦረኞች ነበሩ። ቆላስይስ 3:​11 የሚያመለክተው በዚያ ስም የሚታወቅን አንድ ብሔር ሳይሆን በጭካኔያቸው የሚታወቁ ሰዎችን ሊሆን ይችላል።​—⁠11/15 ገጽ 24-5

ወርቃማው ሕግ ዘወትር ከሐሳባችን መውጣት የማይገባው ትምህርት ነው የምንለው ለምንድን ነው?

ይህ የግብረገብ እውነት በአይሁድ እምነት፣ በቡድሃ እምነት፣ በግሪክ ፍልስፍና እና በኮንፊሺያኒዝም ተብራርቷል። ይሁን እንጂ ኢየሱስ በተራራ ስብከቱ ላይ ያስተማረው ይህ ሕግ አዎንታዊ እርምጃዎችን መውሰድ የሚጠይቅና በየትኛውም ቦታና በማንኛውም ዘመን የኖሩ ሰዎችን ሕይወት የሚነካ ነው። (ማቴዎስ 7:​12)​—⁠12/1 ገጽ 3