በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ወላጆች የልጆቻችሁን ፍላጎት አሟሉ!

ወላጆች የልጆቻችሁን ፍላጎት አሟሉ!

ወላጆች የልጆቻችሁን ፍላጎት አሟሉ!

ልጆች፣ በተለይ ከወላጆቻቸው መመሪያና ፍቅራዊ ተግሳጽ ይሻሉ። በማስተማሩ መስክ የተሰማሩት ብራዚላዊቷ ታንየ ዛጉሪ እንዲህ ይላሉ:- “ሁሉም ልጆች የሚታያቸው ጨዋታ ብቻ በመሆኑ ገደብ ማበጀት ያስፈልጋል። ይህንን ማድረግ ያለባቸው ደግሞ ወላጆች ናቸው። ወላጆች ይህንን ካላደረጉ ልጆች ከቁጥጥር ውጭ ይሆናሉ።”

ይሁን እንጂ ለግል ነፃነት ከፍተኛ ግምት የሚሰጥ ልል ኅብረተሰብ ባለባቸው ብዙ አገሮች ከላይ የተሰጠውን ምክር ተግባራዊ ማድረጉ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ታዲያ ወላጆች እርዳታ ማግኘት የሚችሉት ከየት ነው? ፈሪሃ አምላክ ያላቸው ወላጆች ልጆች “የእግዚአብሔር ስጦታ” እንደሆኑ ይገነዘባሉ። (መዝሙር 127:3) ስለዚህም ልጆቻቸውን በማሳደግ ረገድ መመሪያ ለማግኘት የአምላክ ቃል ወደሆነው ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ዞር ይላሉ። ለምሳሌ ያህል ምሳሌ 13:24 እንዲህ ይላል:- “በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፤ ልጁን የሚወድድ ግን ተግቶ ይገሥጸዋል።”

“በትር” የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሠራበት አካላዊ ቅጣትን ለማመልከት ብቻ አይደለም። በተለያየ መልኩ የሚሰጠውንም እርማት ያመለክታል። አብዛኛውን ጊዜ የአንድን ልጅ አጓጉል አካሄድ ለማስተካከል የሚያስፈልገው የቃላት ተግሳጽ ብቻ ሊሆን ይችላል። ምሳሌ 29:17 “ልጅህን ቅጣ ዕረፍትንም ይሰጥሃል፤ ለነፍስህም ተድላን ይሰጣታል” ይላል።

ልጆች መጥፎ ባሕርያትን እንዲያስወግዱ ፍቅራዊ ተግሳጽ ያስፈልጋቸዋል። እንዲህ ዓይነቱ ጥብቅና በደግነት የተሰጠ እርማት አንድ ወላጅ ለልጁ ያለውን አሳቢነት የሚያሳይ ነው። (ምሳሌ 22:6) ስለዚህ ወላጆች ተስፋ አትቁረጡ! መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ገንቢና ተግባራዊ ምክር በመከተል ይሖዋ አምላክን ታስደስታላችሁ፣ ልጆቻችሁም ያከብሯችኋል።