በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሄንሪ ስምንተኛ እና መጽሐፍ ቅዱስ

ሄንሪ ስምንተኛ እና መጽሐፍ ቅዱስ

ሄንሪ ስምንተኛ እና መጽሐፍ ቅዱስ

ዊንስተን ቸርችል ሂስትሪ ኦቭ ዚ ኢንግሊሽ ስፒኪንግ ፒፕልስ (ጥራዝ 2) በተሰኘ መጽሐፋቸው ላይ የሚከተለውን ብለዋል:- “በሃይማኖት ረገድ የተደረገው ተሃድሶ ታላቅ ለውጥ አስከትሏል። በአሁኑ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ በብዙዎች ዘንድ አዲስ ተቀባይነትን ያገኘ የምክር መጽሐፍ ሆኗል። የቀድሞው ትውልድ መጽሐፍ ቅዱስ ባልተማሩ ሰዎች እጅ መግባቱ አደገኛ እንደሆነና መጽሐፉን ማንበብ ያለባቸው ቄሶች ብቻ እንደሆኑ አድርጎ ያምን ነበር።”

ታሪኩ እንዲህ በማለት ይቀጥላል:- “ቲንደልና ኮቨርዴል ወደ እንግሊዝኛ የተረጎሙትና በአሁኑ ጊዜ በበርካታ መጠን በመታተም ላይ ያለው ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ እይታ የበቃው በ1535 መከር መገባደጃ ላይ ሲሆን ቄሶች የመጽሐፍ ቅዱስን ንባብ እንዲያበረታቱ መንግሥት አሳስቧል።” እንግሊዝ ከብዙ ዓመታት የመጽሐፍ ቅዱስ መሃይምነት በኋላ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ለንጉሥ ሄንሪ ስምንተኛ መንግሥት ምስጋና ይግባውና ከመሃይምነት ልትላቀቅ ነው። a

“መንግሥት በፓሪስ ከፍተኛ መጠን ያለውና ከዚያ ቀደም ከነበሩት እትሞች ይበልጥ ጌጠኛ የሆነ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲታተም ማድረጉና መስከረም 1538 ደግሞ የየገዳማቱ ተሳላሚዎች ሊያነብቡትና በቀላሉ ሊጠቀሙበት የሚችሉት ትልቅ የእንግሊዝኛ እትም በየገዳማቱ እንዲቀመጥ ትእዛዝ መስጠቱ መጽሐፍ ቅዱስን በተመለከተ የቀድሞውን አመለካከት ለሚያራምዱት ሰዎች ተጨማሪ ራስ ምታት ሆኖባቸው ነበር። ለንደን ውስጥ በሚገኘው ቅዱስ ጳውሎስ ካቴድራል ስድስት ቅጂዎች የተቀመጡ ሲሆን በተለይ ጮክ ብሎ ማንበብ የሚችል ሰው ሲገኝ ካቴድራሉ ቅጂዎቹን ለማንበብ በመጡ ሰዎች ተጨናንቆ እንደሚውል ተነግሮናል።”

የሚያሳዝነው በተለያዩ አገሮች የሚኖሩ ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትረው አያነብቡም። ይህ በጣም አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ምክንያቱም ‘የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትና ለትምህርት፣ ለተግሣጽ፣ ልብንም ለማቅናት፣ በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ የሚጠቅመው’ መጽሐፍ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው።​—⁠2 ጢሞቴዎስ 3:​16

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ንጉሥ ሄንሪ ስምንተኛ እንግሊዝን ከ1509 እስከ 1547 ገዝቷል።

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

ሄንሪ ስምንተኛ:- Painting in the Royal Gallery at Kensington, from the book The History of Protestantism (Vol. I)