የመደብ ልዩነት የሌለበት ኅብረተሰብ መፍጠር ይቻል ይሆን?
የመደብ ልዩነት የሌለበት ኅብረተሰብ መፍጠር ይቻል ይሆን?
ከጊዜ በኋላ ሁለተኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የሆኑት ጆን አዳምስ “ሁሉም ሰው እኩል ሆኖ ተፈጥሯል፤ . . . እነዚህ ተጨባጭ ሐቆች ማስረጃ እንደማያስፈልጋቸው እናምናለን” የሚሉት የላቀ ግምት የሚሰጣቸው ቃላት የሚገኙበትን ታሪካዊ የነፃነት ድንጋጌ ከፈረሙት ሰዎች መካከል ይገኙበታል። የሆነ ሆኖ ጆን አዳምስ “በአእምሮና በአካል ረገድ የሚታየው መበላለጥ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ የሰውን ልጅ ሲፈጥር አብሮ የሠራው ነገር በመሆኑ የትኛውም ንድፍ ወይም ፖሊሲ ሊያስተካክለው አይችልም” ብለው መጻፋቸው ሰዎች በእርግጥ እኩል ናቸው በሚለው አባባል ላይ ጥርጣሬ እንዳደረባቸው የሚያሳይ ነው። ከዚህ በተቃራኒ ብሪታኒያዊው ታሪክ ጸሐፊ ኤች ጂ ዌልስ ሦስት ነገሮች ቢሟሉ ሰዎች ሁሉ እኩል የሚሆኑበትን ኅብረተሰብ መፍጠር ይቻላል ብለው ያስባሉ። እነርሱም ንጹሕና ያልተበረዘ ዓለም አቀፍ ሃይማኖት፣ ዓለም አቀፋዊ ትምህርትና የጦር ሠራዊት የሌለበት ዓለም ናቸው።
ዌልስ ያለሙት ዓለም በታሪክ እስከ አሁን ድረስ አልታየም። ሰዎች በእኩልነት መኖር አልቻሉም፤
እንዲሁም የመደብ ልዩነት አሁንም ድረስ ጎልቶ የሚታይ የኅብረተሰብ ገጽታ ነው። እንዲህ ያለው የመደብ ልዩነት ለኅብረተሰቡ ያመጣው አንዳች ጥቅም ይኖራልን? የለም። ማኅበራዊው የመደብ ሥርዓት ሰዎችን በመከፋፈል ምቀኝነትን፣ ጥላቻን፣ ሐዘንና ከፍተኛ ደም መፋሰስን አስከትሏል። በአንድ ወቅት በአፍሪካ፣ በአውስትራሊያና በደቡብ አሜሪካ ነግሦ የነበረው የነጭ የበላይነት አስተሳሰብ (አሁን ታዝማኒያ ተብላ በምትታወቀው) በቫን ዲያመንስ ምድር በሚኖሩ አቦርጂኖች ላይ የደረሰውን የዘር ማጥፋት እርምጃ ጨምሮ ነጭ ባልሆኑ ሰዎች ላይ መከራ አስከትሏል። በአውሮፓ አይሁዳውያንን የበታች አድርጎ መፈረጅ በጀርመን ለተከሰተው እልቂት መንገድ ጠርጓል። መሳፍንቱ ከፍተኛ ሀብት ማካበታቸውና ይህም በዝቅተኛና በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ በሚገኙ ሰዎች መካከል ቅሬታ መፍጠሩ በ18ኛው መቶ ዘመን ለፈነዳው የፈረንሳይ አብዮትና በ20ኛው መቶ ዘመን በሩሲያ ለፈነዳው የቦልሼቪክ አብዮት ዓብይ ምክንያት ሆነዋል።በጥንት ዘመን የኖረ አንድ ጠቢብ “ሰው ሰውን ለመጉዳት ገዢ የሚሆንበት ጊዜ አለ” በማለት ጽፎ ነበር። (መክብብ 8:9) ገዢዎቹ ግለሰቦችም ይሁኑ ቡድኖች እነዚህ ቃላት ትክክል ናቸው። አንድ ሕዝብ ራሱን በሌላው ላይ ከፍ ሲያደርግ ሥቃይና መከራ መከተሉ የማይቀር ነው።
በአምላክ ፊት ሁሉም እኩል ናቸው
አንዳንድ ቡድኖች የሌሎች የበላይ እንዲሆኑ ተደርገው ተፈጥረው ይሆን? በአምላክ ዘንድ ሁኔታው እንደዚያ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ “በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ [አምላክ] የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ” ይላል። (ሥራ 17:26) ከዚህም በተጨማሪ ፈጣሪ “እነርሱ ሁሉ የእጁ ሥራ ናቸውና በአለቆች ፊት አያደላም፣ ባለጠጋውንም ሰው ከድሀው ይበልጥ አይመለከትም።” (ኢዮብ 34:19) ሰዎች ሁሉ ከአንድ ዘር የመጡ ሲሆን ሲወለዱ በአምላክ ፊት ሁሉም እኩል ናቸው።
እንዲሁም አንድ ሰው ሲሞት ከሌሎች የላቀ ሆኖ እንዲታይ ያደረጉት ነገሮች ሁሉ አብረው እንደሚከስሙ አትዘንጋ። የጥንት ግብፃውያን በዚህ አያምኑም ነበር። አንድ ፈርዖን በሚሞትበት ጊዜ ከሞት በኋላ በሚያገኘው ሕይወት ሥልጣኑን ሲይዝ እንዲጠቀምባቸው በማሰብ በመቃብሩ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ዕቃዎች ያስቀምጡ ነበር። ዕቃዎቹን ተጠቅሞባቸው ይሆን? በፍጹም። አብሮት ከተቀበረው ሀብት መካከል አብዛኛው ለመቃብር ዘራፊዎች ሲሳይ ሲሆን ከዘረፋው የተረፉ ብዙዎቹ ዕቃዎች በአሁኑ ጊዜ በቤተ መዘክሮች ውስጥ ይገኛሉ።
ፈርዖኑ በድን ስለነበረ እነዚያን ውድ ዕቃዎች ሊጠቀምባቸው አልቻለም። በሞት ጊዜ ከፍተኛ ወይም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ወይም ሀብታምና ድሀ የሚባል ልዩነት አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ “ብልሃተኞች እንዲሞቱ፣ ሰነፎችና ደንቆሮች በአንድነት እንዲጠፉ፣ . . . አይቶአል። ሰው ግን . . . እንደሚጠፉ እንስሶች መሰለ” በማለት ይናገራል። (መዝሙር 49:10, 12) ነገሥታትም ሆንን ባሪያዎች “ሙታን ግን አንዳች አያውቁም . . . ከዚያ በኋላ ዋጋ የላቸውም። አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና” የሚሉት በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፉት ቃላት በሁላችንም ላይ ይሠራሉ።—መክብብ 9:5, 10
ስንወለድም ሆነ ስንሞት ሁላችንም በአምላክ ፊት እኩል ነን። በዚህ አጭር የሕይወት ቆይታችን ወቅት አንዱ ወገን ከሌላው እንደሚበልጥ አድርጎ ማሰብ ምንኛ ሞኝነት ነው!
የመደብ ልዩነት የማይኖርበት ኅብረተሰብ—እንዴት?
ይሁን እንጂ ወደፊት በውስጡ የመደብ ልዩነት የማይኖርበት ኅብረተሰብ ይመጣል ብሎ ለማሰብ የሚያበቃ ተስፋ ይኖር ይሆን? አዎን አለ። የዛሬ 2,000 ዓመት ገደማ ኢየሱስ ምድር ላይ ሳለ እንዲህ ያለውን ኅብረተሰብ ለማምጣት የሚያስችል መሠረት ተጥሏል። ኢየሱስ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ” ሕይወቱን ቤዛዊ መሥዋዕት አድርጎ ሰጥቷል።—ዮሐንስ 3:16
ኢየሱስ ተከታዮቹ አንዱ በሌላው ላይ ራሱን ከፍ ማድረግ እንደሌለበት ሲያሳስብ እንዲህ አለ:- “እናንተ ግን:- መምህር ተብላችሁ አትጠሩ፤ መምህራችሁ አንድ ስለ ሆነ እናንተም ሁላችሁ ወንድማማች ናችሁ። አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም:- አባት ብላችሁ አትጥሩ። ሊቃችሁ አንድ እርሱም ክርስቶስ ነውና:- ሊቃውንት ተብላችሁ አትጠሩ። ከእናንተም የሚበልጠው ማቴዎስ 23:8-12) የኢየሱስ እውነተኛ ደቀ መዛሙርት በሙሉ በአምላክ ፊት በእምነት እኩል ናቸው።
አገልጋያችሁ ይሆናል። ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል።” (የጥንቶቹ ክርስቲያኖች አንዳቸው ከሌላው ጋር እኩል እንደሆኑ ይሰማቸው ነበር? የኢየሱስ ትምህርት የገባቸው እንደዚያ ተሰምቷቸው ነበር። በእምነት አንዳቸው ከሌላው ጋር እኩል እንደሆኑ አድርገው ያስቡ የነበረ ሲሆን ይህንንም እርስ በርስ ‘ወንድም’ ብለው በመጠራራት አሳይተዋል። (ፊልሞና 1, 7, 20) ማንም ቢሆን ራሱን ከሌሎች የተሻለ እንደሆነ አድርጎ እንዲመለከት አይበረታታም። ለምሳሌ ያህል ጴጥሮስ ሁለተኛ መልእክቱን ሲጽፍ ራሱን በትህትና የገለጸበትን መንገድ ተመልከት:- “የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፣ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ።” (2 ጴጥሮስ 1:1) ጴጥሮስ ከኢየሱስ በቀጥታ የተማረ ሲሆን እንደ አንድ ሐዋርያ ሁሉ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ነበረው። ሆኖም ራሱን እንደ ባሪያ ከመቁጠሩም በላይ ሌሎች ክርስቲያኖች ከእርሱ ጋር የሚተካከል እምነት ማግኘታቸውን ተገንዝቦ ነበር።
አንዳንዶች በቅድመ ክርስትና ዘመን አምላክ እስራኤልን ለእርሱ የተለየ ብሔር አድርጎ መምረጡ ሰው ሁሉ እኩል ነው ከሚለው ሐሳብ ጋር ይጋጫል ይሉ ይሆናል። (ዘጸአት 19:5, 6) እንዲያውም ይህ የዘር የበላይነትን የሚያሳይ ምሳሌ ነው ይሉ ይሆናል። ሆኖም ሁኔታው እንደዚያ አይደለም። እስራኤላውያን የአብርሃም ዘር በመሆናቸው ምክንያት ከአምላክ ጋር ልዩ ዝምድና የነበራቸው ሲሆን መለኮታዊ ራእዮች የሚተላለፉበት መሥመር ሆነው አገልግለዋል። (ሮሜ 3:1, 2) ሆኖም የዚህ ዓላማ እነርሱን የሁሉም ቁንጮ ለማድረግ የታሰበ አልነበረም። ከዚያ ይልቅ ‘አሕዛብ ሁሉ እንዲባረኩ’ ለማድረግ ነበር።—ዘፍጥረት 22:18፤ ገላትያ 3:8
አብዛኞቹ እስራኤላውያን የአባታቸውን የአብርሃምን የእምነት ምሳሌ አልኮረጁም። ታማኝ ሳይሆኑ ከመቅረታቸውም በላይ ኢየሱስን አንደ መሲሕ አድርገው ሳይቀበሉ ቀሩ። በዚህም ምክንያት አምላክ ተዋቸው። (ማቴዎስ 21:43) ይሁን እንጂ ከሰው ልጆች መካከል ቅን የሆኑ ሰዎች ቃል የተገባውን በረከት ማግኘታቸው አልቀረም። በ33 እዘአ በጰንጠቆስጤ ዕለት የክርስቲያን ጉባኤ ተወለደ። በመንፈስ ቅዱስ የተቀቡ ሰዎችን ያቀፈው ይህ የክርስቲያኖች ድርጅት ‘የአምላክ እስራኤል’ ተብሎ የተጠራ ሲሆን ቃል የተገቡት በረከቶች የሚገኙበት መሥመር ለመሆን በቅቷል።—ገላትያ 6:16
የዚህ ጉባኤ አንዳንድ አባላት እኩልነትን በተመለከተ ተጨማሪ ትምህርት ማግኘት አስፈልጓቸው ነበር። ለምሳሌ ያህል ደቀ መዝሙሩ ያዕቆብ ሀብታም ክርስቲያኖችን ከድሆች አስበልጠው ያከብሩ የነበሩ ሰዎችን መክሯል። (ያዕቆብ 2:1-4) እንዲህ ማድረጋቸው ተገቢ አልነበረም። ሐዋርያው ጳውሎስ ከአሕዛብ የመጡ ክርስቲያኖች ከአይሁድ ክርስቲያኖች በምንም እንደማያንሱ እንዲሁም ሴት ክርስቲያኖች ከወንዶቹ በምንም እንደማያንሱ አመልክቷል። “በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤ ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና። አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፣ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፣ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና” በማለት ጽፏል።—ገላትያ 3:26-28
በዛሬው ጊዜ በመደብ ልዩነት ያልተከፋፈለ ሕዝብ
ዛሬ የይሖዋ ምሥክሮች በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ በሚገኙ መሠረታዊ ሥርዓቶች ለመመራት ይጥራሉ። ማኅበራዊ ልዩነቶች በአምላክ ፊት ትርጉም የለሽ መሆናቸውን ይገነዘባሉ። በመሆኑም ቀሳውስትና ምዕመናን በማለት አይከፋፈሉም። እንዲሁም በቆዳ ቀለም ወይም 1 ዮሐንስ 2:15-17 NW ) ከዚህ ይልቅ ሁሉም በአጽናፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ገዢ በይሖዋ አምላክ አምልኮ የተባበሩ ናቸው።
በሀብት እርስ በርስ አይከፋፈሉም። ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ሀብታሞች ቢሆኑ እንኳ እንዲህ ያሉ ነገሮች ኃላፊ መሆናቸውን ስለሚገነዘቡ ‘ያለኝ ይታይልኝ የሚል መንፈስ’ ለማሳየት አይሞክሩም። (እያንዳንዱ ምሥክር የመንግሥቱን ምሥራች ለሌሎች ሰዎች በመስበኩ ሥራ የመካፈል ኃላፊነት ተቀብሏል። ልክ እንደ ኢየሱስ በግፍ የተደቆሱትን እንዲሁም ዞር ብሎ የሚያይ ጠያቂ የሌላቸውን ሰዎች እቤታቸው ድረስ ሄደው በማነጋገርና የአምላክን ቃል እንዲያጠኑ በመጋበዝ ያከብሯቸዋል። ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያላቸው ሰዎች በሌሎች ዘንድ ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ እንዳላቸው ከሚነገርላቸው ሰዎች ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው ይሠራሉ። ትልቅ ግምት የሚሰጠው ለመንፈሳዊ ባሕርያት እንጂ በኅብረተሰቡ ውስጥ ላለን ቦታ አይደለም። እንደ መጀመሪያው መቶ ዘመን ሁሉም በእምነት ወንድማማቾችና እህትማማቾች ናቸው።
እኩልነት ሲባል አንድ ዓይነት መሆን ማለት አይደለም
እርግጥ ነው እኩልነት ሲባል በሁሉም ነገር አንድ ዓይነት መሆን ማለት አይደለም። ከብዙ ዓይነት ዘር፣ ቋንቋ፣ ብሔርና የኢኮኖሚ ሁኔታ የመጡ ሰዎችን ያቀፈው ይህ ክርስቲያናዊ ድርጅት ወንዶችና ሴቶች፣ አዛውንቶችና ወጣቶች ይገኙበታል። በግለሰብ ደረጃ ሁሉም የየራሳቸው አእምሯዊና አካላዊ ችሎታ አላቸው። ሆኖም እንዲህ ያለው የችሎታ መለያየት አንዱን የበላይ ሌላውን የበታች አያደርገውም። ከዚህ ይልቅ አስደሳች የዓይነት ልዩነት ይፈጥራል። እነዚህ ክርስቲያኖች ያላቸው ማንኛውም ዓይነት ተሰጥዖ ከአምላክ ያገኙት ስጦታ እንደሆነ አድርገው የሚመለከቱት ከመሆኑም በላይ ከሌሎች እንደሚበልጡ ለማሰብ ምክንያት እንደማይሆናቸውም ይገነዘባሉ።
የመደብ ክፍፍል ሰው የአምላክን መመሪያ ከመከተል ይልቅ ራሱን በራሱ ለመምራት ያደረገው ሙከራ ውጤት ነው። በቅርቡ የአምላክ መንግሥት የምድርን የዕለት ተዕለት አገዛዝ ስለሚረከብ ላለፉት ዘመናት ሁሉ ሥቃይና መከራ እንዲኖር ያደረጉትን ነገሮች ጨምሮ ሰው ሠራሽ የመደብ ልዩነቶች ይወገዳሉ። ከዚያም ‘ገሮች ምድርን ይወርሳሉ’ የሚለው ትንቢት ቃል በቃል ይፈጸማል። (መዝሙር 37:11) አንድ ሰው የበላይ እንደሆነ እንዲሰማው የሚያደርጉት ነገሮች በሙሉ ይወገዳሉ። ከዚያ በኋላ ማኅበራዊ የመደብ ልዩነቶች የሰውን ዘር ዓለም አቀፋዊ የወንድማማችነት ማኅበር እንዲከፋፍሉ ፈጽሞ አይፈቀድላቸውም።
[በገጽ 5 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ፈጣሪ “ሁሉ የእጁ ሥራ ናቸውና . . . ባለጠጋውንም ሰው ከድሀው ይበልጥ አይመለከትም።”—ኢዮብ 34:19
[በገጽ 6 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
የይሖዋ ምሥክሮች ጎረቤቶቻቸውን ያከብራሉ
[በገጽ 7 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
በእውነተኛ ክርስቲያኖች ዘንድ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ለመንፈሳዊ ባሕርያት ነው