“የሚያነባው” ዛፍና ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ያለው “እንባው”
“የሚያነባው” ዛፍና ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ያለው “እንባው”
ኤርምያስ 51:8 NW ‘ለሕመሟ የበለሳን ዘይት ውሰዱላት’ በማለት ይናገራል። ከፍተኛ የማስታገሥና የመፈወስ ኃይል ያለው የዚህ ንጥረ ነገር ምንጭ ከሆኑት ተክሎች መካከል አንደኛውን ለማግኘት የምናደርገው ፍለጋ በኤጅየን ባሕር ወደምትገኘው የካየስ ደሴት ይመራናል።
በበጋ ወራት መጀመሪያ ላይ የካየስ ገበሬዎች ምርታቸውን ለመሰብሰብ የሚያደርጉት ዝግጅት ለየት ያለ ነው። ማስቲክ በመባል በሚታወቀው ልምላሜው የማይረግፍ ቁጥቋጦ መሰል ዛፍ ሥር ያለውን መሬት ጠርገው ከደለደሉ በኋላ ነጭ ሸክላ ይለቀልቁታል። ከዚያም ቅርፊቶቹን በመብጣት ዛፎቹን “እንዲያነቡ” ያደርጓቸዋል። በዚህ ጊዜ የገረጣ ቀለም ያለው የሙጫ “እንባ” መፍሰስ ይጀምራል። ከሁለት ወይም ከሦስት ሳምንታት በኋላ ጠብታዎቹ ስለሚረጉ ገበሬዎቹ እነዚህን የረጉ ጠብታዎች በቀጥታ ከግንዱ አሊያም ነጭ ሸክላ ከተለቀለቀው ወለል ላይ ይሰበስቧቸዋል። ጋም ማስቲክ የሚባለው ይህ የዛፍ “እንባ” የበለሳን ዘይት ለመሥራት ሲያገለግል ቆይቷል።
ይሁን እንጂ በመጨረሻ ምርቱን ለመሰብሰብ ከፍተኛ ትዕግሥትና ብዙ ድካም ይጠይቃል። ጠመዝማዛዎቹና ግራጫ ቀለም ያላቸው የዛፍ ግንዶች እድገታቸው በጣም አዝጋሚ ሲሆን አንድ ዛፍ ሙሉ እድገቱን ለመጨረስ ማለትም ከ2 እስከ 3 ሜትር ለመድረስ ከ40 እስከ 50 ዓመት ይወስድበታል።
ግንዶቹን ከመቁረጥና “እንባውን” ከመሰብሰብ በተጨማሪ ማስቲክ ለመሥራት ሌላም ነገር መከናወን ይኖርበታል። ገበሬዎቹ “እንባውን” በወንፊት ከነፉና ካጠቡት በኋላ በመጠንና በጥራቱ ይለዩታል። ከጊዜ በኋላ ተጨማሪ ማስቲኩን የማጥራት ሥራ ከተከናወነ በኋላ ብዙ ጥቅም ላይ ለመዋል ዝግጁ ይሆናል።
የዚህ ልዩ ተክል ታሪክ
“ማስቲክ” የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል “ጥርስ ማፋጨት” የሚል ትርጉም ካለው የግሪክኛ ቃል የመጣ ነው። (ማቴዎስ 8:12፤ ራእይ 16:10) ይህ ስም እንደሚያሳየው በጥንት ጊዜ የማስቲክ ሙጫ ለጥሩ የአፍ ጠረን ሲባል ይታኘክ ነበር።
ማስቲክ ተጠቅሶ ከሚገኝባቸው ምንጮች ሁሉ ጥንታዊ ነው የሚባለው የ5ኛው መቶ ዘመን የግሪክ ታሪክ ጸሐፊ የሆነው ሄሮዶተስ ሲሆን አፐሎዶሮስ፣ ዲስኮረዲስ፣ ቲየፍራስተስ፣ ሂፖክራተስን ጨምሮ ሌሎች የጥንት ጸሐፊዎችና ሐኪሞችም ማስቲክ በሕክምናው ዘርፍ የሚጫወተውን ሚና በማስመልከት ጽፈዋል። የማስቲክ ዛፎች በመላው የሜዲትራንያን ባሕር ዳርቻ የሚበቅሉ ቢሆንም ከ50 እዘአ ገደማ ጀምሮ የማስቲክ ምርት በካየስ ብቻ ማለት ይቻላል ተወስኖ ቆይቷል። እንዲሁም ሮማውያን፣ የጀነዋ ሰዎችና የኦቶማን ቱርኮች ካየስን ለመውረር በዋነኛነት ያነሳሳቸው የማስቲክ ምርት ነበር።
ባለ ዘርፈ ብዙ ጥቅሙ ማስቲክ
የጥንት ግብፃውያን ሐኪሞች ተቅማጥንና አርትራይተስን ጨምሮ ሌሎች ልዩ ልዩ በሽታዎችን ለማከም በማስቲክ ይጠቀሙ ነበር። ለዕጣንነትና ሬሳን ለማድረቅም ይጠቀሙበት ነበር። ምናልባትም የማስቲክ ዛፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የመድኃኒትነት ባሕርይ እንዳለውና ለመዋቢያነት ኤርምያስ 8:22 NW ፤ 46:11 NW ) እንዲያውም ለቅዱስ አገልግሎት ብቻ የተወሰነ ጣፋጭ መዓዛ ያለው ዕጣን ለመሥራት ከሚደባለቁት ንጥረ ነገሮች አንዱ የሆነውን ዓይነት ሙጫ የሚያወጣው ዛፍም የማስቲክ ዛፍ ዝርያ ሊሆን እንደሚችል አስተያየት ተሰንዝሯል።—ዘጸአት 30:34, 35
ብሎም ለሽቶ መቀመሚያነት እንደሚያገለግል የተነገረለት ‘የገለዓድ የበለሳን ዘይት’ ምንጭ ሊሆን ይችላል። (በዛሬው ጊዜ ማስቲክ የዘይት ቀለሞችን፣ የቤት እቃዎችንና የሙዚቃ መሣሪያዎችን ከብልሽት ለመጠበቅ በሚቀቡ ቫርኒሾች ውስጥ ይገኛል። ኤሌክትሪክ የማያስተላልፍና ውኃ የማያሳልፍ ቁስ ሆኖ የሚያገለግል ከመሆኑም ሌላ ለልብስ ማቅለሚያነትም ሆነ ለሥዕል የሚያገለግሉ ቀለሞች ተጠብቀው እንዲቆዩ በማድረግ ረገድ ተመራጭ ነው። ማስቲክ ለማጣበቂያነትና ለቆዳ ማለስለሻነት ያገለግላል። ከጣፋጭ መዓዛውና ከሌሎች ባሕርያቱ የተነሣ ማስቲክ ለሳሙናዎች፣ ለመዋቢያዎችና ለሽቶዎች መሥሪያነት ያገለግላል።
ማስቲክ በዓለም ዙሪያ በሚሠራባቸው 25 ኦፊሴላዊ የመድኃኒት ዝርዝሮች ውስጥ ተካትቷል። በአረቡ ዓለም ደግሞ አሁንም በአብዛኛው በባሕላዊ መድኃኒትነት ያገለግላል። ማስቲክ የተቦረቦረን ጥርስ መሙያ ንጥረ ነገርና የመድኃኒት መያዣ ፕላስቲኮችን (capsule) ውስጠኛ ግድግዳዎች ለመሥራትም ያገለግላል።
የበለሳን ዘይት ምንጭ የሆነው “የሚያነባው” የማስቲክ ዛፍ “እንባ” ለበርካታ መቶ ዓመታት በሥቃይ ማስታገሻነትና በፈዋሽ መድኃኒትነት ሲያገለግል ቆይቷል። እንግዲያው የኤርምያስ ትንቢት ‘ለሕመሟ የበለሳን ዘይት ውሰዱላት’ ማለቱ ያለ ምክንያት አይደለም።
[በገጽ 31 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ካየስ
የማስቲክ ምርት መሰብሰብ
የማስቲክ “እንባ ” የሚሰበሰበው በጥንቃቄ ነው
[ምንጭ]
Chios and harvest line art: Courtesy of Korais Library; all others: Kostas Stamoulis