በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ንጹሕ ሕሊና ለማግኘት የሚከፈለው ዋጋ ምን ያህል ነው?

ንጹሕ ሕሊና ለማግኘት የሚከፈለው ዋጋ ምን ያህል ነው?

ንጹሕ ሕሊና ለማግኘት የሚከፈለው ዋጋ ምን ያህል ነው?

“መንግሥት 20, 000 የብራዚል ሪል እንዲቀበል ታዘዘ።” ይህ እንግዳ የሆነ ርዕሰ ዜና በቅርቡ ኮራዩ ዶ ፖቮ በተሰኘ አንድ የብራዚል ጋዜጣ ላይ ወጥቶ ነበር። ዘገባው መሬቱን ለመንግሥት ስለሸጠ ሉዌዝ አልቮ ዴ አራውዞ ስለሚባል አንድ ፖስታ አመላላሽ ይገልጻል። የንብረት ባለቤትነቱን ለመንግሥት ካዛወረ በኋላ ከተስማሙበት ዋጋ በ20,000 ሪል (ወደ 8, 000 የአሜሪካን ዶላር ይጠጋል) የሚበልጥ ገንዘብ እንደተከፈለው ተገነዘበ!

ይሁን እንጂ ትርፉን ገንዘብ መመለስ ቀላል አልነበረም። ለበርካታ ጊዜያት ወደ መስተዳድሩ ቢሮ ከተመላለሰ በኋላ ጠበቃ ቀጥሮ ጉዳዩን በፍርድ ቤት እንዲከታተል ተነገረው። “አንድ ሰው ስህተት የሠራ ይመስላል። መሥሪያ ቤቱ ውስጥ በሚታየው ቢሮክራሲያዊ አሠራር ምክንያት ችግሩን እንዴት መፍታት እንደሚቻል የሚያውቅ የለም” በማለት መንግሥት ገንዘቡን እንዲቀበልና ግለሰቡ ለፍርድ ቤት ያወጣውን ወጪ እንዲሸፍን የፈረዱት ዳኛ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። “እንዲህ ያለ ጉዳይ ሲያጋጥመኝ ይህ የመጀመሪያዬ ነው።”

የይሖዋ ምሥክር የሆነው ሉዌዝ እንዲህ በማለት ይገልጻል:- “በመጽሐፍ ቅዱስ የሰለጠነው ሕሊናዬ የራሴ ያልሆነውን እንድወስድ አይፈቅድልኝም። ገንዘቡን መመለስ ነበረብኝ።”

እንዲህ ያለው ዝንባሌ ለብዙዎች እንግዳ ብሎም ፈጽሞ የማይመስል ነገር ነው። ይሁን እንጂ የአምላክ ቃል እውነተኛ ክርስቲያኖች ከዓለማዊ ባለ ሥልጣናት ጋር ባላቸው ግንኙነት ረገድ ንጹሕ ሕሊና ይዞ መመላለስን ከፍ አድርገው እንደሚመለከቱት ያሳያል። (ሮሜ 13:​5 NW ) የይሖዋ ምሥክሮች ‘በንጹሕ ሕሊናና በሃቀኝነት ለመኖር’ ቁርጥ ውሳኔ አድርገዋል።​—⁠ዕብራውያን 13:​18 NW