በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሙሉ በሙሉ የጠፋ ዓለም!

ሙሉ በሙሉ የጠፋ ዓለም!

ሙሉ በሙሉ የጠፋ ዓለም!

እስቲ በከተሞች፣ በተለያዩ ባሕሎች፣ በሳይንሳዊ ግኝቶችና በቢልዮን በሚቆጠሩ ሰዎች የተሞላውን

በዙሪያህ ያለውን ዓለም ተመልከት። ዘላቂ የሚመስለው ገጽታው በቀላሉ ሊማርከን ይችላል። አይደለም እንዴ?

ይህ ዓለም አንድ ቀን ሙሉ በሙሉ ይጠፋል ብለህ ታስባለህ? ይህ ለማሰብ እንኳ የሚከብድ ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ አስተማማኝ ከሆነ ምንጭ በተገኘ መረጃ መሠረት ከዚህ በፊት አንድ ዓለም እንደነበረና ይህም ዓለም ሙሉ በሙሉ እንደጠፋስ ታውቃለህ?

እየተናገርን ያለነው በሥልጣኔ ኋላ ቀር ስለነበረ ዓለም አይደለም። ከዚህ በፊት የጠፋው ዓለም ከተሞች፣ ሥነ ጥበባዊ ግኝቶችና ሳይንሳዊ እውቀት የነበሩት የሰለጠነ ዓለም ነው። ይሁን እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ እንደሚነግረን በ2ኛው ወር ከወሩም በ17ኛው ዕለት ፓትርያርኩ አብርሃም ከመወለዱ 352 ዓመታት ቀደም ብሎ የጥፋት ውኃ መጥቶ መላውን ዓለም ጠራርጎ አጠፋ። a

ይህ ዘገባ ትክክል ነው? እንዲህ ያለው ነገር በእርግጥ ተፈጽሟል? አሁን ካለው ዓለም በፊት በእርግጥ የበለጸገና በኋላም የጠፋ ጥንታዊ ዓለም ነበረን? ከነበረስ ለምን ጠፋ? ችግሩ ምን ነበር? ከደረሰበት ጥፋት እኛ ልናገኝ የምንችለው ትምህርትስ ይኖራል?

በእርግጥ ከዚህ በፊት የነበረ ጥንታዊ ዓለም ጠፍቷልን?

እንዲህ ያለው እንግዳ ክስተት በእርግጥ ደርሶ ከሆነ ፈጽሞ የሚረሳ አይሆንም። እንዲያውም ብዙ አገሮች ይህን ጥፋት የሚ​ያወሱ ታሪኮች አሏቸው። ለምሳሌ ያህል በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ተመዝግቦ የሚገኘውን ትክክለኛ ቀን ተመልከት። በጥንቱ የቀን መቁጠሪያ መሠረት ሁለተኛው ወር አሁን እኛ ከጥቅምት አጋማሽ እስከ ኅዳር አጋማሽ ብለን ከምንጠራው ጋር እኩል ነው። ስለዚህ 17ኛው ቀን ኅዳር መግቢያ ላይ ይውላል ማለት ነው። ስለዚህ በብዙ አገሮች ሙታንን የሚያስታውሱ በዓሎች በዚህ ወቅት መከበራቸው እንዲያው በአጋጣሚ የሆነ ነገር አይደለም።

የጥፋት ውኃ እንደደረሰ የሚያረጋግጡትን ሌሎች ማስረጃዎች ደግሞ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ በቆዩ ባሕሎች ውስጥ ማግኘት ይቻላል። እያንዳንዱ ባሕል ለማለት ይቻላል የቀድሞ አባቶቻቸው ከዓለም አቀፉ የጥፋት ውኃ በሕይወት እንደተረፉ የሚገልጹ አፈ ታሪኮች አሉት። ጥቂቱን ለመጥቀስ ያህል በአላስካ፣ በአውስትራሊያ፣ በቻይና፣ በህንድ፣ በሊቱዋኒያ፣ በሚክሲኮ፣ በማይክሮኔዥያ፣ በኒው ዚላንድና በአንዳንድ የሰሜን አሜሪካ አገሮች የሚኖሩትን ሕዝቦች ጨምሮ የአውሮፓ ሴልቶች፣ የአፍሪካ ፒግሚዎችና የደቡብ አሜሪካ ኢንካዎች ሁሉም ተመሳሳይ አፈ ታሪኮች አሏቸው።

እርግጥ ነው ጊዜ እያለፈ ሲሄድ አፈ ታሪኮቹ ተቀባብተው ቢቀርቡም ሁሉም በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ያተኮሩ ዝርዝር ሐሳቦች ይዘዋል። ከእነዚህም ውስጥ አምላክ በሰዎች ኃጢአት እንደተቆጣ፣ ከባድ የጎርፍ መጥለቅለቅ እንደደረሰ፣ መላው የሰው ዘር እንደተደመሰሰ፣ ጥቂት ጻድቃን በሕይወት እንደተረፉ፣ እነዚህም ሰዎችና እንስሳት የሚተርፉበትን መርከብ እንደሠሩ፣ ከጊዜ በኋላ ደረቅ ምድር ለመፈለግ ወፎች እንደተላኩ፣ በመጨረሻም መርከቡ በአንድ ተራራ ላይ እንዳረፈና ከጥፋቱ የተረፉት ከመርከቡ ወጥተው መሥዋዕት እንዳቀረቡ የሚገልጹ ሐሳቦች ይገኙበታል።

ታዲያ ይህ ምን ያረጋግጣል? እንዲህ ያለው ተመሳሳይነት እንዲያው የአጋጣሚ ጉዳይ ሊሆን አይችልም። እነዚህ የአፈ ታሪክ ማስረጃዎች ተዳምረው ሁሉም ሰው መላውን የሰው ዘር ከደመሰሰው የጥፋት ውኃ ተራፊዎች የመጣ ነው የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥንታዊ ዘገባ ያረጋግጣሉ። ሆኖም የተፈጠረውን ሁኔታ በትክክል ለማወቅ በአፈ ታሪኮች አሊያም በተረቶች ላይ መደገፍ አይኖርብንም። በዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ በጥንቃቄ ተጠብቆ የቆየ ዘገባ አለልን።​—⁠ዘፍጥረት ምዕራፍ 6-8

መጽሐፍ ቅዱስ ሕይወት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ያለውን ታሪክ የሚገልጽ በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ ዘገባ ይዟል። ይሁን እንጂ ማስረጃዎቹ እንደሚያሳዩት የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ እንዲያው ታሪክ ብቻ አይደለም። መሬት ጠብ የማይለው ትንቢቱና ጥልቅ ጥበቡ መጽሐፉ ራሱ እንደሚለው አምላክ ከሰው ጋር የሐሳብ ግንኙነት የሚያደርግበት መስመር እንደሆነ ያመለክታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ከአፈ ታሪክ በተለየ በታሪካዊ ዘገባዎቹ ውስጥ የዘር ግንድንና የቦታ ዝርዝሮችን ጨምሮ ስሞችንና ቀናትን በትክክል ይገልጻል። ከጥፋት ውኃው በፊት ሕይወት ምን ይመስል እንደነበረና መላው ዓለም በድንገት ሊጠፋ የቻለው ለምን እንደሆነ በግልጽ ይነግረናል።

የዚያ ከጥፋት ውኃ በፊት የነበረ ኅብረተሰብ ችግር ምን ነበር? የሚቀጥለው ርዕስ ይህንን ጥያቄ ይመልሳል። የዓለማችን የወደፊት ዕጣ ምን ያህል ያስተማምናል ብለው ለሚያስቡ ሰዎች ይህ ጠቃሚ ጥያቄ ነው።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ የግርጌ ማስታወሻ]

[በገጽ 4 ላይ የሚገኝ ግራፍ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

በዓለም ዙሪያ ስለ ጥፋት ውኃ የሚናገሩ አፈ ታሪኮች

አገር ተመሳሳይነት 1 2 3 4 5 6 7 8 9 10

ግሪክ 7 ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆

ሮም 6 ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆

ሊቱዋኒያ 6 ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆

አሦር 9 ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆

ታንዛኒያ 7 ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆

ህንድ - ሂንዱ 6 ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆

ኒው ዚላንድ - ማኦሪ 5 ◆ ◆ ◆ ◆ ◆

ማይክሮኔዥያ 7 ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆

ዋሽንግተን ዩ ኤስ ኤ - ያኪማ 7 ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆

ሚሲሲፒ ዩ ኤስ ኤ - ቾክታው7 ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆

ሜክሲኮ - ሚኮአካን 5 ◆ ◆ ◆ ◆ ◆

ደቡብ አሜሪካ - ኬችዋ 4 ◆ ◆ ◆ ◆

ቦሊቪያ - ቺሪጉዋኖ 5 ◆ ◆ ◆ ◆ ◆

ጉያና - አራዋክ 6 ◆ ◆ ◆ ◆ ◆ ◆

1: አምላክ ከክፋት የተነሣ ተቆጣ

2: በውኃ ጠፋ

3: በአምላክ ታዘዘ

4: መለኮታዊ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

5: ጥቂት ሰዎች ተረፉ

6: በመርከብ ውስጥ ዳኑ

7: እንስሳት ዳኑ

8: ወፍ ወይም ሌላ ፍጡር ተላከ

9: በመጨረሻ ተራራ ላይ አረፈ

10: ከመርከብ ሲወጡ መሥዋዕት አቀረቡ