በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ክንውን

በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ክንውን

በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ክንውን

ይህ ክንውን የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ነው። ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ለምንድን ነው? ይህ የሆነው በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ነው።

ኢየሱስ እስከ ሞት ድረስ ታማኝ መሆኑ ሰዎች ለአምላክ ፍጹም አቋማቸውን መጠበቅ እንደሚችሉ ያረጋግጣል።

የክርስቶስ ሞት ለአንዳንዶች በሰማይ ከኢየሱስ ጋር ተባባሪ ገዥዎች የመሆን መብት አስገኝቶላቸዋል። እንዲሁም ለብዙዎች ገነት በምትሆነው ምድር ላይ የዘላለም ሕይወት ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ ከፍቶላቸዋል።

ኢየሱስ በሞቱ ዋዜማ ምሽት ላይ በፍቅር ተነሳስቶ የሚያቀርበውን ሰብዓዊ መሥዋዕት ለማመልከት ያልቦካ ቂጣ እና ቀይ የወይን ጠጅ ተጠቀመ። ከዚያም ደቀ መዛሙርቱን “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አላቸው። (ሉቃስ 22:​19) አንተስ ይህን ታላቅ ክንውን አስበህ ትውላለህ?

የይሖዋ ምሥክሮች በኢየሱስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ አብረሃቸው እንድትገኝ በአክብሮት ይጋብዙሃል። በዚህ ዓመት በዓሉ የሚከበረው መጋቢት 28 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር መጋቢት 19) ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይሆናል። ለቤትህ ቅርብ በሆነ በአንዱ የመንግሥት አዳራሽ ላይ መገኘት ትችላለህ። በዓሉ የሚከበርበትን ትክክለኛ ሰዓትና ቦታ ለማወቅ ከፈለግህ በአቅራቢያህ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮችን አነጋግራቸው።