በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ወደ ጥልቁ ወረዱ”

“ወደ ጥልቁ ወረዱ”

“ወደ ጥልቁ ወረዱ”

“ቀላያትንም ለበሱ፤ እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቁ ወረዱ።”

ሙሴና አብረውት የነበሩት እስራኤላውያን ቀይ ባህርን አቋርጠው ነፃ በመውጣታቸውና እያሳደዷቸው የነበሩት ግብጻውያን ጠላቶቻቸው ፈርዖንና ሠራዊቱ ድምጥማጣቸው በመጥፋቱ የተሰማቸውን ደስታ ከላይ ያሉትን ቃላት በመጠቀም በመዝሙር ገልጸዋል።​—⁠ዘጸአት 15:​4, 5 አ.መ.ት 

ያንን አስደናቂ ክስተት ለተመለከተ ሰው መልእክቱ ግልጽ ነበር። የይሖዋን ሥልጣን የተገዳደረ ወይም የተቃወመ ማንኛውም ሰው ተሳክቶለት በሕይወት ሊኖር አይችልም። ይሁን እንጂ ከጥቂት ወራት በኋላ አንጋፋ የሆኑት እስራኤላውያን ማለ​ትም ቆሬ፣ ዳታን፣ አቤሮንና 250 ደጋፊዎቻቸው አምላክ ለሙሴና ለአሮን የሰጣቸውን ሥልጣን በይፋ ተገዳደሩ።​—⁠ዘኁልቊ 16:1-3

ሙሴ በይሖዋ በመመራት እስራኤላውያን ከዓመፀኞቹ ድንኳኖች ዘወር እንዲሉ አስጠነቀቀ። ዳታንና አቤሮን ግን በቤተሰቦቻቸው አባላት እየተደገፉ አመለካከታቸውን ለማስተካከል አሻፈረን አሉ። በዚህ ጊዜ ሙሴ ይሖዋ በራሱ መንገድ እነዚህ ሰዎች “እግዚአብሔርን እንደ ናቁ” ለሕዝቡ እንደሚያሳውቅ ተናገረ። በዚህ ጊዜ ይሖዋ ከእግራቸው ሥር ያለውን መሬት ሰነጠቀው። “እነርሱም ለእነርሱም የነበሩ ሁሉ በሕይወታቸው ወደ ሲኦል ወረዱ፤ ምድሪቱም ተዘጋችባቸው።” ቆሬና ሌሎቹ ዓመፀኞችስ? “እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጥታ ያጥኑ የነበሩትን ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች በላች።”​—⁠ዘኁልቊ 16:23-35፤ 26:​10

ፈርዖንና ሠራዊቱም ሆኑ በምድረ በዳ ያመፁት ሰዎች ሊጠፉ የቻሉት የይሖዋን ሥልጣን አንቀበልም በማለታቸውና ሕዝቡን ለሚመለከቱ ጉዳዮች ትኩረት እንደሚሰጥ ሳይገነዘቡ በመቅረታቸው ነው። እንግዲያው በእነዚህ አስጨናቂ ጊዜያት የይሖዋን ጥበቃ ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ስለ ይሖዋ መማርና እሱን እንደ “ልዑል” እና ‘ሁሉን ቻይ አምላክ’ አድርገው መታዘዛቸው አጣዳፊ ነው። እንደዚያ ካደረጉ በሚከተሉት የይሖዋ ቃላት ሊበረታቱ ይችላሉ:- “በአጠገብህ ሺህ፣ በቀኝህም አሥር ሺህ ይወድቃል፤ ወደ አንተ ግን አይቀርብም። በዐይንህ ብቻ ትመለከታለህ፤ የክፉዎችንም መቀጣት ታያለህ። እግዚአብሔርን መሸሸጊያ፣ ልዑልንም መጠጊያህ አድርገኸዋልና።”​—⁠መዝሙር 91:1, 7-9 አ.መ.ት