በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ፈጽሞ ባልተጠበቀ ቦታ እውነትን ማግኘት

ፈጽሞ ባልተጠበቀ ቦታ እውነትን ማግኘት

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

ፈጽሞ ባልተጠበቀ ቦታ እውነትን ማግኘት

የአምላክ ፈቃድ “ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ” ነው። (1 ጢሞቴዎስ 2:3, 4 አ.መ.ት ) ይህንን ዓላማ ዳር ለማድረስ የይሖዋ ምሥክሮች በሚልዮን የሚቆጠሩ መጽሐፍ ቅዱሶችንና መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት የሚረዱ ጽሑፎችን እያተሙ ሲያሰራጩ ቆይተዋል። አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ጽሑፎች ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ፈጽሞ ባልተጠበቀ መንገድ እውነትን እንዲማሩ አስችለዋል። በዚህ ረገድ በፍሪታውን፣ ሴራሊዮን የሚገኙት የመን​ግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች የሚከተለውን ተሞክሮ ሪፖርት አድርገዋል።

ኡስማን ዘጠኝ ልጆች ባሉበት ቤተሰብ ውስጥ ሁለተኛው ልጅ ነው። ሃይማኖተኛ በሆነ ቤተሰብ ውስጥ በማደጉ ከአባቱ ጋር አዘውትሮ ወደ አምልኮ ቦታ ይሄድ ነበር። ይሁን እንጂ ኡስማን ሃይማኖቱ ስለ ሲኦል የሚያስተምረው ነገር በጣም ይረብሸው ነበር። መሐሪ የሆነ አምላክ ክፉ ሰዎችን በእሳት በማቃጠል የሚያሠቃይበት ምክንያት ሊገባው አልቻለም። የእሳታማ ሲኦል መሠረተ ትምህርት እንዲገባው ለማድረግ የቀረቡለት ማብራሪያዎች ሁሉ የአእምሮ ሰላም ሊሰጡት አልቻሉም።

አንድ ቀን ኡስማን 20 ዓመት ሆኖት እያለ በአንድ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ በከፊል በቆሻሻ የተሸፈነ ሰማያዊ መጽሐፍ ተመለከተ። መጻሕፍት ስለሚወድ መጽሐፉን አነሳና ቆሻሻውን ካጸዳ በኋላ ርዕሱን ተመለከተው። ወደ ዘላላም ሕይወት የሚመራው እውነት ይላል። a

ኡስማን ‘ይህ ምን ዓይነት እውነት ነው?’ ሲል አሰበ። የማወቅ ጉጉት ስላደረበት ወደ ቤቱ ይዞት ሄደና ወዲያውኑ ሙሉውን መጽሐፍ አነበበው። አምላክ ይሖዋ የተባለ የግል ስም እንዳለው ሲረዳ በጣም ተደሰተ! (መዝሙር 83:18 NW ) ኡስማን የአምላክ ዋነኛ ባሕርይ ፍቅር እንደሆነና ሰዎችን በእሳታማ ቦታ የማሠቃየቱ ሐሳብ በአምላክ ዘንድ አስጸያፊ መሆኑንም ተገነዘበ። (ኤርምያስ 32:35፤ 1 ዮሐንስ 4:8) በመጨረሻም በቅርቡ ይሖዋ ምድርን ወደ ገነትነት በመለወጥ ሰዎች ለዘላለም እንዲኖሩባት የሚያደርግ መሆኑን ከንባቡ ተረዳ። (መዝሙር 37:29፤ ራእይ 21:3, 4) መሐሪና አፍቃሪ ከሆነ አምላክ የተገኘ እንዴት ያለ አስደናቂ እውነት ነው! ኡስማን ፈጽሞ ባልተጠበቀ ቦታ እውነትን እንዲያገኝ ስላስቻለው ልቡ በአድናቆት ስሜት ተሞልቶ ይሖዋን አመሰገነው።

ከጥቂት ቀናት በኋላ ኡስማን በጓደኞቹ እርዳታ የይሖዋ ምሥክሮችን የመንግሥት አዳራሽ አገኘና ለመጀመሪያ ጊዜ በስብሰባ ላይ ተገኘ። በስብሰባው ላይ አንድን ምሥክር ቀርቦ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያስጠናው ጠየቀው። ከባድ የቤተሰብ ተቃውሞ ቢገጥመውም ኡስማን መንፈሳዊ እድገት ማድረጉን ቀጠለና ተጠመቀ። (ማቴዎስ 10:​36) ዛሬ በጉባኤ ውስጥ ሽማግሌ ሆኖ ያገለግላል። ቆሻሻ መጣያ ውስጥ የተገኘ አንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፍ ይህንን የመሰለ ውጤት ማስገኘቱ እንዴት አስገራሚ ነው!

[የግርጌ ማስታወሻ]

a በ1968 በይሖዋ ምሥክሮች የታተመ።