በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምሥጢርን ለመግለጥ ጊዜ አለው

ምሥጢርን ለመግለጥ ጊዜ አለው

ምሥጢርን ለመግለጥ ጊዜ አለው

አንዳንድ ጉዳዮችን በምሥጢር መያዝና አለመያዝ ሰላምን በማስፈን ረገድ ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል። ይሁን እንጂ ምሥጢር የሆነውን ጉዳይ የምንገልጥበት ጊዜ ይኖራል? ነቢዩ አሞጽ ይሖዋን በሚመለከት ምን ብሎ እንደተናገረ ልብ በል:- “በእውነት ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለባሪያዎቹ ለነቢያት ካልነገረ በቀር ምንም አያደርግም።” (አሞጽ 3:7) ምሥጢር መጠበቅን በተመለከተ ከእነዚህ ቃላት አንድ ነገር ልንማር እንችላለን። ይሖዋ ለተወሰነ ጊዜ አንዳንድ ጉዳዮችን በምሥጢር ሊይዝና ከጊዜ በኋላ ለአንዳንድ ግለሰቦች ሊያሳውቃቸው ይችላል። በዚህ ረገድ ይሖዋን ልንመስለው የምንችለው እንዴት ነው?

አንዳንድ ጊዜ በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ያሉ የተሾሙ እረኞች አንድን ጉዳይ በምሥጢር መያዙን አስፈላጊ ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ። (ሥራ 20:28) ለምሳሌ ያህል ለጉባኤው ጥቅም በማሰብ አንዳንድ ዝግጅቶችን ወይም በጉባኤ ኃላፊነት ረገድ የተደረጉ ለውጦችን ዝርዝር እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ በምሥጢር ለመያዝ ይወስኑ ይሆናል።

ይሁን እንጂ በዚህ ጊዜ ምሥጢሩ መቼና እንዴት ባለ ሁኔታ ይፋ እንደሚሆን ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ሰዎች ግልጽ ማድረጉ አስፈላጊ ነው። አንድ ጉዳይ ይፋ የሚደረገው መቼ እንደሆነ ማወቃቸው ያ ጊዜ እስኪደርስ ድረስ በምሥጢር እንዲይዙት ሊረዳቸው ይችላል።​​—⁠⁠ምሳሌ 25:9