በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በ2003 ብሔራት አቀፍ ስብሰባዎች ይካሄዳሉ

በ2003 ብሔራት አቀፍ ስብሰባዎች ይካሄዳሉ

በ2003 ብሔራት አቀፍ ስብሰባዎች ይካሄዳሉ

ጥቅምት 6, 2001 ቅዳሜ ዕለት የፔንሲልቫኒያው የመጠበቂያ ግንብ መጽሐፍ ቅዱስና ትራክት ማኅበር አባላት ዓመታዊ ስብሰባ በዩ ኤስ ኤ፣ ጀርሲ ሲቲ ኒው ጀርሲ ተደርጎ ነበር። ከስብሰባው በኋላ የማኅበሩ አባላትና እንግዶቻቸው በተገኙበት ልዩ ፕሮግራም ተካሄደ። በቀጣዩ ቀን በካናዳና በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኙ አራት ከተሞች በተደረጉ ተጨማሪ ስብሰባዎች ላይ የይሖዋ ምሥክሮች የአስተዳደር አካል አባላት የመደምደሚያውን ንግግር ካደረጉ በኋላ የሚከተለውን ማስታወቂያ ተናገሩ:-

“የወደፊቱን ጊዜ በጉጉት በምንጠባበቅበት በአሁኑ ጊዜ የአምላክ ሕዝቦች አንድ ላይ መሰብሰባቸውን ፈጽሞ ችላ ማለት አይኖርባቸውም። ሐዋርያው ጳውሎስ ታላቁና አስፈሪው የይሖዋ ቀን መቅረቡን ስናይ አንድ ላይ መሰብሰባችንንና አንዳችን ሌላውን ማበረታታታችንን ይበልጥ መቀጠል እንዳለብን አሳስቦናል። (ዕብራውያን 10:24, 25) ከዚህ ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክር ጋር በመስማማት በሚቀጥለው ዓመት [ማለትም በ2002] በሁሉም የዓለም ክፍሎች የአውራጃ ስብሰባዎችን እናደርጋለን። ከዚያም ይሖዋ ፈቃዱ ከሆነ በ2003 በአንዳንድ የዓለም ክፍሎች ልዩ ብሔራት አቀፍ ስብሰባዎችን ለማድረግ አቅደናል። የዓለም ሁኔታዎች ወዴት እያመሩ እንዳሉ የምናስተውልበትና ንቁ ሆነን የምንኖርበት ጊዜ አሁን ነው።”

ይህ ሥርዓት ወደ ፍጻሜው ሲቃረብ ያልታሰቡ አደጋዎችና ውጥረቶች እየጨመሩ ቢሄዱም የአምላክ ሕዝቦች በሚሠሩት ሥራ ወደ ፊት መግፋት አለባቸው። የመጽሐፍ ቅዱስን የማስጠንቀቂያ መልእክት ጨምሮ የመንግሥቱ ምሥራች ለሁሉም ብሔር፣ ነገድ፣ ቋንቋና ሕዝብ መታወጅ አለበት። ሰዎች ‘የፍርዱ ሰዓት ስለደረሰ አምላክን እንዲፈሩና ክብርንም እንዲሰጡት’ ሊነገራቸው ይገባል። (ራእይ 14:6, 7) ስለዚህ እንደ ሰማያዊው አባታችን መልካም ፈቃድ በ2003 በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ብሔራት ዓቀፍ ስብሰባዎችን ለማድረግ ዝግጅቶችን እያደረግን ነው።

በመጀመሪያ እነዚህ ስብሰባዎች በሰሜን አሜሪካ በሚገኙ በአንዳንድ ከተሞችና ከዚያ ብዙም ሳይቆይ በአውሮፓ እንዲካሄዱ ጊዜያዊ እቅድ ተይዟል። ትንሽ ቆየት ብሎ ልዑካን እስያ ውስጥ በሚገኙ አንዳንድ ከተሞች በሚደረገው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ዝግጅት ይደረጋል፤ ከዚያም በዓመቱ መገባደጃ አካባቢ ሌሎች ተጨማሪ ልዑካን ወደ አፍሪካ፣ ደቡብ አሜሪካና የፓስፊክ ክልሎች ይሄዳሉ። የተመረጡ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ስብሰባ ወደሚደረግባቸው አንዳንድ ቦታዎች እንዲልኩ ጥያቄ የሚቀርብላቸው የተወሰነ ቁጥር ላላቸው ልዑካን ስለሆነ ሁሉም ሰው በዚህ ዝግጅት እንዲታቀፍ ግብዣ ማቅረብ አስቸጋሪ ነው። ሆኖም ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ ጥቂት ልዑካን በሁሉም ስብሰባዎች ላይ መገኘታቸው የሚያስደስት ነው።

ስብሰባዎቹን የሚመለከት መረጃ በቅርቡ ለይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች ይላካል። ተጋባዦቹ ልዑካን የሚገኙባቸው ስብሰባዎች የሚደረጉበትን ትክክለኛ ቀንና ቦታ የሚመለከቱ መረጃዎች በቅርንጫፍ ቢሯቸው በኩል ይደርሳቸዋል። ስለዚህ በአሁኑ ወቅት ይህን ጉዳይ በሚመለከት ጥያቄ ማቅረብ አያስፈልግም።

የስብሰባዎቹ ልዑካን ሆነው የሚመረጡት መልካም ምሳሌዎች የሚሆኑና በሚሄዱበት ስፍራ ለሚገኙ ወንድሞች ወንድማዊ ፍቅር የሚያሳዩ ራሳቸውን ወስነው የተጠመቁ ምሥክሮች ብቻ ይሆናሉ። ልዑካኑ በሚሄዱበት ስፍራ ያሉ ወንድሞች በተራቸው ለጎብኚዎቹ ፍቅራዊ አቀባበልና ከልብ የመነጨ እንግዳ ተቀባይነት ማሳየት የሚችሉበት አጋጣሚ ያገኛሉ። (ዕብራውያን 13:1, 2) ይህ ‘እርስ በእርሳቸው እንዲበረታቱ’ ያስችላቸዋል። (ሮሜ 1:11, 12) እነዚህን ዝግጅቶች የሚመለከቱ ተጨማሪ ዝርዝር ጉዳዮች ልዑካኖችን እንዲልኩ ጥያቄ ከቀረበላቸው ቅርንጫፍ ቢሮዎች ማግኘት ይቻላል።

በአብዛኞቹ አገሮች በ2003 እንደ ሌላው ጊዜ ሁሉ የሦስት ቀን የአውራጃ ስብሰባዎችን ለማካሄድ ዝግጅት ይደረጋል። ሁሉም አንድ ላይ በመሰብሰብ ‘ለማዳመጥ፣ ለመማርና ለመበረታታት’ የሚችሉበት አጋጣሚ ያገኛሉ። (ዘዳግም 31:12፤ 1 ቆሮንቶስ 14:31) ይህም የአምላክ ሕዝቦች በሙሉ ‘የይሖዋን ጥሩነት እንዲቀምሱና እንዲያዩ’ አጋጣሚ ይሰጣቸዋል። (መዝሙር 34:8) በሁሉም ብሔራት ዓቀፍ ስብሰባዎችና በአብዛኞቹ የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ ሚስዮናውያን የሚገኙ ሲሆን አንዳንዶቹም በፕሮግራሙ ላይ ክፍል ይኖራቸዋል።

በዚህ ዓመት “ቀናተኛ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች” የሚል ርዕስ ያለው የአውራጃ ስብሰባ የሚደረግ ሲሆን ይህም ተጨማሪ ምሥክርነት እንድንሰጥ የሚያነሳሳን ይሆናል። በዚህ ስብሰባ ላይ ስንገኝ በቀጣዩ ዓመት ይሖዋ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ለመገኘት ያለን ፍላጎት ይበልጥ ይጨምራል። ይህም አሁን ከምንኖርበት ጊዜ አንጻር ‘ነቅተን እንድንጠብቅና ተዘጋጅተን እንድንኖር’ ይረዳናል።​—⁠ማቴዎስ 24:42-44